@yeslasebarya3: በጎንደር ከተማ ሕገወጥ የቁማር ቤቶችና ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት ላይ እርምጃ ተወሰደ በጎንደር ከተማ በሕግ የተከለከሉ የቁማር ቤቶችን፣ ቤቲንግ ቤቶችን፣ የጫትና ሽሻ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቦታዎች ላይ የቁጥጥር እርምጃ መወሰዱን የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ። የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም እንደገለጹት፣ በከተማዋ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅና በሕግ የተከለከሉ ተግባራትን ለመቆጣጠር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተጠናከረ የቁጥጥር ሥራ ተካሂዷል። በተካሄደው ቁጥጥርም በ84 የቁማር ቤቶች፣ በ13 ሽሻና 12 ጫት ቤቶች ጨምሮ በድምሩ 109 ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን አቶ አለልኝ ገልጸዋል። እርምጃው የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ሕገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር በከተማ ደረጃ ከተጀመረው የተጠናከረ የቁጥጥር ሥራ አካል መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል። ለህብረተሰቡ ጉዳት የሚያደርሱ ሕገወጥ የቁማር፣ የቤቲንግ፣ የጫትና የሽሻ ንግድን ጨምሮ በመሰል ሕገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃም ከዚህ በኋላ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አቶ አለልኝ አስገንዝበዋል። ህብረተሰቡ ሕገወጥ ተግባራትን በመከላከልና ሰላምና ፀጥታን በማስጠበቅ ረገድ ለፀጥታ አካላት የሚያደርገውን የተለመደ ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል። ህብረተሰቡ ሕገወጥ ተግባራትን ሲመለከት በ058 211 5291 እና 097 718 6161 የጥቆማ ስልክ ቁጥሮች መረጃ እንዲያደርስም ተጠይቋል።
Chalachew Dagne Fans
Region: ET
Tuesday 06 October 2026 18:29:09 GMT
Music
Download
Comments
user3047685680102 :
ህገወጥ ጫትቤት ማለት አልገባኝም መንግሰት ተብየው ቀረጥ እየቀረጠ መሰሎኝ የሚያሰገባው ጫቱን
2026-10-06 19:22:16
9
surafail :
እንደዚህ ያለ ቀልድ አይቸ አላቅም ቁማር የሚያጫውቱ እኮ ግብር የከፈሉ መሰለኝ
2026-10-07 18:22:05
1
amsal ay :
ጫት ቤት ነው ያልከው ክቡር ከንቲባ አንዳይሰሙህ
2026-10-07 07:30:28
2
የመዘርጋት ዓመት ይሆናል :
አዘዞ ያሉ ቁማር ቤቶችን ከገነቱ ጃንቦ ሀውስ ጎን ያሉትን ምናለ እርምጃ ብትወስዱ
2026-10-07 06:30:48
1
Kepaso 22 :
እኛን ያስቸገረን ገዳይ ነው እነሱን ያዙልን !!!
2026-10-07 17:24:56
1
Marko :
grosri bate yemtzgu wanawe esu new
2026-10-07 17:41:55
0
@Smegnew Gebrie :
ጥሩ ጅማሮ ነው ግን ማራኪ ብቻ 153ቁማር ቤት አለ ይጠናከር።
2026-10-07 16:52:44
0
G/G/G/w :
አሁን ጥሩ ስራ ሠራችሁ በጥቅሉ ቁማር ቤቶች ለትዉልዱ ጥሩ አይደሉም
2026-10-07 14:20:12
0
user58019749437802 :
አለልኝ ጀግና መሪ ነህ በርታ
2026-10-07 12:07:43
0
Tadila Misganaw :
በትክክል በርቱ
2026-10-07 17:22:20
0
benjamin :
በጣም አሪፍ ስራ
2026-10-07 11:52:55
0
አብርሃም :
ወንድም በርታል አለልይ
2026-10-07 15:09:46
0
Wendwesen :
ቢንጎምክልክልነው
2026-10-07 15:17:00
0
amane :
መንግስትኮ ሊፈቅድ ነው ስንት ወንጀል የሚሰራበት ሀገር አሁን ይሄ ዜናነው
2026-10-07 16:32:51
0
MULE 🦘 :
እዉነት የህግ እርምጃ ከተወሰደ ደስ ይላል
አላስፋላጊ ህዝብን የሚበዘብዝ ቁማር ነዉ ዝጉልን🙏🙏
2026-10-07 17:42:53
0
Amanuel :
ያስቸገረ መች ቃሚ ነው መች ቢንጎ ተጫዋች ነው አጋች እና አንዳድ ባለስልጣኖች ናቻው እንጂ
2026-10-07 20:09:01
0
Messe :
በጣም ደስ የሚልዜና
2026-10-07 18:07:12
0
micheal Alebel :
መላካም ሰው 🥰🥰🥰🥰
2026-10-06 19:09:05
0
ፍኖ መዳኒቱ :
አለልኝ አለም በርታ ወንድማችን
2026-10-07 09:56:56
0
Mf abohye Abohye mf :
ለማን ልናገር አቶ አለልኝ የተከበሩ ስራው ይበል የሚያሰኝ ነው
2026-10-07 07:47:14
0
bini Aserat :
ሀሳባችሁ ኮ ጥሩ ነው
ግን ደግሞ እሄንን ስታደርጉ ለወጣቱ የስራ እድል
እየፈጠራችው ቢሆን ጥሩ ነበር
2026-10-07 11:42:58
0
Zemene Tiruneh :
ማሪያምን ይህን የቁማር ቤት እስከመጨረሻው ድረስ መዘጋት አለበት አለበለዚያ ስርቆት እና ዝርፌያ አያቆምም በተለያዩ ቦታዎች ከተቀሙ በኋላ ብር እየተቀጡ ነው ሚመለስ ስለዚህ የመጨረሻ መሆን አለበት
2026-10-08 07:27:51
0
አይሰው ከንቱ የ16Leje :
በጣም ወጣቱ ይስተካከላል
2026-10-07 09:45:45
0
bayuh :
2026-10-07 09:03:57
0
yesuf ibrahim :
መልካም ነው ግን .........
2026-10-06 20:28:27
0
To see more videos from user @yeslasebarya3, please go to the Tikwm
homepage.