@anhpham3644: #thudong2026 #thoitrangtreem

anhpham
anhpham
Open In TikTok:
Region: VN
Wednesday 07 October 2026 02:45:23 GMT
6
0
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @anhpham3644, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#post 1064 | ሰንበት በክርስቲያናዊ አስተምህሮ የሥጋ ዕረፍት ብቻ ሳትሆን፣ የነፍስ መታደሻ፣ የፈጣሪን ድንቅ ገብረ ኃይልና ፍቅር የምናስብበት፣ ከሕይወት ምንጭ ጋር የምንገናኝበት ታላቅ መንፈሳዊ ድልድይ ነች። በዓለም ውጣ ውረድ፣ በዕለታዊ ጭንቅ፣ በሥጋ ድካምና በሕሊና ውጥረት ውስጥ ለደከመች ነፍስ አምላክ የሰጣት ታላቅ መጽናኛና ዕረፍት ሰንበት ነች።  ዓለም ሳታቋርጥ
#post 1064 | ሰንበት በክርስቲያናዊ አስተምህሮ የሥጋ ዕረፍት ብቻ ሳትሆን፣ የነፍስ መታደሻ፣ የፈጣሪን ድንቅ ገብረ ኃይልና ፍቅር የምናስብበት፣ ከሕይወት ምንጭ ጋር የምንገናኝበት ታላቅ መንፈሳዊ ድልድይ ነች። በዓለም ውጣ ውረድ፣ በዕለታዊ ጭንቅ፣ በሥጋ ድካምና በሕሊና ውጥረት ውስጥ ለደከመች ነፍስ አምላክ የሰጣት ታላቅ መጽናኛና ዕረፍት ሰንበት ነች። ዓለም ሳታቋርጥ "ሩጥ፣ ድከም፣ አትርፍ፣ ውጣ፣ ውረድ" እያለች የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ድካም ስታበዛበት፤ የሰንበት ጌታ የሆነው ኢየሱስ ግን በፍቅር፣ በትሕትናና በምሕረት ድምፅ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ የለሰለሰ ሸክሜም ቀሊል ነውና" (ማቴ 11፥28-30) በማለት ወደ መለኮታዊ ዕረፍቱ ይጠራናል። ​ሰንበት የተሰጠችው ሰውን በከባድ እስራት፣ በሕግ ድንጋጌና በባርነት ልታስጨንቅ ወይም ልታጠብቅ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ ከውጥረትና ከኃጢአት ባርነት ነፃ ልታወጣ፣ ልታሳርፍና ልታድስ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል የታወሩትንና የተጨነቁትን ፈሪሳውያንን ሲገስጽ "ሰንበት ስለ ሰው ተፈጠረ እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ ስለዚህ የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው" (ማር 2፥27-28) በማለት እንዳስተማረን፤ ሰንበት የፍቅር፣ የሕይወት፣ የፈውስና የነፃነት ቀን ነች። እውነተኛዋ ሰንበትና የዕረፍት አምላክ እርሱ ክርስቶስ ራሱ ነው፤ የሰው ልጅ ከኃጢአት፣ ከጥላቻና ከጭንቀት ሸክም አርፎ በእርሱ ሰፊ ምሕረት ውስጥ እውነተኛውን የልብ ሰላም ያገኛል። ​በዚች ቅድስት ቀን በሳምንቱ የገጠሙንን ተስፋ መቁረጦች፣ ፍርሃቶች፣ የሥጋና የምድር ውጥረቶች ሁሉ በሰንበት ጌታ እግር ሥር አስቀምጠን፣ ከምድር ከንቱነት ይልቅ የሰማዩን አባታችንን ሰላምና ማጽናናት እንቀበላለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ቀን የተመታች እጅ ያላቸውን፣ ሽባዎችንና የታመሙትን በፍቅር እንደ ፈወሰ፤ እኛም ልባችንን ለይቅርታ፣ ለእርቅ፣ ለምሕረትና ለበጎ ሥራ ሁሉ እንከፍታለን፤ የተጣላነውን ይቅር በማለት እውነተኛውን የሰንበት ፈውስ በሕይወታችን እንለማመዳለን። በጸሎት፣ በምስጋና፣ በቃሉ ብርሃንና በመንፈሳዊ ስብሰባ ነፍሳችንን እያደስን፤ ለሚመጣው አዲስ ሳምንት የሚሆን መንፈሳዊ ብርሃን፣ ጽናትና ረድኤት ከሕይወት ምንጭ እንቀዳለን። የኔ ተወዳጆች የሰንበት ጌታ የሆነው አምላክ ዘላቂ ዕረፍትና ሰላምን፣ ለቤታቹ ለቤተሰባችሁ ደግሞ የተረፈ በረከትንና ፍቅርን ይስጥልን! መልካም ሰንበት! እወዳችኋለሁ❤🙏 #አሼ_ነኝ✌ #ቤቱን_like_share_follow_copylink_repost_ማድረጋችሁን_አትርሱ🙏 #ሰንበት

About