@luv4skai_: queen of everything #skaiwater #fyp #xyzabc #underground #xbcyza

LUV4SKAI
LUV4SKAI
Open In TikTok:
Region: GB
Thursday 08 October 2026 23:37:59 GMT
4436
978
3
31

Music

Download

Comments

m_drid3
madrid :
Gurl i canttt😩
2026-10-08 23:53:27
12
wayt0high
￴ ￴ ￴ ￴ ￴￴ ￴ ￴ ￴ ￴ gimpr :
2026-10-08 23:46:58
1
sadchoppa
T :
Like how u find dat
2026-10-09 00:08:45
0
To see more videos from user @luv4skai_, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ጴንጤ ነኝ፡፡እልል ያልኩ ጴንጤ፡፡እሁድ እሁድ ቸርች የማልቀር ጴንጤ..!!ዛሬም እንደተለመደው በጠዋት ሂጄ በስድስት ቁጥር ባስ ወደቤቴ እየተመለስኩ ነበር አንድ ቀልብ የራቀው ሰውዬ ዘሎ ገብቶ አጠገቤ የቆመው፡፡ እባብ የመሠ፤ከስልባቦት የቀጠነ ነገር ነው፡፡ በዚህ ቅጥነቱ የያዘው ቦርሳ እራሱ እሱን ይበልጠዋል።በዛላይ ይቅበዘበዛል፡፡ወዲህ ወዲያ ይላል፡፡እጁን ያውለበልባል... እቺ ንብ ጤና የላትም እንዴ?? ሂጂ ወዲያ..ሂጂ.. (በመስኮት የገባችው ንብ አናቱ ላይ ጥዝዝዝ እያለች እረፍት ነስታው ሳይ አሳዘነኝና ቦርሳውን እኔ ልያዝልህ??(አልኩት ባስ ውስጥ ለቆመ ሠው ቁጭ ያለው እቃ መሸከም ግዴታው ነው አይ አይሆንም ይከብድካል!!(
ጴንጤ ነኝ፡፡እልል ያልኩ ጴንጤ፡፡እሁድ እሁድ ቸርች የማልቀር ጴንጤ..!!ዛሬም እንደተለመደው በጠዋት ሂጄ በስድስት ቁጥር ባስ ወደቤቴ እየተመለስኩ ነበር አንድ ቀልብ የራቀው ሰውዬ ዘሎ ገብቶ አጠገቤ የቆመው፡፡ እባብ የመሠ፤ከስልባቦት የቀጠነ ነገር ነው፡፡ በዚህ ቅጥነቱ የያዘው ቦርሳ እራሱ እሱን ይበልጠዋል።በዛላይ ይቅበዘበዛል፡፡ወዲህ ወዲያ ይላል፡፡እጁን ያውለበልባል... እቺ ንብ ጤና የላትም እንዴ?? ሂጂ ወዲያ..ሂጂ.. (በመስኮት የገባችው ንብ አናቱ ላይ ጥዝዝዝ እያለች እረፍት ነስታው ሳይ አሳዘነኝና ቦርሳውን እኔ ልያዝልህ??(አልኩት ባስ ውስጥ ለቆመ ሠው ቁጭ ያለው እቃ መሸከም ግዴታው ነው አይ አይሆንም ይከብድካል!!("ቆጣ ብሎ እጁን ሲያሸሸኝ ሌላኛ የቆመው ሰው.. ይያዝልክ እንጂ ስጠው...ጎረምሳ ነው.. አለ(እሱም ወሰድ የሚያደርገው እብድ ነገር ነው፡፡ተከታትለው ሲገቡ የሚተዋወቁ ቢመስለኝም የተለያዩ ሰወች ናቸው፡፡እንደ እብድ የሚያደርገው ሰውዬ በመሀል በመሀል ተመለስ ብዬካለው....ዋ...በኋላ እንዳታዝን....ዋ..(ከገባ ጀምሮ እቺን ቃል ሲደጋግማት ነው ወሰድ እንደሚያደርገው ያወቅነው፡፡ስልባቦቱ ሰውዬም ገልመጥ አርጎ አይቶኝ "ምን ገዶኝ" በሚል ወፍራም ቦርሳውን አሳቀፈኝ፡፡እውነትም ይከብዳል። መንገዱ ስለተዘጋ ባሷ አስሬ ትቆማለች፡፡እብዱ አስሬ "ተመለስ"ማለቱን አላቆመም ቦርሳውን ያሸከመኝ ሰውዬም መቅበዝበዙ ብሶበት ጭራሽ "አረ ሽንቴን"እያለ መለፈፍ ጀምሯል፡፡ ንቧም ጥዝዝዝ ማለቷን አላቆመችም.. አረ ሹፌር ሽንቴን ልፈነዳ ነው...አረ አውርደኝ....(ስልባቦቱ ሰውዬ ጮኸ ተመለስ ብዬካለሁ...ዋ....ተመለስ(ወሰድ የሚያደርገው ጨለል ጋ ባሷን በጠበጧት የባሱ ሹፌር እንዳልሰማ ሲነዳ ቆሞ የሚቁነጠነጠው ሰውዬ ዞር ስል ብልቱን በሁለት እጁ አቅፎ ተዝለፍልፎ ሲወድቅ ተገጣጠምን፡፡ሽንት እንዲ ያደርጋል እንዴ!?? በየሱስ ስም አልኩኝ...በየሱስ ስም!!ደገምኩት፡፡ሰውዬው ግን መንፈራፈሩን አላቆመም አደራ ሩፋኤል...አደራ ሩፋኤል....(ይላል በወደቀበት፡፡ሩፋኤል ነው ጌታ ነው ሚያድነው???ግራ ገብቶኝ አየሁት እባካችሁ አድርሱኝ...አደራ ሩፋኤል ገዳም ውሰዱኝ..እባካችሁ....ሆዴ ተነፋ( አለ እያቃሰተ፡፡ተመለስ ከሚለው እብድ በቀር ባሱ ሁሉ ትርምስምሱ ሲወጣ እብዱ የባሱን በር መከፈት ጠብቆ እብስ ብሎ ወጣ።አደራ ሩፋኤል ገዳም የት እንደሆነ ባናቅም ከባስ አስወጥተነው ቦርሳውን እንደተሸከምኩ ቆሜ የሚሆነውን እያየሁ አጠገባችን ፈጥና መጥታ የቆመችው ራይድ ብንን አደረገቺኝ እ ራይድ ነው ወንድም..? አዎ አዎ ና እባክህ አድርሳቸው፡፡(አሉ የተሰበሰቡ ሰወች፡፡አድርሳቸው??እነማንን?ደነገጥኩ፡፡ግን አልቀረልኝም አዋክበው አስገብተውኝ ከሚንቆራጠጠው ሰውዬ ጋ እየተንቆራጠጥኩ ጉዞ ጀመርን፡፡ብዙ ሳንጓዝ ከአዲስ አበባ ወጣ እንዳልን ቆምን። ደርሰናል አይዞክ ወንድሜ ውረዱ ውረዱ... ያ ከጥንብ የሚከብድ ቦርሳውን እየጎተትኩ ወረድ።ባለራይዱ ደሞ ሰውየውን እየጎተተ አስቤ የማላውቀው ገዳም ውስጥ ባዶ እግሬን እራሴን አገኘሁት"አደራ ሩፋኤል ገዳም'' ይላል።ከበሩ አለፍ እንዳልን ደሞ. እዛጋ ውሰዱኝ እዛጋ እዛጋ..(ከቤተክርስትያኑ በር አለፍ ብላ የተሰራች ቤት እየጠቆመን ስልባቦቱ ሰውዬ እያቃሰተ ጮኸ።እኛም ይዘነው እንደደረስ ጠቆር ያሉ አረጋዊ መለኩሴ ልትፈርስ የደረሰች ደሳሳ ቤታቸውን እየከፈቱ እኩል ደረስን፡፡ አባ..አባቴ...ታማሚ ነው፡፡እዚህ ገዳም ውሰዱኝ ብሎ... (ባለራይዱ ቀባጠረ ።አንገቱ ላይ ክር ስላየሁ እኔ ዝም ማለትን መርጩ የሚሆነውን ማየት ጀምሬያለሁ ምነው ምን ሆነ ልጆቼ?አሉ እርግት ያሉ ናቸው፡፡ከጥቁረታቸው የተነሳ አይናቸው እና ጋቢያቸው ብቻ ነው ነጭ፡፡ምናልባት ምላሳቸው ቀይ ይሆን... አባ ይቅርታ ሽንቴን ወጠረኝ መሽናት አልቻልኩም፡፡ሁሉም ገብቶኛል፡፡ይፀልዩልኝ አባ(ግራ ገባኝ፡፡ይሄ ስልባቦት ማነው ቆይ???ያቃቸዋል ማለት ነው?(አባ እንድንገባ በአንገታቸው ጠቆም አድርገውን ሲገቡ ተከተልናቸው፡፡በጠራራ ፀሀይ ብርድ ብርድ የምትል ጠረኗ የሚጣፍጥ ቤት ውስጥ ዘለቅንና እንደተቀመጠን. ዘገየህ ልጄ..አያጠፉ ጥፋት ነው ያጠፋከው ከዚህ ወዲያማ.. ስለሩፋኤል አባ መሞቴ እኮ ነው፡፡ማሩኝ አይ እሱስ ምህረት የጌታ ነው፡፡አየህ እዚህች ገዳም የዛሬ ሳምንት ስትረግጥ ጀምሮ አውቄህ ነበር፡፡የመጣከው በተልእኮ መሆኑን ወገብህ ስር ወሽቀህ በመጣከው ስለት አውቄያለሁ፡፡አንተ ግን ለሱባኤ ብለህ ቤቴ ድረስ መጣህ፡፡እኔም ትታነፃለህ ብዬ አስገባሁክ። ያው አንተ ተልእኮህ ታቦቱን ሰርቆ መሄድ ስለነበር እኔ የዋዜማውን ማህሌት ልቆም በሌሊት ስወጣ አንተ ታቦቱን በቦርሳህ ከተህ ወጣህ...(አባ ገና ታቦት ሲሉ ሰውነቴን ውርር አረገኝ፡፡እውነት እዚህ ቦርሳ ውስጥ ያለው ታቦት ነው? ተርበተበትኩ፡፡የምገባበት አጣሁ፡፡ጴንጤ ብሆንም የታቦትን ሀይል ሲወራ ሰምቻለሁ. አዎ ሁሉም በደሌን አምናለሁ ብቻ ሆዴ ሊፈነዳ ነው ሽንቴን ወጥሮኛል አሁን ፀልዪልኝ አባቴ.. አየህ በጣም የሚያሳዝነው ግን ይቺን ሌባ ሁሉ ሚፈልጋትን ታቦት ፍለጋ መጥተህ በቦርሳህ ተሸክመህ የወጣከው ታቦት ሳይሆን ተመሳስሎ የተሰራ የወንዝ ጥቁር ድንጋይ ነው፡፡ልጄ ሌብነትምኮ እውቀት ይፈልጋል።አይደለም አንተ የማታቀው ይቅርና የሚያቁትም ታቦትን አይሰርቁም፡፡እኔም ይህንን ሁሉ ስታደርግ ዝም ያልኩህ አውቄ ነው፡፡ከቤተክርስትያን እንኳን ታቦት በተንኮል ጠጠር አንስቶ መውጣት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል እንድታውቅ ነው፡፡እርግጥ ታቦት ተሰርቆ እናውቃለን ብዙ ሰውም ታቦት ተአምር አያደርግም ሲል ይሰማል፡፡የሚገርማችሁ ግን ታቦት ሀይሉ በእግዚአብሔር ሀይል ለሚያምኑ ብቻ ነው፡፡ያንተ ጣት ካንተ ብትቆረጥ ለኔ አታገለግልም ታቦት ከክርስትያን ቢሰረቅ ታቦት አይሆንም ስለዚህ ታቦትን ለመስረቅ ለማጣጣል ብዙ አትጣጣሩ ሌላው ታቦት ማለት ማደርያ ነው፡፡ፅላት ደሞ የእግዚአብሔር ቃሉ የተፃፈበት ሰሌዳ ማለት ነው፡፡በሌላ አነጋገር ታቦት ስጋችን ፅላት ደሞ ልብ ናት፡፡"አንድ ቤተክርስትያን ያለ ፅላት ሙሉ እንደማትሆንም አንድ ሰውም ያለ ልብ ሰው አይባልም"ስለዚህ ሙሉ ለመሆን ልብ ግዙ፡፡ያለበለዚያ ልባችሁ ልብ ሳይሆን ከእግዜሩ የተጣላ የመናፍቅ ታቦት(ማደርያ) ይሆናል፡፡አንተም የታመምከው ባለማስተዋል እንጂ እየተከተለህ "ተመለስ" የሚል ሰው ልኬብህ ነበር፡፡እሱ የኔ ረድ እንጂ እብድ አልነበረም፡፡አሁን በመኪና ያመጣችሁም ንሰሐ ልጄ ነው፡፡ችግር እንደሚፈጠር ስለማቅ እንዲከተልህ መልክተኛ ልኬበት ነው፡፡አያችሁ ቤተክርስትያን እንዲህ ናት ሊሰርቃት የመጣን በጥበብ ልቡን ትሰርቃለች እንጂ አሳልፋ አሰጥም፡፡እግዜር ደሞ "አንዳንዱን በመምህር ሌላው በተአምር ይመልሳል"።በል እግዚአብሔር ይፍታህ ልጄ እግዚአብሔር ይፍታህ...(አባ ምርቃቱ ከአፋቸው ሳያልቅ የወጣቱ ሱሪ ሲረጥብ እየጮኸ ሲተነፍስ ሲያለቅስ አይኔን ማመን አቅቶኝ ስርበተበት ጥዝዝዝ የምትል ድምፅ በበር በኩል ስትገባ ሰማሁና ቀና አልኩ፡፡አንዲት ንብ አባ ቆብ ላይ ስታርፍ አየሁ. ጎሽ መልእክትሽን አድርሰሽ መጣሽ..?ጀግኒት በይ እረፊ አሉ አባ ፈገግ እያሉ፡፡ያቺ ባስ ውስጥ ያየኋት ንብ ትዝ ብላኝ በድንጋጤ ነብስና ስጋዬ ተላቀቀ በሉ አሁን መሄድ ትችላላች፡፡የአደራው ሩፋኤል ከክፉ ይጠብቃችሁ...(አባ እቺን ቃል ሲያወጡ ቅር ቅር እያለኝ ከዚህ ወዴት እንሄዳለን?አልኳቸው፡፡እውነትም ከተዋህዶ የት ይኬዳል?!የትም ✍️ ቻቻ

About