@jahmc1: ~ሙዚቃው ሲጀመር ገና የምትሰሙት የወፍ ድምፅ ሌላ ታሪክ ውስጥ ያስገባቹሀል! ~ራሱ ገጣሚው አያ ሙሌ "ወፍዬ ለኔ ሶስተኛ ልጄ ናት... ስለዚህም አማረኛ ተናጋሪ ፍጡር በህይወት ዘመኑ ወፍዬን ቢያንስ አንድ ጊዜ ሊሰማ ግድ አለበት " ብሎ አደራ ስለጣለብን ~ታዲያ እኔ ግዴታዬን ደጋግሜ በመስማት ተወጥቻለሁ እላለሁ...ዘፈኑን ተረድቼው ባልጨረስውም ባይገባኝም የአያ ሙሌ ቅኔ...ቅኔ እንደፈችው ነው ስለሚባል ይህን ሀሳቤን ስለ "ወፊቱ" ዘፈን ላጋራችሁ አበበ ተካ ~"ወፊቱ" ❤ ~ዘፈኑን አበበ ተካ ደስ ከሚል የወፎች ድምፅ በኋላ እንዲህ ሲል ይጀምረዋል ልብን በሚሰርቅና በሚያሳዝን ድምፅ "ጭራ ጭራ የምታድረው፣ 4x እንዲህ አስናቀችኝ ቀድማኝ ጎጆ ወጥታ ጎጆ አስተማረችኝ ጎጆ ..አቤት ጎጆን..ወፍዬ አስቀናችኝ።" ~ታዲያ ከላይ ያለው ስንኝ ስለ አንድ ጭራ ስለምታድር ወፍ የራሷን ጎጆ ቤት ሰርታ ስለማደሯ ይነገራል..ይቺ ጭራ የምታድረው ምስኪን ወፍ (ወፏ በቅኔው ውስጥች ያለች ምስኪን ሴትን ወካይም ናት) ከጎጆ አልባው ገጣሚ ቀድማ የራሷን ጎጆ በመያዟ ገጣሚውን እጅግ አስቀንታዋለች! . ~ታዲያ ገጣሚው በጭራ አዳሪዋ ወፍ ወይም በለፍቶ አዳሪዋ ምስኪን ሴት ከመቅናት በተጨማሪ የሷን ጋሻ ጃግሬን መሆንን ተመኘ.... የሷ መከታ የሆነው ጃግሬ እንደሷ ጠንከራና ብርቱ መሆኑ ገብቶት ገጣሚው እንደሱ በርትቶ ጎጆውን እንዲቀልስና ራሱን እንዲችል እሱን መሆን ተመኝቶ እንዲህ ይላል በታችኛው ስንኝ... "እህህ... ምነው ባደረገኝ እህህ... የሷ ጋሻ ጃግሬ እንደምንም ብዬ እኔም ጥሬ ግሬ ያገዳ ጎጆዬን ባቆምኳት ማግሬ። " . ታዲያ ይሄ ገጣሚ የበቃ ሙሉ ሰው መሆን ይፈልጋል....የዚህ ሰው የመሆን ምኞቱ ደግሞ መስፈርቱ የራሱን ጎጆ ቀልሶ ከራሱ አልፎ ለሰው ለቤተሰቡ መትረፍ መቻሉ ነው.. ግን ሳይሆንለት ሲቀር በቁጭት እንዲህ ይላል ከታች "እህህ... አጉል በቃኝ ላ'ይል እህህ... ዐይን አይቶ ገምቶ ወይ ሞልቶ ላይሞላ ጆሮ አይችሉ ሰምቶ እንዴት ጎጆ ይቅር አርሶና ሸምቶ።" . ~አይኑ አይቶ እና ጆሮው ሰምቶ ከመመኘት... አለም ሞልታ ባትሞላም እንኳን ምድራዊ ጎጆ ወይም ቤት አልባ መሆኑ አሳዝኖታል!....ድንገት ምድራዊ ቤት ያጣው ሰው "ነፍሴስ ከሞትኩ በኋላ ቦታ ይኖራት ይሆን በሰማይ?" ብሎ ራሱን ሲጠይቅ እርግጠኛ መሆን አልቻለም የሰማይ ቤቱን ስለማገኝቱ... ከዛ ያቺን ጭሮ አዳሪ ወፍ(ምስኪን ሴት) እንዲህ ብሎ ይጠይቃታል ከታች "ገመና ከታቹ የሣር ቤት ያማረሽ ሚስጥረ መለኮት ማነው ያስተማረሽ? ካፈር ክዳን ጎጆ መሬቱን ፈልፍሎ ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ። " ~ታዲያ ከላይ ባለው ስንኝ ገጣሚው ወፏን "በሌሊቱ ተነስተሽ የምትዘምሪው ወይም ኪዳን የምታደርሽው ኧረ ለመሆኑ ሚስጥረ መልኮት (እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም ስጋ ለብሶ ተወልዶ ሰው ሆኖ በሰው አእምሮ ሙሉ ለሙሉ ሊመረመረ የማይችለውን መለኮታዊ ሚስጥር ማን አስተማረሽ?.....ድንግል ማርያምስ ይሄን ሚስጥረ ተረድታ በማይገባት ስፍራ ጌታን ስለመውለዷ ስለዛ መለኮታዊ ሚስጥር እንዴት አወቅሽ? "ይላታል...ግን ደግሞ ተመልሶ በምድር ቤት ማገኝቷ ሲገርመው በሌሊት ተነስታ ለአምላኳ የምታሰማውን ዝማሪ (ምስኪኗ ሴት የምታደርሰው ኪዳን..ቅዳሴ) ባሰበ ጊዜ ከሱ በተሻለ የሰማይ ቤት እንድምታገኝ ገባው...በመጨረሻም የምድሩን ረስቶ "ከሰማይ ቤት እጣሽ ማን በሰጠኝ ከፍሎ?" ሲል ይጠይቃታል . . ~ከሁለት ያጣ ከንቱ ሰው መሆኑ ቆይቶ ይገበዋል (የሰማይም የምድሩንም ቤት ) ከዛ ለራሱ ያዝናል...ሩቅ አስቦ ቅርብ ያደረውን ልቡንም ይወቅሳል..."ምን አለ ልቤ ቢቆጨው እንደዚህ ጎጆ አጥቶ ከማፈር" እያለ ለራሱ እያዘነ ደረቱን ይደቃል...ሀዘኑ የመጣው በስጋዊና በመንፈሳዊ ቤት ማጣቱ የተነሳ ነው!... ከታች ባለው ስንኝ እንዲህ ይገልፀዋል ሀዘኑን እኔን ዐይኔን እኔን ይብላኝ 4x የቀን ሰው ሌጣ አፈር ልቤ ሩቅ አሳቢው ቅርብ አድሮ ሲደፈር ምን ነበር ቢቆጨው ጎጆ አጥቶ ከማፈር።" . . ~ታዲያ ይቺ ለፍቶ ጭሮ አዳሪ ወፍ ወይንም በጠዋት ተነስታ ሰርታ ፣ ደክማና ለፍታ ለእለት ጉርስ ለእሷና ለልጆቿ የምትበቃው ምስኪን ሴት አንዲት ኢትዮጵያዊ እናት ናት!....ይቺ እናት የገጣሚው እናት፣ የናንተ እናት እና የኔ እናት ናት! ታዲያ የዚችን ምስኪን ኢትዮጵያዊ እናት የዕለት ኑሮዋን ገጣሚው በታችኛው ስንኝ እንዲህ ይገልጠዋል. "እህህ... ፈጣሪዋን አምና ያፏን ጥሬ ሰጥታ ለጭሮ አዳር ውሎ በዝማሬ ወጥታ አዳኝ እንዴት ያጥቃት ፍርድና ዳኛ አጥታ!" ~ታዲያ በላይኛው ስንኝ ይቺ ምስኪን ወፍ በጎጆዋ ውስጥ ልጆቿን ለማኖር ስትል በአፏ የያዘችውን ጥሬ ለኔ ይቅርብኝ ብላ ልጆቿን ትመገብላች...በሌሊት ተነስታ በዝማሪ ፈጣሪዋን አመስግና እና አምና ጭሮ ለመዋል ከጎጆዋ ትዋጣለች....ነገር ግን የሰው ልጅ ፈጣሪን አምና ጭራ በበላች በድንጋይ ያድናታል ይመታታል ፤ ያለ በደሏም ትሰቀያለች!" ይለናል..(ሌላኛው መልክት ወፏ የኛ እናት ስትሆን በሌሊት ተነስታ ፀሎቷን አድርጋ ቅዳሴዋን አድርሳ ፣ ካለት የዕለት ጉርስ ለኔ ይቅርብኝ ብላ ልጆቿን አብልታ ወደ ዕለት ስራዋ ስትሄድ...ያላቸውና በኑሮ የተሻሉት ሰዎች ፤ ኑሮዋን በውሸት፣ በማጨብርርና የልፋቷን ዋጋ በመካድ ቁስሏን ህመሟን ለፍታ ባደረች አብዝተውባት ትመለሳለች ይቺ ምስኪን እናት!) ይሄን ነው የሚገልፀው የላይኛው ስንኝ! . . ~ ይቀጥልና በታችኛው ስንኝ "ወፍ ከእኛ ምንም አትፈልግም ተርፎን እንኳን ምፅዋት አንሰጣትም ...ጭራሽ ለራሷ ጥራ ግራ በልታ በኖረች ...እኛ ሰዎች ግን በገዛ ጥረቷ የሰራችውን ያቺን አነስተኛ ጎጆዋን እንኳን እናፈርስባታለን ነፃነቷን እነጥቃታለን" ይለናል...." (በሌላኛው መልዕክትም ይቺ ምስኪን እናት አጣሁ የለኝም ብላ አታማርርም ፣ አይከፋትም...ስላጣችም ምፅዋት አለመነችም ፤ እኛም አልደገፍናትም..ይልቅ ማጣቷን ለመቅረፍ በቤቷ በራሱ ጉልበት በደከመች ምን አለበት የሰው ልጅ ባይገፋት ሊጣለት...መደገፉና ማበረታቱ ቀርቶባት ምን አለ እንቅፋት ባይሆንባት" ይለናል ከታች ባለው ግጥም "እህህ... አጣሁ፣ ነጣሁ ብላ እንደሰው ባይከፋት ምፅዋት ባትለምን ተርፎን ባንደግፋት ጎጆዋ ለቻላት ምን ነበር ባንገፋት!" . . ~ይቀጥልና "ይቺ ሴት በጎጆዋ ውስጥ ታማ ደክማ ስታጣጥርና እርዳታ ስትፈልግ..ማን ይሆን የሚደርስላት ፣ ውለታ ሳይቆጥር ለነፍስና ለሰባዊነት ብሎ ማን ይሆን የሚያግዛት?.... ብዙ ሰው እኮ ወልዶ ማሳደግ ያውቃል ይችላል ...ነገር ግን የእጇ ሲርቅባት ስታጣ የምታጎርሰው ለልጇ ..ማን አለ ከቶ እንደሷ የአፋን የሚሰጥ ለልጁ?" ይለናል በታችኛው ስንኝ የዚችን እናት (የወፍዬን ደግናታቸው ተመሳስሎ እያስገረመውና እየመሰከረላቸው ከታች ባለው ስንኝ "ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር? ማን ያቃናት ይሆን፥ ውለታ ሳይቆጥር ወልዶ ማሳደጉን ብዙ ሰው ቢያውቅበት ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት? ያፉን ማን ይሰጣል የእጁ ሲርቅበት?" ~በመጨረሻም ገጣሚው "እህህ ወፊቱ...እህህ ወፍዬ" እያለ ሲቀዋንና ህመሟን ተረድቶ ይገልፃል ከታች እህህ... ወፊቱ ኡሁሁ... ወፍዬ! ✍️Jah Mc #jahmc1 #ethiopianmusic #ayamule #abebeteka @gigi_shebabaw fans
Jah Mc
Region: ET
Friday 09 October 2026 13:13:41 GMT
Music
Download
Comments
objrctive :
አያ ሙሌ ከድምጻዊው ጋር በአንድ ቤት ይኖሩ ነበር አሉ። እናም አንድ ቀን አቤ ሴት ይዞ ይመጣና አያ ሙሌ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዲያድር ይጠይቀዋል።መሽቶ ስለነበር የሚሄድበት ስላልነበረው አያሙሌ ውጪ ያድርና በዚህም ተሰምቶት ነበር እናም ጥዋት ላይ በዛፎች ቅርንጫፍ ላይ ማልደው ጎጇቸውን ሲስሩ ተመለከተ ይህንን ዘመን አይሽሬ የማይጠገብ ግጥም ጻፈ:: ገጣሚው በለቅኔ አያ ሙሌ ልበ በና ሰው ወዳድ መልካም ሰው ነበር። ግን ደግ አይበረክትም
2026-10-09 14:14:33
9
ባህራን የሶፋ እጥበት እና ጠቅላላ ፅዳት :
ቃል የለኝም ለዚ ስራ
2026-10-09 15:10:53
5
teke yemaryam lij :
የምር ከሙዚቃም ከዘፈንም በላይ ጥልቅ ሀሳብ ከአምሮ በላይ የሆነ ስጦታ መታነፅ የሚፈልግ ሰው ራሱን የሚያንፅበት ምርጥ ጥበብ። ከማይረባ ስብከት ይሄን ሙዚቃ በቀን 2 ጠዋትና ማታ መውሰድ ለጆሮም ለህሊናም ሰላም አለው።
2026-10-09 13:28:51
7
አቤኔዘር :
👑 አያ ሙሌ የሰው ጥግ ። በጣም እናመሰግናለን ለዚህ ድንቅ! ስራህ በርታ።
2026-10-09 17:49:15
4
Nemo :
ይህ ታላቅ መዝሙር ነው።
2026-10-09 18:52:24
1
Damian Marley :
ተጀምሮ እስኪያልቅ ይለያል
2026-10-09 19:50:07
1
user3631357147281 :
አይ አያ ሙሌ መቃብር ውስጥ ሆኜ ብሰማው ይል ነበር ?!!
2026-10-09 19:15:35
1
habtom :
መቃብሬ ሆኞ እሰማታለው ብሎ ነበር ባለቅኔው
2026-10-10 06:17:54
1
EZRA :
ሙዝቃ ማዳመጥ ስፈልግ መጀመሪያ የምከፍተው ወፊቱን ነው caption ከማንበቤ በፊትም ለናቴ ነበር ማዳምጠው እናቴ ሺ አመት ኑርልኝ።
2026-10-09 20:11:28
1
Jossy16 🇱🇷 :
አቦ ይመችህ ወደ ፌቡ አላመጣኸውም እኮ እዚህ ባልመጣ አስመልጠኸኝ ነበር
2026-10-10 07:49:12
1
Ahmed mobile solution :
በህመም ውስጥ ሆኘ እንኳን እሰማዋለሁ ለምን ከህመሜ ስለሚፈውሰኝ
2026-10-10 03:19:41
1
nasir :
ብዙዎች ያላወቁት የሚያዉቁትም ያልተረዱት የኢትዮጵያ የስነ ግጥም አርማ ነዉ አያ ሙሌ
እንደ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር አይነት ደራሲ ደግሞ ባለቅኔነቱን ከዊሊያም ሼክስፒር ጋር ያስተካክለዋል የፍልስፍናዉን ከፍታ ከካህሊል ጂብራን ጋር ያመሳስሉታል በጥበብ አይን ደግሞ ሙሉዕ ጌታ ይሉታል ሙሉጌታ ተስፋዬን
አይገርምም ዛሬ ሁለቱም ሙሉጌታዎች በህይወት ዬሉም
2026-10-09 18:47:49
1
Hope :
እስኪ ቆይ ላንብበው 🙆🏽♂️
2026-10-09 13:15:31
1
Music Lover :
ፀዴ ኮንተንት🔥👌
2026-10-09 13:18:38
2
₩adu :
ሙሌ ሀያል ሰው🖤
2026-10-10 12:19:13
1
zehan :
❤️❤️❤️
2026-10-09 14:18:19
2
gigi_shebabaw fans :
❤️
2026-10-09 13:19:52
1
€phŕém :
🥰🥰🥰
2026-10-09 20:16:03
1
𝕐𝕆𝕋𝕆ℝᶜʰʳᵒⁿⁱᶜˡᵉ :
❤️❤️❤️
2026-10-09 20:49:41
1
ጓል በላይነሽ መስፋን ግደይ :
😢😢
2026-10-10 05:27:50
1
ayal :
🥰
2026-10-09 13:26:26
1
Fermu_90s :
❤️
2026-10-09 20:18:15
2
Estifanos Merto (የዘውድዬ ልጅ 👑) :
@Yuyu🫧 ታማ ትንፋሽ አጥሯት ደክማ ስታጣጥር፣ 🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️ማን ያቃናት ይሆን ውለታ ሳይቆጥር ።
2026-10-10 21:49:47
0
To see more videos from user @jahmc1, please go to the Tikwm
homepage.