@yetariekimahideri: 1. አንድን ሰው (እንደሰማህ እያወቅክ) በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራው፡፡ መልስ ካልሰጠህ ምናልባት የሆነ እየሰራው ያለው ነገር ሊኖር እንደሚችል ወይም በራሱ ምክንያት መልስ ሊሰጥህ እንዳልፈለገ ይግባህ፡፡ 2. የተበደርከውን ገንዘብ አበዳሪህ ከመጠየቁ በፊት መልስ፡፡ ምን ያህል ለቃልህ ታማኝና ሃላፊነት የሚሰማህ ሰው እንደሆንክ ማረጋገጫው እሱ ነው፡፡በአንጻሩ የተበደርከውን ጃንጥላም ቢሆን እስክሪፕቶ ሳትጠየቅ መመለስ ቁምነገረኝነትህን ያሳያል፡፡ 3. ማንም ሰው ሊጋብዝህ ወደሆቴል ቢወስድህ ከሜኑው ውስጥ ውድ ዋጋ የሚያወጣውን ምግብ አትዘዝ፡፡ሰዎች ምን ደግ ቢሆኑ ይሉኝታ የሌለው ሰውን መታዘባቸው እንደማይቀር አትርሳ፡፡ 4. ማንንም ሰው “ለምን እስካሁን አላገባህም/ሽም?" አይነት የግል ጥያቄዎችን አትጠይቅ። ወይም "ለምን ልጅ አልወለድክም/ሽም " አትበል፡፡ ይህ የነርሱ እንጂ ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት ጥያቄ ሰዎችን ያሳቅቃል፡፡ 5. በር ከፍተህ ስትገባ ከኋላህ ወንድም ሆነ ሴት፣ ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰው ቢኖር በሩ በላያቸው እንዳይዘጋ ያዝላቸው፡፡ ለሰዎች ትህትና ማሳየት አንተን ያስከብርህ ይሆናል እንጂ ትንሽ አያደርግህም፡፡ 6. ከጓደኛህ ጋር ታክሲ ተሳፍረህ ስትሄድ እሱ ከከፈለ ሌላ ቀን ደግሞ ራስህ ክፈል፡፡ ፈቅዶ ካልሆነ በቀር በይሉኝታ ማንም ሰው ያንተን ወጪ የመካፈል ግዴታ የለበትም፡፡ 7. ሁሌም እኔ ብቻ ልክ ነኝ አትበል፡፡ ላንተ 6 ቁጥር የሚመስለው ለሌላው ሰው 9 ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡ ትክክልነት ካለህበት አንጻር የሚታይ አንጻራዊነት ነው፡፡ ካንተ የተለየ አስተያየት ማግኘት ይጠቅምሃል እንጂ አይጎዳህም፡፡ 8. ሰው ሲናገር እስኪጨርስ ጠብቅ እንጂ አታቋርጥ፡፡ አንድ ሰው ለማለት የሚፈልገውን ሳይጨርስ አስተያየት መስጠት ወደስህተት ሊመራህ ይችላል፡፡ 9. በሰዎች ላይ በቀልድ አታሹፍ፡፡ በተለይ ሹፈቱን ካልወደዱት ወዲያውኑ አቁም፡፡ እንዲህ ያለውን ነገር አለመድገም ለሰዎች ስሜት ምን ያህል እንደምትጠነቀቅ ማሳያ ነው፡፡ 10. ሁሌም ሰዎች በጥያቄህ መሰረት ከረዱህ በኋላ “አመሰግናለሁ” ማለት ይልመድብህ፡፡ 11. ሰዎችን በአደባባይ አመስግን፡፡ የሚታረም ነገር ካላቸውም ቀስ ብለህ በግላቸው ንገራቸው እንጂ በሰው ፊት አታሳጣቸው፡፡ ለመሻሻል የሚጠቅማቸው ይህንን ማድረግህ ነው፡፡ 12. ማንንም ሰው ክብደቱን በተመለከተ አስተያየት አትስጥ፡፡ ምናልባት ጥሩ ለብሶ/ሳ ካየህ “ዛሬ ዘንጠሃል ወይም በጣም ታምሪያለሽ” ብቻ በል፡፡ሰዎች ስለውፍረታቸውና ስለቅጥነታቸው ከፈለጉ ራሳቸው ይናገሩ እንጂ ያንተ አስተያየት ሊያበሳጫቸው ይችላል፡፡ 13. ሰዎች በስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ሲሰጡህ ያሳዩህን ብቻ አይተህ መልስ፡፡ ሳይፈቀድልህ ወደቀጣዩ ፎቶ አትሂድ፡፡ በድንገት የግል እና ማንም እንዲያየው የማይፈልጉትን ፎቶ አይተህ ቅር ልታሰኛቸው ትችላለህ፡፡ 14. አንድ የሥራ ባልደረባህ ሃኪም ጋር ቀጠሮ አለኝ ካለህ “ምንህን አሞህ ነው?” ብለህ አትጠይቅ፡፡ "ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ" ብቻ በል፡፡ የሰዎችን ግላዊነት አክብር፡፡ 15. በመስሪያ ቤትህ ስራ አስፈጻሚም ይሁን ጽዳት ሰራተኛ ሁሉንም ሰው በአክብሮት ጥራ፡፡ ብዙዎች “ለሁሉ ትሁት ነው” የሚሉትን ሰው አብልጠው እንደሚወዱና እንደሚያቀርቡ እወቅ፡፡ 16. ከሰው ጋር እያወራህ ሳለ በፍጹም ስልክህን አትመልከት፡፡ ይህ ለሰውየው ያለህን ንቀት ማሳያ ነውና ይቀየምሃል፡፡ 17. ለሰው ምክር መስጠት ያለብህ ከጠየቀህ ወይም ከፈለገ ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አብዝቶ የሚመክራቸውን ሰው አይወዱም፡፡ ያነሱ መስሎ ሊሰማቸውም ይችላል፡፡ 18. የሰውን እድሜና ደመወዝ አትጠይቅ፡፡ ራሱ ማውራት ካልፈለገ በቀር ሰው መናገር ከማይፈልጋቸው ነገሮች ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው፡፡ 19. አንተን በቀጥታ የሚመለከትህ ካልሆነ በቀር በሌላ ሰው ጉዳይ በተለይ በባለትዳርና በፍቅረኞች ጉዳይ ጣልቃ አትግባ፡፡ 20. የዝነጣ መነጽር አድርገህ መንገድ ላይ እየሄድክ የምታውቀውን ሰው ስታገኝ መነጽርህን አውልቀህ አነጋግረው፡፡ ከሰዎች ጋር ስታወራ የአይን ግንኙነት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህንን ማድረግህ ለዚያ ሰው ያለህን አክብሮት ያሳያል፡፡ 21. ጊዜ ፊቱን ካዞረባቸው ሰዎች ጋር ስትሆን ስለ ሀብትህ አታውራ፡፡ በዚህም አትኩራራ፡፡ በተለይም ልጅ መውለድ ባልቻሉ ሰዎች መካከል ስለልጆችህ አጥብቀህ ከማውራት ተቆጠብ፡፡ 22. ማንኛውንም መልካም መልዕክት ከተቀበልህ በኋላ “ለመልእክቱ አመሰግናለሁ” በል፡፡ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏 @Aderaw @Adony444 #History #Ethiopia

የታሪክ ማህደር
የታሪክ ማህደር
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 10 October 2026 03:26:20 GMT
730
43
0
8

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @yetariekimahideri, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About