@paulwon21: ✍️ከኢየሩሳሌም በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ በኢያሪኮ ደሴት የሚኖርና እመቤታችንን እጅግ የሚወድ ስሙ አስቴራስ የሚባል አንድ ዲያቆን ነበረ፡፡ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ማርያም ሆይ አምላክን በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽና፤ ደስ ይበልሽ! እያለ ቅዱስ ገብርኤል ያበሠራትን (ያቀረበላትን) ሰላምታ፣ (ምስጋና) ሉቃ.1÷26-29 ሳያቋርጥ ዘወትር ይጸልይ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ዲያቆን ለተግባሩ ወደሩቅ አገር ሲሄድ፣ ርኅራኄ የሌላቸው ሰዎች በመንገድ አገኙትና በጭካኔ ገድለዉ ሳይቀብሩት ሄዱ፣ነገር ግን ሌሎች ሰዎች በመንገድ ሲያልፉ አስከሬኑን አይተዉ፣ በመንገዱ ጥግ መቃብር ቆፍረዉ ቀብረዉት ሄዱ፡፡ ከተቀበረ ከ3 ቀን በኋላም፣ እመቤታችን ክፉ ስዎች ባሉባት በዚያች አገር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ለሚያገለግል ለአንድ ዲያቆን በራእይተገልጻ፤ "ወዳጄ ሆይ"ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት የሚያገለግልና በእኔና በልጄ ዘንድ፣ ጸሎቱ የተወደደችለት ዲያቆንን ስለገደሉት አዝኛለሁ፣ ጓደኞችህ ዲያቆናትን ይዘህ በመንገድ ጥግ ወደ ተቀበረው ዲያቆን ሂዱና መቃብሩን ቆፎራችሁ አውጥታችሁ፤ በቤተ-ክርስቲያን ቅበሩት አለችው፤ ዲያቆኑም እመቤታችን እንደነገረችው መቃብሩን ቆፍረዉ፤ አስከሬኑን ባወጡ ጊዜ ርሔ እንደሚባል ሽቱ መዓዛው እጅግ ደስ : የሚያሰኝ ከአፉ የበቀለ አንድ የጽጌረዳ አበባን አገኙ፡፡ ይህንን ሲያይ ሊቁ እንዲህ አለ ! ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምዓጽሙ ፤ ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ ፤ ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ ፤ ለተአምርኪ አሐሊ እሙ ፤ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡ ገብርኤል ሰላምታ ቃል ጋር ባመሰገነሽ ሰው፤ የክርስቶስ እናቱ ማርያም ሆይ መልአኩ ገብርኤል አበባን ይዞ ደስ ይበልሽ እያለ ከአቀረበልሽ ሰላምታ ጋር፣ ሉቃ.1+26-311 እጅ ከነሳሽ ሰው ዐፅም፣ የጽጌረዳ አበባ በቅሎ ታየ፤ ስለዚህም የተአምርሽ የጣዕሙ ዜና ባስደሰተኝ ጊዜ፤ ስሙ የአበባ ማኅሌት ለሚባል ተአምርሽ እዘምራለሁ፡፡#orthodox #ማህሌተ_ፅጌ
ጳውሎስ
Region: ET
Saturday 10 October 2026 06:51:35 GMT
Music
Download
Comments
Fira :
🙏🙏🙏
2026-10-10 08:28:48
0
ዳኒ_lyrics :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-10 07:31:31
0
TheCodecraft💻 :
🥰
2026-10-10 14:25:55
0
To see more videos from user @paulwon21, please go to the Tikwm
homepage.