@melakufekadu1: ህጋዊ እና ህገ ወጥ ይዞታ እንዴት ይለያል? ********** 1. በቅድሚያ ገዢው ይዞታውን ከመግዛቱ በፊት ማረጋገጥ ያለበት የሚገዛው ይዞታ በከተማ አስተዳደር ውስጥ መጠቃለሉን ነው ምክንያቱም በከተማ አስተዳደር ውስጥ ያልተጠቃለለ ይዞታ ከሆነ ካርታና ፕላን ለማግኘት አዳጋች ይሆናል። 2. ሻጭ የሚያቀርበው ካርታና ፕላን በከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት ውስጥ ስለመኖሩ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በዚሁ ካርታና ፕላን የማን ስም እንዳለ? ባለመብቱ ማን እንደሆነ? ማገናዘብ ያስፈልጋል ምክንያቱም ተመሳስሎ በተሰራ ካርታፕላን የይዞታ ትክክለኛ ሻጭ ያልሆኑ ሰዎች የሌሎችን ይዞታ አሳስተው ሊሸጡ ስለሚችሉ ቅድሚያ ተገቢውን ማጣራት ከማዘጋጃ በማድረግ መግዛት ጠቃሚ ነው። አንድ ይዞታ ተመሳስሎ በተሰራ ካርታናፕላን ለብዙ ሰዋች የሚሸጥበት ሁኔታ ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከተ በመምጣቱ ተጠንቅቆ መግዛት የግድ ይላል። 3. በይዞታው ላይ ለሌሎች ሰዋች መብት ያላቸው ስለመሆኑ በቅድሚያ ማጣራት ያስፈልጋል ሻጩ ባለትዳር ስለመሆኑ? ይዞታው በዕዳ አለመያዙን? ከፍርድ ቤት እገዳ ነፃ ስለመሆኑ? ሌሎች ሶስተኛ ወገኖች በይዞታው ላይ ጥያቄ እንደማያነሱ?በማረጋገጥ መግዛት ሕጋዊ እና ዋስትና ያለው ግዢ እንድንፈጽምና ወደፊት የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር ይረዳል። ሻጭ ያለውን የትዳር ሁኔታ ለማወቅ ያላገባ የሚል ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ገዢው ለመጠየቅ ይችላል። የፍርድ ቤት እግድ ነፃ መሆኑን ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ በአቅራቢያ ከሚገኘው ማዘጋጃ ጽ/ቤት በመሄድ ማረጋገጥ ይቻላል። 4. የሚሸጠውን ይዞታ በቀጥታ ቦታው ድረስ ሄዶ በማየት መግዛት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ባዶ መሬት አጥረው የሚሸጡ ስላሉ ባዶ መሬት ደግሞ የህዝብናየመንግስት ነው አይሸጥም አይለወጥም ስለዚህ ይዞታ ላይ ቤት የተሰራበት መሆኑን በቅድሚያ በማየት መግዛት ያስፈልጋል። 5. የሽያጭ ውሉ የሕጉን ፎርማሊቲ ያሟላ መሆኑን በሕግ ባለሙያ በቅድሚያ በማረጋገጥ መዋዋል ያስፈልጋል ምክንያቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት በተመለከት የሚደረጉ ውሎች በፅሁፍ እና ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠው አካል ፊት ቀርበው መፅደቅ አለባቸው። በሕጉ አግባብ ያልተዘጋጀ የሽያጭ ውልና በመንደር ውል የተፈፀመ ስምምነት በሕግ ግፊት ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ እነዚህንና መሠል ቅድሚያ ማጣሪያ ሂደቶችን በማገናዘብ መስማማት ሕጋዊ ይዞታን ለማግኘት አስፈላጊ ግብዓት ነው። Telegram 👇 https://t.me/melakufek facebook 👇 https://www.facebook.com/share/

መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 10 October 2026 10:15:36 GMT
2333
80
5
4

Music

Download

Comments

wondimu.seifu0
Wondimu Seifu :
What is the duty of DARA 922/2008 and civil code 1723:1195-1198:1204-1206 Do you think DARA will authonticate : Registered : transferred ownership if anybody as per his knowledge proof that legality is valid ?
2026-10-10 18:08:59
0
user7414224371532y
Omer Hussen :
l am accept you
2026-10-10 15:14:19
1
addis8049
Addis :
🔔🔔🔔በጣም ገላጭ እና አስረጂ መረጃ ነው ያስቀመጥከው! ከልብ አመሰግናለሁ🫶🙏🙏🙏 በርታልን🙏🙏🙏
2026-10-11 12:40:21
0
user9684240825623
ሁን እንጅ አትመሠል ☝️ :
ቢብራራ👍👍👍
2026-10-10 16:30:41
0
user7703571859933
fenan :
ጽሁፉ በጥቁር ቢፃፍ ወይ ባክግራውንዱ ቢጠቁር ማንበብ ይቻል ነበር
2026-10-11 09:31:51
0
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About