@gigi_shebabawfan2: የታላቁ ባለቅኔ «አያ ሙሌ» እውነተኛ ገጽታ _ ጋዜጠኝነት ሀቀኝነትን፣ ጥልቅ ምርምርንና ገለልተኛነትን የሚጠይቅ የተከበረ ሙያ ነው። አንድ ባለሙያ ጋዜጠኛ መረጃን ሳይመረምርና ሳይያዝ ከማሰራጨት ይልቅ እውነታውን ከወሬ ለይቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በቅርቡ በአንድ ቃለ-መጠይቅ ጋዜጠኛው ከአርቲስት ፀደንያ ጋር በነበረው ቆይታ «እኔ እንግዲህ የሰማሁትን ነው... አሉ እንግዲህ» እያለ ስለ ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) ያነሳው አባባል የጋዜጠኝነትን ስነ-ምግባር ያጎደለና ፍጹም ያልተጣራ አሉባልታ ነው። ሰሞኑን ያየሁት ሸገር ራዲዬ ሸገር መዝናኛ የተሰኘው ፕሮገላይ ላይ ወንድሙ ሀይሉ የተባለ ጋዜጠኛ ተብየ ከአርቲስት ፀደንያ ጋር በነበረው ቆይታ «እኔ እንግዲህ የሰማሁትን ነው... አሉ ነው» በሚል ሰበብ ስለ ታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) የተናገረው የዚህን ታላቅ ሙያ ድንበር የጣሰና ያልተጣራ አሉባልታ ነው። ጋዜጠኛው «ኪሴ ባዶ ሆኖ እናንተ በእኔ ግጥም ትጨፍራላችሁ ብሎ ድንጋይ ወረወረ» የሚል የቡና ላይ ወሬ እንደ እውነተኛ መረጃ ከማቅረቡ በፊት፣ ስለ አያ ሙሌ ስብዕና ጥቂት ቢመረምር(Fact-checking) ኖሮ እውነታው ከዚህ እጅግ የራቀ መሆኑን በተረዳ ነበር። ✓ ግን አያ ሙሌ ማን ነበር? (የምስክሮችና የሥራዎቹ እውነት) ፩. የተወደደ ስብዕና እና የመናኝነት ህይወት: ልጁ ሄዋን ሙሉጌታ «አባቴን ለምን መዘንጡን ተውክ ስለው፤ እስከዛሬ ስጋዬ ውስጥ ነበርኩ፤ አሁን ግን ዓለማዊ ህይወት በቃኝ ብሎኛል» በማለት እንደተናገረችው፣ አያ ሙሌ ለሥጋዊ ፍላጎት መኖርን ትቶ «የከተማው መናኝ» ለመሆን የበቃ ሰው ነው። ፪. ለጥበብና ለሰው ያለው ቅንነት: አያሙሌ በአደባባይ «ግጥሞቼን ማንም ሰው በባለቤትነት ሊወስዳቸው ይችላል፤ መፈለጋቸው ብቻ ለእኔ ይበቃኛል» በማለት ልፋቱንና ጥበቡን ለሌሎች በነፃ የሚቸር እንጂ «ኪሴ ባዶ ሆነ» ብሎ ድንጋይ የሚወረውር ስብዕና አልነበረውም። ፫. «እንዴት እኔ እያለሁ የራስ ጡት ይደርቃል» እኔማ ሰገል ነኝ የሚያዝያ ወገል ነኝ ደህና ሰንበት ማጣት ከአንተ ሚገላገል.. እናት የሰፋችው የአገርልጅ አገልግል ቲምም ብሎ ሞልቶ. . . ላይል ፈንገል ፈንገል ምንም የለኝ የግል እንዴት እኔ እያለሁ የራስ ጡት ይደርቃል እንዴት የጋሜ ሆድ ከአንጀቱ ይደርቃል . . . በ1977 ዓ.ም ድርቅ ወቅት ከተፈናቀሉ ወገኖች ጋር አብሮ በመቆም ኪሱ ውስጥ የነበረውን ሰጥቶ «እንዴት እኔ እያለሁ የራስ ጡት ይደርቃል?» ሲል የተቀኘ ሰብአዊ ሕሊና ያለው ገጣሚ ነው። የሙያ አጋሮቹ ስለ እሱ የተናገሩት አርቲስት አበበ ተካ፡ «ሙሉጌታ ለሃብት፣ ለክብርና ለዝና አይጨነቅም። ውሎው ከእሱ በታች ካሉት ጋር የመዋል ልምድ ያለው ትሁት ሰው ነው።» ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፡ «ሙሉጌታ ራሱን የተወና ከራሱ ይልቅ ሰዎችን የሚያስቀድም (Selfless) ነበር።» ገጣሚ ዮሐንስ ገብረመድህን፡ «ስሙ ሳይፃፍ ብዙ ግጥሞችን የሰጠ ሰው ነው። ነገር ግን አሻራው በሁለት ስንኝ ማንበብ ብቻ ይታወቃል።» የዜማ ደራሲ አበበ ብርሃኔ፡ «ሙሉጌታ ደግ ከመሆኑ የተነሳ ግጥሞቹን ለብዙዎች በነፃ የሰጠ ታላቅ ሰው ነው።» «ሙሉጌታ ሰወች በግጥሜ ለምን ተደሰቱ ብሎ ድንጋይ የሚወረውር አልነበረም ባይኖረው እንኳ ለምኖ መስጠትን በግጥሞቹ እንዲህ ሲል . . .የእነ ሀርቡ ጌታ በፍቅር አስግሮ ጦሙን ያድራል እሱ ለሰው ተበድሮ . . . ገልፆታል። ✓ ለዚህም ነበር አያ ሙሌ «ቅዱስም ንጉሥም ነኝ» እያለ የሚናገረው። ራሱን መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ያለን ታላቅ ባለቅኔ ባልተረጋገጠ አሉባልታ ስሙን ማደፍረስ ከአንድ ጋዜጠኛ ፈጽሞ የማይጠበቅ ተግባር ነው። እዚህ ላይ ምሰጋናየ ለፀደንያ ገ/ማርቆሰ ይህን የ”አሉ “ወሬ ሲያወራ አላውቅም ውሸት ምን ያደርጋል ብላ ኩም ላደረገችው❤️ ✍️ኪዲ የጂጂ #አያሙሌ #ወሎ #gigi_shebabawfan2 #gigishebabaw #ethiopiamusic

gigi_shebabaw fans
gigi_shebabaw fans
Open In TikTok:
Region: SA
Sunday 11 October 2026 20:58:02 GMT
11461
416
15
28

Music

Download

Comments

yaredinatube
𝐘𝐚𝐫𝐞𝐝𝐢𝐧𝐚 :
😢😢😢ለአረጋሀኝ ከእድሜዬ ሁለት ዓመት ቆርጠህ ስጠው ብሎ አምላኩን የለመነ ሰው ነውኮ እንኳን በግጥም ሰው ሊናገር 😔 "አያዋ💔"
2026-10-11 21:46:42
7
mengedegaw_12
መንገደኛዉ :
በነገራችን ላይ የተወራ ጥያቄ ነዉ የጠየቃት! መፅሀፉም ላይ የሰፈረ ይመስለኛል ረሳሁት እንጅ! ብዙም አትከፉ እንደኔ ሙሌን የምትወዱ ሁሉ።
2026-10-12 14:43:10
1
driller0101
Drill🤨 :
ስድብ እንዳልፅፍ የባለቅኔው ነገር ላይ ሆነ😬መቸ ታሪኩን አንብቦትና ተረድትቶት ነው? የ50,000 ብሯን ታሪክ ሹክ ብትየው እንዲህ ባልተለፋደደ! ያች መንገድ ላይ ራበኝ ስትለው ያደረገውን ታሪክ ብትጠቅሽለት ይሄ ጋፈተኛ(ቃዘተኛ) ይሄን ጥቁር ልብሱን አንጥፎ አያ ሙሌ ይመጣል ብሎ መንገድ መንገዱን ያይ ነበር! ይሄ ሰካራም....😫
2026-10-11 21:13:52
4
elizabethtilahun6
ቅ.ድ.ስ.ት 🎀 :
በስመአብ ባውቃቸው ብዬ ከምመኛቸው ሰዎች መሀል ነው 🥹አያሙሌ ማለትኮ ደሞዝ ተቀብሎ እንኳን ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር በመዝናናት የሚጨርስ ሰው ነው እንኳን እንዲህ ባለ ነገር ስሙ ሊነሳ ፣ አያ ሙሌ የከተማው መናኝ አደል የሚባለውስ 😊
2026-10-14 11:11:55
3
jahmc1
Jah Mc :
ብዕርሽ አይንጠፍ 🙏🏻🔥🔥
2026-10-11 21:06:59
4
abebeyadechu
AB በቸርነቱ :
እፍይ ሙዚቃ ተከፈተ እናመሰግናለን 🎵🎶🎵
2026-10-12 15:13:43
0
user3396184837805
ጠበቃና የህግ አማካሪ መንግስቱ ዘገየ :
yes
2026-10-19 00:38:28
0
aguye11
ወገደ :
«ከአንተ ሚገላገል» ሳይኾን ካንተ 'ሚገላ[ግ]ል «ላይል ፈንገል ፈንገል» ሳይኾን «ላይል ፍን[ግ]ል ፍን[ግ]ል» ....(🙏)
2026-10-14 15:07:23
0
samfekadu
Samuel :
🙏🙏🙏
2026-10-14 07:19:19
0
m5051286
hard work :
🥰🥰🥰
2026-10-12 14:09:35
0
gash_basha
jo ta :
🥰
2026-10-12 08:03:56
0
2taglife
Tag_life :
👏
2026-10-12 02:50:16
0
rozaaa1921
Rozina 🎀 :
[Twin hearts][Twin hearts]
2026-10-14 10:55:40
0
To see more videos from user @gigi_shebabawfan2, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About