@antonioethio: “ልጄ ሆይ፣ ጠንካራ ሰው ሁን!” (1ኛ ነገሥት 2፥3) 🌱 ሰው ከመሆናችን በፊት ዶክተር አልነበርንም፤ መሐንዲስ አልነበርንም፤ መምህር አልነበርንም፤ የሕግ አስከባሪ አልነበርንም፤ ፖለቲከኛ አልነበርንም፤ ጋዜጠኛም አልነበርንም። ሰው ከመሆናችን በፊት መሪ አልነበርንም፤ አማካሪም አልነበርንም! 🌱 አዎ! ከሁሉም በፊት ሰው እንሁን! ሰው ከመሆናችን በፊት ተናጋሪ አንሁን፤ ዘፋኝ አንሁን፤ ጸሐፊ አንሁን፤ ሰባኪ አንሁን፤ ባለሥልጣን አንሁን፤ አማካሪ አንሁን፤ እናትና አባት ከመሆናችን በፊት፣ ባልና ሚስት ከመሆናችን በፊትም ሰው መሆንን እንማር! 🌱 ከሁሉም በፊት ሰው መሆን ነው! ዓለማችን ዛሬ የምታጣው ባለሙያ ብቻ አይደለም፤ ከሁሉም በላይ የምታጣው እውነተኛ ሰው ነው። 🌱 ከሁሉም በፊት ሰው እንሁን! ሰው መሆን ከማንኛውም ማንነት በላይ የተከበረ ማንነት ነው። ፈጣሪያችን ከፍጥረታቱ ሁሉ የተለየ ክብር ሰጥቶን፣ በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮናል፤ እኛ ግን የተሰጠንን ዋጋና ክብር እንዘነጋለን። ሰው እንደ ሰው ማሰብንና ሰብዓዊነትን በተግባር ማሳየትን ካልቻለ፣ እውነተኛ ሰው መሆንን አልተረዳም ማለት ነው። «ሰብዓዊነት የሌለው ማንኛውም ሙያ፣ ጣፋጭ ምግብን በመርዝ በተሞላ ዕቃ ውስጥ እንደመመገብ ነው!» 🌱 የችግሮቻችን ሁሉ መነሻ ሰብዓዊነት የጎደላቸው ድርጊቶቻችን ናቸው። 🤌🏾 ይህ መልዕክት ለሁላችንም ትምህርት ይሁን! 🫶🏽 🙏 እግዚአብሔር በፍቅር የተሞላ ልብ፣ ማስተዋል፣ ጥበብና እውቀት ይስጠን። አሜን! #creatorsearchinsights #ፍቅር➻ብቻ🖇ፍቅር➻ብቻ❤🥀🔐 #ethiocanada🇪🇹🇨🇦 #torontohabesha

Antonio Ethio
Antonio Ethio
Open In TikTok:
Region: CA
Monday 12 October 2026 16:06:27 GMT
494
79
4
2

Music

Download

Comments

nibeyt
Mercy :
🙏🙏🙏
2026-10-12 16:47:30
1
batee.batee6
የጎንደሯ ቀበጥ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-12 17:04:58
1
jerfikir
ሀሴት ❤️ :
👌👌👌👌👌
2026-10-12 16:26:19
0
kidu.kassahun3
It’s Me…. :
🥰
2026-10-12 21:39:42
0
To see more videos from user @antonioethio, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About