@ayxzxfxk: #abcxyz #fyppppppppppppppppppppppp

★Ay☆me★
★Ay☆me★
Open In TikTok:
Region: US
Tuesday 13 October 2026 00:24:39 GMT
305
22
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @ayxzxfxk, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አቤቱ የማይመረመር ግርማ፣ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪና የዘመናት ጌታ የሆንክ ታላቁ አምላክ ሆይ፤ ሰማየ ሰማያት የማይበቁህ፣ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ በክንድህ ውስጥ የሆኑ፣ በብርሃን የምትኖርና መቅረብ በማይቻል ክብር የተከበብክ አምላክ ነህ። ዙፋንህ ከዘላለም የጸና፣ ስልጣንህም በፍጥረት ሁሉ ላይ የሆነውን አንተን በማድነቅና በመንቀጥቀጥ በፊትህ እንሰግዳለን።አባታችን ሆይ፤ አንተ ይህን ያህል ታላቅ ሆነህ ሳለ፣ እኛ ግን ከትቢያ የተገኘን፣ እንደ ሣር የምንጠወልግ፣ እጅግ ደካማና ጎስቋላ ፍጥረታት ነን። ኃጢአታችንንና አቅመ ቢስነታችንን ስናስብ፣ በፊትህ መቆም አይገባንም። ነገር ግን የሰውን ልጅ ውድቀትና ደካማነት ሊያቋርጠው የማይችለው ያ ታላቁ በመስቀል ላይ የታየው የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር ወደ አንተ አቀረበን። ለሰው ልጅ ያለህ የዘላለም አጀንዳና የሰላም ሀሳብ ከድካማችን በለጠ። ውድቅና የተጣልን ስንሆን በልጅህ በኢየሱስ ደም ታጥበን፣ የከበረውን የልጅነት ስፍራ አግኝተን ይሄው ዛሬም በጸጋህ ዙፋን ፊት ቆመናል።​ጌታ ሆይ፤ ዛሬ በዚህ ቀን በአራቱም የዓለም ማዕዘናት በሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ስለሚነገረው ህያው ቃልህ እንጸልያለን። የሚዘራው ቃል በሰሚዎች ልብ ውስጥ ስር ሰዶ ሰላሳ፣ ስልሳና መቶ እጥፍ መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈራ መንፈስ ቅዱስህ ይስራ። ቃልህ የተሰበረውን ይጠግን፣ የታወረውን ያብራ፣ የሞተውንም መንፈስ ህያው ያድርግ፤ የሰዎችን ልብ እንደ ሰም አቅልጦ ወደ እውነትህ ይመልስ። ​አምላካችን ሆይ፤ በዚህ ሰዓት በህመም አልጋ ላይ ሆነው ለሚሰቃዩትና ፈውስ ለሚፈልጉት ወገኖቻችን ሁሉ የፈውስ እጅህን እንድትዘረጋላቸው እንማጸናለን። በእስር ቤት፣ በጨለማ፣ በጭንቀትና በሱስ እስራት ውስጥ ላሉት የመንፈስና የስጋ ነጻነትን አውጅላቸው። ቃልህ ሲነገር፣ ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ያለው ትውልድ ሁሉ ልቡ በእውነት ብርሃን ይለወጥ። ትውልዱ ሁሉ ክርስቶስን ወደመምሰል እንዲያድግና የጽድቅ መሳሪያ እንዲሆን በመንፈስህ አድሰው።ይህንን የልመና፣ የምስጋናና የምልጃ ጩኸታችንን ሰምተህ፣ እንደ በጎ ፈቃድህና እንደ ቸርነትህ ብዛት ስለምትመልስልን እናመሰግንሃለን። ይህንን ጸሎት፣ አዳኛችን፣ ታዳጊያችንና የህይወታችን ራስ በሆነው፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ህያውና ቅዱስ ስም አቀረብን፤ አሜን!!

About