@cortesreals: @augustoeruanvictor #augustoeruanvictorcy

Cortes real
Cortes real
Open In TikTok:
Region: BR
Tuesday 13 October 2026 03:19:20 GMT
0
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @cortesreals, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

መስታወት አራጋው ለጥበብ የተፈጠረች ድንቅ አርቲስት!   ከጨርቆስ ሰፈር አውራ ጎዳናዎች ተነስታ የብዙዎቻችንን ቤት በቅንነትና በጥበብ ያሞቀች ድንቅ የጥበብ ሰው ናት። በአብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያ የጀመረው ያ የልጅነት የጥበብ ፍቅር፣ ዛሬ ድረስ በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ጥሎ አልፏል።  የንግግር ቅላፄዋ ብቻ ሳይሆን ለቅሶዋም ተወዳጅ ነው! በኢትዮጵያ የድራማ ታሪክ ከዚህ በፊትም ሆነ ምናልባትም እስከሚቀጥሉት 50ና ከዛም በላይ አመታት ያልተሰራና ሊሰራ የማይችል ድራማ በኢትዮጵያ ራድዮ ለአንድ አመት ተላልፎ ነበር። ============
መስታወት አራጋው ለጥበብ የተፈጠረች ድንቅ አርቲስት! ከጨርቆስ ሰፈር አውራ ጎዳናዎች ተነስታ የብዙዎቻችንን ቤት በቅንነትና በጥበብ ያሞቀች ድንቅ የጥበብ ሰው ናት። በአብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያ የጀመረው ያ የልጅነት የጥበብ ፍቅር፣ ዛሬ ድረስ በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ጥሎ አልፏል። የንግግር ቅላፄዋ ብቻ ሳይሆን ለቅሶዋም ተወዳጅ ነው! በኢትዮጵያ የድራማ ታሪክ ከዚህ በፊትም ሆነ ምናልባትም እስከሚቀጥሉት 50ና ከዛም በላይ አመታት ያልተሰራና ሊሰራ የማይችል ድራማ በኢትዮጵያ ራድዮ ለአንድ አመት ተላልፎ ነበር። ============ "የማእበል ዋናተኞች" ድራማ የሀይሉ ፀጋዬ ድርሰት በሆነው ድራማ ላይ ይህቺ ድንቅ አርቲስት "እፁብ" በተባለች ገፀ ባህርይ ተውናለች። ያ ምትክ የለሽ ድራማ የማይረሳ ከመሆኑ ባሻገር ድራማው ባለቀ ማግስት ጎሳዬ ተስፋዬ "እፁብ ልጅ ነሽ አንቺ" ብሎ ድንቅ ዘፈን ለቋል። በተጨማሪም "መታ መንገድ" የተስኘው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ይጠቀሳል። ከታዋቂው አርቲስት ተመስገን አፈወርቅ ጋር በትዳር ተሳስረው 2 ልጆች አፍርተው በሜሪላንድ ይኖራሉ። ======== የሙዚቃ ሰዋስው በሆነው ያሬድ ትምህርት ቤት በቫዮሊን ተጫዋችነት ስትመረቅ፤ ያንን ክቡር መሣሪያ በጣቶቿ ዳስሳ እንደ "ባቲ" እና "አምባሰል" ያሉ የዘለቄታ ዜማዎችን ስታንቆረቁር የሰማት ሁሉ ጥበቧን ያደንቃል።ያ ብቻ ግን አይደለም፤ በመስታወት ድምፅ "እፉኝት"ን፣ "ሲጨልም"ን፣ "ፍርሃት"ን የሰማን ሁላችን በትረካዎቿ ተማርከናል። በተለይ ደግሞ የገዛ ሰፈሯን ትዝታና ፍቅር የከፈለችበት "አቦቸር የጨርቆሱ ልጅ" ትረካዋ ለእድገትዋና ለሰፈርዋ ያላትን ጥልቅ ፍቅር በጉልህ ያሳየ ልዩ ስራዋ ነው። በአሜሪካ ሆና በሰራችበት "ሰንሰለት" ድራማም በትወና ብቃትዋ ሁላችንንም አስደምማለች። የትም ብትሄድ የጨርቆስ ልጅነቷን በኩራት የምትናገረው፣ በድምፅዋ፣ በቫዮሊንዋና በትወናዋ የኢትዮጵያን የጥበብ ታሪክ ያደመቀችው መስታወት አራጋው ሁሌም ትልቅ ክብር ይገባታል። "የማዕበል ዋናተኞች" ድራማ ላይ የነበራትን ድንቅ የድምፅ ትወና የምታስታውሱ ምን ትዝታ አላችሁ?

About