@ethiopian.electri: ⚡️የከስተመር ኢንተርፌስ (CIU) ኮዶች እና አጠቃቀም‼️ ውድ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎን (CIU - Customer Interface Unit) በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን በቀላሉ ለማወቅ የሚረዱ ኮዶችና አጠቃቀማቸው፣ 1️⃣ ቀሪ ሂሳብ እና የ KWH መጠን ለማወቅ 👉 የሚጫነው ኮድ: 170 በመቀጠል ሰማያዊውን በተን (Enter) ይጫኑ። ➡️ ጠቀሜታው: ቀሪ ሂሳብዎ ወይም ምን ያክል የ KWH መጠን እንዳለዎት ለማወቅ ያስችላል። 2️⃣ አሁን ላይ እየተጠቀሙበት ያለውን የኤሌክትሪክ መጠን ለማወቅ 👉 የሚጫነው ኮድ: 034 ➡️ ጠቀሜታው: በቤትዎ ውስጥ ምጣድ፣ ስቶቭ ወይም የተለያዩ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን ሲጠቀሙ አሁን ላይ እየተጠቀሙበት ያለውን የኤሌክትሪክ መጠን ማወቅ ይችላሉ። 3️⃣ ቆጣሪው ከተገጠመ ጀምሮ ያለውን ጠቅላላ ፍጆታ ለማወቅ 👉የሚጫነው ኮድ: 000 ➡️ጠቀሜታው: እስከ ዛሬ ድረስ ቆጣሪዎ ከተገጠመ ጀምሮ የተጠቀሙትን ጠቅላላ የፍጆታ መጠን ያሳየዎታል። 4️⃣ የሞሉበትን ጊዜ ብዛት ለማወቅ 👉 የሚጫነው ኮድ: 500 ➡️ጠቀሜታው: በተለያዩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች እስከ አሁን ድረስ ምን ያክል ጊዜ ካርድ እንደሞሉ ማወቅ ይችላሉ። 5️⃣ ለመጨረሻ ጊዜ የሞሉትን ሂሳብ ለማወቅ 👉 የሚጫነው ኮድ: 501 ➡️ ጠቀሜታው: ለመጨረሻ ጊዜ የሞሉትን የሂሳብ መጠን ወይም የ KWH መጠን ያሳየዎታል። 6️⃣ የቆጣሪዎን የኃይል መጠን (Capacity) ለማወቅ 👉 የሚጫነው ኮድ: 200 በመቀጠል ኢንተር (Enter) ይጫኑ። ➡️ ጠቀሜታው:- ለቆጣሪዎ የተፈቀደውን ከፍተኛ የኃይል መጠን ያሳያል (ለነጠላ ፌዝ እስከ 7.5 ኪ.ወ የሚፈቀድ ሲሆን፤ለምሳሌ 5 ካለ ለቆጣሪው የተፈቀደው 5 ኪሎ ዋት ነው ማለት ነው)። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Ethiopian Electric Utility
Region: ET
Tuesday 13 October 2026 06:57:31 GMT
Music
Download
Comments
Amir mohammed :
Based on people's comments, my trust has faded.
2026-10-13 09:45:52
0
Amanu Hospital :
1000ብር አለው ግን ትንሽ በርቶ ይጠፋል እና ደጋሜ እናበራዋለን በሬከሩ ግን አይመልስም
2026-10-13 22:51:58
0
mame 🤳 :
አረ ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ መጋዶ ማብራት ከጠፋች ወር አለፍው አረ መላ በሉን
2026-10-13 22:24:33
0
sintayehu bekele :
የመደበኛ ስልክ ቁጥራችሁን ብትጽፉ ይመረጣል !!
2026-10-13 07:01:33
0
GeneralOmar :
[Red heart]
2026-10-13 08:45:35
0
To see more videos from user @ethiopian.electri, please go to the Tikwm
homepage.