@jahmc1: ~ መስፍን አበበ ከ 22-24 የሚደርሱ አልበሞች ያሉት የቦክስ ጊታር ንጉስ የተባለ....የሚወደድ መምህርም የነበረ ሰው ነው! ~ለብዙ ዘፋኞችም መምህር የነበረ የሚገርሙ ዘፈኖች ያሉት...ጊታርን ለኢትዮጵያ ያስታዋወቀ....እንዲሁም ለልደት የዘፈነ የመጀመሪያው ዘፋኝ ነው! ~መስፍን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ በሰራው ልክ እውቅናንና የሚገባውን ያላገኘ ገራሚ ድምፃዊና የግጥምና ዜማ ደራሲ ነው! ~ዘፈኖቹ የብዙዎቻችን እናትና አባት ማስታወሻ ናቸው....ምክንያቱም የእነሱ ተመራጭ ድምፃዊ መስፍን ነውና! ~ዘፈኖች በቦክስ ጊታር ሲታጀቡ አጥንትን ዘልቀው ይሰማሉ...ልብ ላይ እርፍ ብለው መረጋጋት የሚሰጡም ናቸው!...በድምፁና በዜማው ውስጥ ደስ የሚል ሰላምና መረጋጋት አለ! ~ከምወዳቸው ውስጥ አንዱ "ናፍቆቴ" የተሰኘው ዘፈኑ ነው! ~ከናፍቆት ...ከትዝት ወደየትም መሸሽ አይቻልም! ~ናፍቆትና ትዝታን መጋፈጥ ደግሞ ቀስ በቀሰ እየደከሙና እየሰለሉም መሄድ ነው!....አቅም ያሳጣል! ~ናፍቆት በትዝታ ሲደገፍ ደግሞ ...መመንመን ነው!... ያለፈ ትዝታ ደግሞ በሙዚቃ፣ በሽቶ ጠረን ፣ በሳቅና በጨዋታ ፣ አብረን ባደረግናቸው ነገሮች ድንገት ተወስቶ ድጋሚ  ቁጭት ፣ የህመም ሳቅ፣ ሀዘንና ሆድ መባስ ላይ...የድሮውን መናፈቅ ላይ እንወደቃለን! ~መስፍን አበበም "ናፍቆቴ" በሚለው ዘፈኑም...የሚወዳት ሴት ትዝታ ሲያስቸግረው...ከእሱ ርቃ ሄዳም እሱ ግን ድንገት አስተውሷት ...በትዝታዋ መቸገሩን ይነገረናል! ~ታዲያ በዚህ ዘፈን ትዝታዋ ያስቸገረው ምስሏ ፊቱ ድቅን እያለበትና እየመጣበት በናፍቆት የሚሰቃየው መስፍኔ....ይቺ ሴት ከእሱ ተለይታ ይሆን ወይ ደግሞ ሞታበት ግልፅ የሆነ ነገር የለም....ግን በጣም ከመናፈቁ የተነሳ እሷን የሚጠራት ራሱ "ናፍቆቴ" እያለ ነው! መስፍን አበበ ~”ናፍቆቴ” ❤ ~ታዲያ መስፍን ይችን ሴት ... አሁን ከእሱ ብትርቅም ግን አብረው በነበሩበት ጊዜ ያሳለፈው ህይወት በደስታም በሀዘንም ስአት...በቅደም ተከታል ምንም ሳይረሳ ሲመጣበት...መልኳ ውበቷና ገፅታዋ ፊቱ ላይ መሳል ሲጀምርበት እንዲህ ይላታል... “ተጠራ ትዝታሽ ተራራውን አልፎ ገፅታ ውበትሽ መጣ ተሰልፎ ......ዋ..መጣ ተሰልፎ ከወዲያኛው አገር ከዛኛው ተራራ መጣብኝ ትዝታሽ በተራ በተራ ...........ዋ.. በተራ በተራ” . . . ~ታዲያ ከተለያዩና ከተያዩ ብዙ አመት እንደሆናቸውና ዛሬ በድንገት እንዴት እንዳስታወሰት ለእሱ ራሱ ገርሞታል...ያለችው ከአድማስ ባሻገር እሩቅ ቢሆንም...ርቀት የማይገድበው ትዝታዋ ግን አድማሱን አቋርጦ መጥቶ እሱን ሲያስጨንቀው እንዲህ ይላታል ከታች ባሉት ስንኞች.. “ብዙ ዓመት አለፈኝ ቆየሁኝ ካየሁሽ ዛሬ እንዴት ሆነና ድንገት አስታወስኩሽ               ....  ዋ ድንገት አስታወስኩሽ እርቀሻል በጣም ከወዲያኛው ማዶ ታዲያ እንዴት ደረሰ ትዝታሽ ተራምዶ              .....ዋ ትዝታሽ ተራምዶ “ . . . ~ይቀጥልና እጅግ የናፈቀትን ሴት ናፍቆቴ እያለ የሆነውን የደረሰበትን ያስረዳታል....ተራራውን አሻግሮ ሲመለከት ከዳመናው ላይ እሷ ያያ መስሎት መደንገጡን....አይኑ በሚያየው በሚመለከተው ነገር ላይ እሷን መሳሉን እንዲህ ይነግረታል ከታች... “ከተራራው ወዲያ .. ናፍቆቴ ከዳመናው ውስጥ.. ናፍቆቴ አንቺን ያየሁ መስሎኝ ...ናፍቆቴ ልቤ መደንገጥ ...ናፍቆቴ” . . . ~ማታ ተኝቶ እንቅልፍ አልወስደው ሲል እሷን እያሰበ ጣራ ጣራ ሲመለከትና ሲገላበጥ.. የእሷን ኮቴና ድምጽ የሰማና ጨላማውን ጥሳ ከእሱ ጋር የደረስች ሲመስለው ደግሞ...እንዲህ ይላታል.. “አልጋ ላይ ተኝቼ ..ናፍቆቴ እንቅልፍ አልወስድ ቢለኝ.. ናፍቆቴ ጨለማውን ጥሰሽ ...ናፍቆቴ የመጣሽ ሲመስለኝ...ናፍቆቴ” . . . ~ንቀጥልና ደግሞ እንደው በከንቱ ልቤ ይደነግጣል ያስባል እንጂ በዙሪያዬ እንደሌለሽና ተራራውን አቋርጠሽ ጨለማ ጥስሽ እንደልማጣሽ እኮ ልቤ ደህና አድርጎ ያውቀዋል...ይላታል! “ልቤ መደንገጡ ...ናፍቆቴ መሸበሬ ምን ነው ...ናፍቆቴ በዚያ አንቺ እንደሌለሽ....ናፍቆቴ ደህና አድርጎ እያወቀው...ናፍቆቴ” . . . ~ታዲያ የታችኛውን ስንኞች ስሰማ "ትዝታና ናፍቆት እንደዚህ ያስቸገረው ሙታበት ነው እንዴ?" ያስብለኛል...ምክንያቱም ከዳመናው በላይ እንደምትኖርና ድጋሚ እሷን ማየት እንደማይችልና መሰወሯን እንዲህ ይናገራልና... “እርቀሻል በጣም ከወዲያኛው ማዶ ታዲያ እንዴት ደረሰ ትዝታሽ ተራምዶ                   ..ዋ ትዝታሽ ተራምዶ ከአድማሱ ባሻገር ከዳመናው በላይ ምን ነው ተሰወረሽኝ አይንሽን እንዳላይ” . . ~ይቀጥልና ደግሞ ከማትጠፋበት ከእሱ ጎን ከመገኛው አለመኖሯን...ትዝታው ግን በዙሪያው አልጠፋ ብሎ እስከዛሬም አብሮት እንዳለ እንዲህ እያለ ይነግረናል... "እርቀሽ ከጎኔ ከምትገኝበት ተሰማ ትዝታሽ እኔ ባለሁበት               ...ዋ ዛሬ ባለሁበት እርቀሽ ከጎኔ ከምትገኝበት ትዝታሽ ደረሰ እኔ ባለሁበት               ...ዋ ዛሬ ባለሁበት" . . ~በመንገድ ሲሄድና ሲራመድ የሚያቸው ሰዎች ሁሉ እሷን እየመሰሉት መቸገሩን....አይኑ በሚያው ነገር ላይ እሷን እያሳለ ትዝታውንና ናፍቆቱን እየጨመረ እንዳሳቀያውም ይነገረናል በታችኛው ስንኝ... “በመንገድ ላይ ስሄድ... ናፍቆቴ ከሩቅ ሰው ሲመጣ ...ናፍቆቴ አንቺን ያየሁ መስሎኝ...ናፍቆቴ አይ ያየውት ጣጣ....ናፍቆቴ” . . . “ልቤ መደንገጡ ...ናፍቆቴ መሸበሬ ምን ነው ...ናፍቆቴ በዚያ አንቺ እንደሌለሽ....ናፍቆቴ ደህና አድርጎ እያወቀው...ናፍቆቴ” ~በመጨረሻም በላይኛው ስንኝ ታዲያ እሷ እንደሌለች እንደማትመጣ እያወቀ የልቡ መሸበሩና መደንገጡ ለምን እንደሆነ ራሱ ለራሱ እንዳልገባው ይነገረናል! ✍️ Jah Mc #mesfinabebe #jahmc1 #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fyp @gigi_shebabaw fans

Jah Mc
Jah Mc
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 13 October 2026 09:07:24 GMT
62863
3348
103
222

Music

Download

Comments

josi_ruzelfo
Josi dsm ፋውስቱስ 🇻🇦 ⚓️ :
አባቴ ሲወደው😁 the twisted story at its back aucks though🙈
2026-10-13 10:02:44
7
cleaningservice253
አምሽ የፅዳት አገልግሎት :
hulem endezi sraln kene tztaw thanks
2026-10-13 18:19:05
1
edl182
edl🦅 :
abate betam yiwedewal[Heartwarming]
2026-10-13 17:17:45
2
user1843115222578
user1843115222578 :
wow becha nw lel yemchelew
2026-10-13 09:21:53
1
natnaeltesfaye65
NATI DECOR :
ላባቴ ከ መስፍን አበበ ውጪ ዘፋኝ አልነበረም ለኔ ራሱ ፍቅሩን አጋብቶብኝ ነው ያለፈው !!!!
2026-10-13 11:03:38
48
surajtiga
Bony 💧 :
መስፍንና ኤፍሬም ተደብቄ ምሰማቸው ዘፋኞች ❤️ብቻዬንን ❤️
2026-10-13 17:05:18
17
addika305
addika :
ስላልተጮኸለት በሰወች ልብ ውስጥ የለም ማለት አደለም በጣም ብዙ ህዝብ ህወደዋል
2026-10-13 13:33:49
13
brzafmebrahtu12
𝐁𝐫𝐳𝐚𝐟 {ʙᴇʀʀʏ}😍 :
My favorite❤
2026-10-13 14:08:01
1
yetorhoney
𝖐𝖎𝖗𝖚𝖇𝖊𝖑💫✨ :
22 album ??
2026-10-13 10:51:41
7
kinfemichele16
ክንፈ ሚካኤል :
በትክክለኛው ድሬዳዋ ላይ ያስተምር ነበር
2026-10-13 13:05:03
6
adamreta4
Adam reta :
Please download endihon argln🙏🙏🙏
2026-10-13 17:10:35
1
samrawitmezgebu
Samrawit :
እናት ሳይኖርህ ስትሰማው😭
2026-10-13 10:21:30
6
davo_mit0
davo_mit0 :
ግሩም አርገህ ነዉ ያቀረብከዉ 👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼
2026-10-13 17:04:25
3
selamlihon
selamlihon🕊️🕊️⚓️ :
መስፍን አበበ የ እድሜ ልክ የ አባቴ ማስታውሻ 🥺🥺
2026-10-13 16:36:35
2
tinsusha8
Tinsusha :
አባቴን ማስታውስበት ዘፋኝ። በጣም ይወደው ነበር😭
2026-10-13 20:02:21
1
arisema12
አበባ ( ፃድቃኔ ማርያም እናቴ) :
ብዙ ያልወራለት ዘፋኝ
2026-10-13 19:13:18
1
andargie53
andargie :
ኤፍሬም ታምሩን መድሀኒቴ
2026-10-13 14:43:09
1
dagi_ye_mariyam_lij
dagi 🎙 :
በጣም ማርያምን 🥰🥰🥰🥰 ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት መስፍኔ 🙏🙏🙏
2026-10-13 16:56:11
1
yegeteru.lij
ባላገሩ ኪሩ 🇨🇬 :
music name pls
2026-10-13 12:37:48
1
mmuussiicc_12
Music Lover :
እንጉርጉሮው ከጊታሩ ጋር👌
2026-10-13 09:10:27
4
mintesnot197
MENTU 🏅 :
Mesfin abebe simeta abate new tez milgn 😂
2026-10-13 10:47:58
4
kedstpfuffr
ቅድስት መነፅር :
ኡፍፍፍፍፍፍፍ ምን ላርገው ኢሄን ሙዚቃ my fup
2026-10-13 11:37:43
4
fetiyaahmed4
fafi :
በሂወት አለ
2026-10-13 14:01:11
1
henockyilma
ሶልዲ :
24 ዘፈን ነው አልበም?
2026-10-13 14:43:35
0
To see more videos from user @jahmc1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About