@mullerlawyer: አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝርአመልክቷል፡፡ ይኸውም፡- ✨ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ሥልጣን የሌላው ከሆነ ✨ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ✨ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክርላይ ያለ ከሆነ ✨አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ ✨ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ ✨ክሱ የተነሳበት ነገር _ በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ፤ ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል። 🤝ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም _ ወገን ከላይከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይእንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው፡፡ አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀርመቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠርበድንጋጌው ንዑስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡#lawyer #lawschool #የመጀመሪያደረጃመቃወሚያ

LAWYER M_u-Le የሕግ አማካሪ♏️
LAWYER M_u-Le የሕግ አማካሪ♏️
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 13 October 2026 10:01:42 GMT
8065
245
7
71

Music

Download

Comments

amanoadera
amanoadera :
Important law tip
2026-10-13 16:16:09
2
mullerlawyer
LAWYER M_u-Le የሕግ አማካሪ♏️ :
ሼርርርርርርርርር 💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 ኮፒ ሊንክ.....🤝አድርጉ ለሁሉም እንዲዳረስ Please
2026-10-15 06:40:13
0
beti...bire
🍂𝑏𝑖𝑟𝑒ℎ𝑎𝑛𝑒🦋 :
🥰🥰
2026-10-14 05:53:38
0
zakirahmed503
Zakir :
💪
2026-10-14 08:22:36
1
To see more videos from user @mullerlawyer, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About