@melakufekadu1: የፍትሐብሔር ክርክሮች የሚስተናገዱበት መንገዶች! *********** በመደበኛ የፍትሃብሄር ሥነ ሥርዓት ሙግት የሚመራበት ሂደት የፍትሃብሄር ሥነ ሥርዓት ህጉ ጉዳዮች በፍርድ ቤት በዋናነኝት በሶስት መንገዶች እንዲስተናገዱ እድል ይሰጣል፡፡ እነዚህ ሶስት መንገዶች መደበኛ ሥነ ሥርዓት (Regular procedure)፣ አጭር ሥነ ሥርዓት (Summary Procedures) እና የተፋጠነ ሥነ ሥርዓት (Accelerated Procedure) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡለት ጉዳዮች ባህሪና ሁኔታ ከሶስቱ አንዱን ሥነ ሥርዓት ተጠቅሞ ለቀረቡ ጉዳዮች እልባት ይሰጣል፡፡ በመደበኛ ሥነ-ሥነስርዓት የግራ ቀኝ ተከራካሪዎችን በሁለት ምዕራፎች ከፍሎ ያሟግታል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ ቅድመ ሙግት መስማት (Pre-trial Stage) ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆኑና ተከራካሪ ወገኖች ለክርክሩ የሚያስፈልፉ መረጃዎቻቸውን ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርቡበትና የመከራከሪያ ጭብጥ የሚያዝበት ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ፡- 1. የክስ አቤቱታ (ከሰነድና ከጽሑፍ ማስረጃ ዝርዝር ጋር) ይቀርባል፤ 2. ተከሳሹ የመከላከያ መልሱን ይዞ እንዲቀርብ ይታዘዛል፤ 3. የመከላከያ መልስ(ከሰነድና ከጽሁፍ ማስረጃ እንዲሁም ከማስረጃ ዝርዝር ጋር) ይቀርባል፤ 4. የመከላከያ መልሱ ከቀረበ በኋላ የጽሁፍ ክርክሩ ያቆማል፤ ክሱን ለመስማት ይቀጠራል፤ 5. በተቀጠረው ቀን ባለጉዳዮች ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ይቀርባሉ፣ ከጽሁፍ አቤቱታ ጋር ያላቀረቡትን የጽሁፍ ማስረጃ ይዘው ይቀርባሉ፤ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የጽሁፍ ማስረጃዎች በሙሉ ተጠቃለው እንዲገቡ ይደረጋል፤ 6. ፍርድ ቤቱ ባለጉዳዮችን ወይም ወኪሎቻቸውን ይመረምራል፤ 7. የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከቀረበ ውሳኔ ይሰጥበታል፤ 8. በተደረገ ምርመራ ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ካመነ ወዲያው ውሳኔ ይሰጣል፤ 9. ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ካላመነ የክርክሩ ጭብጥ ይያዛል፡፡ ሙግቱ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ይሸጋገራል፡፡ ይህ ምዕራፍ ሙግት የመስማት (trial stage) በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክሩን የሚሰማበትና ማስረጃ የሚመረምርበት ሲሆን በዋናነት የሚከተሉት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ 1. በቅድመ ሙግት ጭብጡ ከተመሰረተ በኋላ ክርክሩን መስማትና ማስረጃ መመርመር ይቀጥላል፤ 2. ለሁሉም ወገን ምስክሮች መጥሪያ ይላካል፤ 3. የሁሉም ወገን ምስክሮች ተሟልተው ይቀርባሉ፤ 4. ከሳሽ (በተወሰኑ ሁኔታዎች ተከሳሽ) ሙግቱን ይከፍታል፤ 5. ሙግቱ የጀመረው ወገን ምስክሮቹ የሚመሰክሩለትን ነጥብ በአጭሩ ያስረዳል፤ 6. ምስክሮች እውነት ለመናገር ይምላሉ ወይም እውነት እንደሚናገሩ ያረጋግጣሉ፤ 7. ሙግቱም የጀመረው ወገን ምስክሮቹን አንድ በአንደ አቅርቦ ዋና ጥያዌ ይጠይቃል፤ ሌላው ወገን መስቀለኛ ጥያቄ ያቀርባል፤ የጀመረው ወገን የማጣሪያ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ፍርድ ቤቱ በማንኛውም ሰዓት አስፋላጊ የሆነ ጥያቄ ይጠይቃል፤ 8. ሙግቱን የከፈተው ወገን ምስክሮቹን አሰምቶ ከጨረሰ በኋላ ሌላኛው ወገን ምስክሮቹ የሚያስረዱለትን የመከላከያ ነጥብ አስረድቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ምስክሮቹን ያሰማል፤ የመስቀለኛ እና የማጠሪያ ጥያቄዎች ይቀርባሉ፣ ፍርድ ቤቱም አስፈላጊ ናቸው ብሎ ባመነባቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፤ 9. ማስረጃ የመስማት ሂደቱ ሲጠናቀቅ ግራ ቀኙ የመዝጊያ ቃላቸውን ይሰጣሉ፤ 10. በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በግራ ቀኙ የቀረቡትን የጽሁፍና የቃል ማስረጃዎችን መርምሮ እና አጣርቶ በተገቢው ህግ ሚዘን መዝኖ የፍርድ ውሳኔውን ይሰጣል፡፡ Telegram 👇 https://t.me/melakufek facebook 👇 https://www.facebook.com/share/
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Region: ET
Wednesday 14 October 2026 03:07:34 GMT
Music
Download
Comments
gech biruke :
@[Laughing]
2026-10-23 15:25:51
0
Faye the citizen :
are u lawyer???
2026-10-14 13:37:21
0
Feker Meta :
❤️❤️❤️
2026-10-15 11:47:14
0
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm
homepage.