@jahmc1: ~ናፍቆት ምን ያህል እንደሚያወዛውዝ...በፍቅር አለም ውስጥ የአይን ርሃብ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በዚህ ዘፈን እንያለን ~ዘፈኖ ከኢንትሮው ጀምሮ እስከ አስቴር ድምፅ ዜማና ግጥሙን ጨምሮ....በአንድ ላይ ናፍቆትን ይገልፃሉ ፣ ያስታምሙታል....አንዳንዴ ስጋ ለብሶ ናፍቆት ይታያል በዚህ ዘፈን! ~እኔ በግሌ ናፍቆት ምን ይመስላል ተብየ ብጠየቅ "አካል ሰው" የሚለውን ይሄን የአስቴርን ዘፈን ይመስላል ነው የምለው! ~በዚህ ዘፈን አቀናባሪውን ደረጀ መኮንን ፣ግጥምና ዜማ ደራሲውን አበበ መለሰን ፣ሳክሶፎኒስቱን ጥላዬ ገብሬንና ድምፃዊቷን አስቴር አወቀን እኩል የማደንቀበት ዘፈን ነው! ~ኢንትሮው ፣ ዜማው የአስቴር አዚያዚያም በቃ አንጀት ይበላል....ናፍቆትን ይገልፃል! . . . አስቴር አወቀ ~ "አካል ሰው"❤ ~በዘፈኑ አስቴር የምትወደው ሰው ቀርቶባት ትንቆራጠጣለች ደጅ ደጁን እያየች...የወዳጇን አይን ተርባለችና ለማየት እጅግ ናፍቃ ትጠብቃለች... አይኗን ወደ መንገድ ልካ እሱን ፍለጋ ቢንከራተትም እሱ ግን አልመጣም....ዓይኑን ሳታይ በመቅረቷና በመመለሷ እንዲህ ትለዋለች...         "ትመጣለህ ብዬ ስጠብቅህ           ከማዶ በላይ እህህ          ቀርተህ ስመለከት አንተዬ           ደጁን ደጁን ሳይ እህህ         ዓይኔ ሲንከራተት ላትመጣ           ከመንገድ ላይ እህህ         አጥቼህ ተመለስኩ ናፍቆቴ           ዓይንህን ሳላይ እህህ “ . . . . ~ታዲያ አስቴር ከወደደችና ካፈቀረች ..በፍቅር ቀልድ እንደማታውቅ ፣ ያልተሸነፈ ሰው መስላ ማስመሰል እንደማትችልና ፍቅሯን በግልፅ የምትናገርና የምታሳይ ሴት መሆኗን ትናገራለች...ታዲያ የምትወደውን ሰው ጠረን ከትራሷ ልብስ ቀርቶ...ስተኛ እሱን እሱን እንደሚሸታት አልፎ አልፎ የሽቶ ጠረኑን እንደሚያስታውሳትና ትዝታ እያሳቀያት ናፍቆት እየበዛበት መሆኑን እንዲህ ትነግረዋለች.... “እወዛወዛለው... አካልዬ ትዝታው በርክቶ ጠረንህ ከልብሱ.. አካል ሸጋ ከትራሱ ቀርቶ ፍቅር ከነካካኝ.. አካልዬ እኔስ ከወደድኩኝ መመለሻም የለኝ...አካልዬ አንዴ ከጀመርኩኝ” . . . ~አስቴር እንደሌሎቹ መውደዳቸው ማፍቀራቸው እንዳይታወቅባቸው እንደሚታገሉት አይነት አፍቃሪ አይደለችም...እንዳይኮራብኝ ምናምን ብላ ፍቅሯን አትደብቅም ፣ መሸነፏን መውደዷን አላሳይም አትልም...ተይዛ እንዳልተያዘች ድራማ አትሰራም....ከስሜቷ ጋር ግብግብ አትገጥም....በአጠቃላይ ካፈቀሩ ወዲያ መደባባቅ ምን ጥቅም የምትል ሴት ናት ለዛም እንዲህ ትላለች በታችኛው ስንኝ “ል.....ናዘዘዘው እንጂ አ.......ካል ሰው ዝምታስ ያስጠቃል እህህ እ........ራብ እየሰጠኝ የአ.......ካል ሰው መውደድ ያስጨንቃል እህህ ካፈቀሩስ ወዲያ ምን ያደባብቃል “ 2x . . . ~አስቴር "የምጨነቅልህ የማስብለህ ዘመዴ አንተ ነህ....የምወድህና የማፈቅርህ የያዝኩት በሆዴ የማስብህ አንተ ነህ " ትለዋለች የቀረባትን  የምትወደውን የናፈቃትን ሰው በታችኛው ስንኝ... “ዘመዴ አንተው ነህ ዘመዴ እህህ ዘመዴ ዘመዴ አንተው ነህ እህህ ዘመዴ የያዝኩህ በሆዴ” . . . . ~አስቴር ናፍቆት ሲወዘውዛት ውሃ ልቅዳ የሚል ምክንያት እየፈጠረች እሱን ለማየት ገባ ወጣ እንደምትል...ብርድና ፀሀይ ሳትፈሯ እሱን ብቻ ተርባ አይኑን ለማየት አስር ጊዜ ወጣ ገባ እያለች መንገድ መንገዱን እንደምታይ....እሱ ወዳለበት ሀገርና መንደር ፍለጋ እንዳትወጣ ደግሞ ቤተሰቦቿ አይደለም ፍለጋ ወጥታ አስር ጊዜ እሱን ለማየት ወጣ ገባ ለምትለውም እየተቆጧት መሆኑን እንዲህ ትገልፃለች.... “ውሃ ልቅዳ ብዬ ...አካልዬ ዘዴ እየፈጠርኩኝ ተወዛወዝኩልህ ..አካል ሸጋ ወጣ ገባ እያልኩኝ ቤቶቼም ተቆጡ ...አካልዬ እንዳልሄድ ወደ ሃገርህ መጣ ቀረ እያልኩኝ ...አካል ሸጋ በወጣሁኝ ቁጥር” . . . . “ስ.....ንቴ ተመላለስኩኝ አ.....ካል ሰው ምሽቱን በሙሉ እህህ ስ....ንት ጊዜ ዞርኩት አ....ካል ሰው ጓሮውን በሙሉ አካል ሰው ልቤን ከበራፉ እንደተወኩት ወድቆ ልቤን ከበራፉ እንደተወኩት ወድቆ “ ~በመጨረሻም በላይኛው ስንኞች ስንቴ ወዳጇን ለማየት ጓጉታና ናፍቃ ስንቴ ገባ ወጣ እንዳለች ፣ስንቴ ተመላልሳ ጓሮውን እንደዞረች ...እንደዛም ሁና ሳይመጣ በመቅረቱ...ልቧ በር ላይ  ቀርቶ  ዛሬም እሱን ጥበቃ ላይ መሆኗን ትናገራለች . . . ግጥምና ዜማ ~ አበበ መለሰ ቅንብር ~ ደረጀ መኮንን ሳክስፎን ~ ጥላዬ ገብሬ ✍️ Jah MC #aster #asteraweke #jahmc1 #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @gigi_shebabaw fans

Jah Mc
Jah Mc
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 14 October 2026 11:38:45 GMT
36361
2276
96
342

Music

Download

Comments

yu58963
yu :
ufffff..thats the feeling of asters aweqes music🥰🥰legendery
2026-10-14 20:02:54
1
yoba.der
yoba Der :
arrangement 100% lyrics % melody % astu offff
2026-10-14 16:20:31
1
user9878966349719
ሲፈን ጌታሁን :
ፍቅርን ኩላ አሳምራና ሰጋ አልብሳ ውብ አርጋ ፈጥራ በዘፈኖቿ አግብተን ወልደን እራሱ አብረናት እየዘፈንን አረጀን ልክ እንደ አፍላው እድሜያችን ነው ዘፈኗን ሰንሰማ የሚያረገን።ሺ ዓመት ለአሰቱ ከድብርት መንጭቃ አውጥታ በፍቅር ለምታሰክረን
2026-10-14 14:20:41
35
henok_neff
Henok Adane :
Introው ደግሞ👌🖤🖤
2026-10-14 13:47:10
29
wubass1
WB🇪🇹 :
የሙዝቃ ልክ
2026-10-14 18:33:46
7
edendbas
Eden🏋️‍♀️ :
The intro 🔥🔥 ሆዴ ይላወሳል🥹
2026-10-14 20:26:24
2
tesfahungg
ቴስ :
I went back when I heard this music. 🥰🥰🥰
2026-10-14 18:53:39
1
astuka96
Astuka :
ልትገለኝ ነው🥺🥺
2026-10-14 14:26:13
5
gigi_shebabawfan2
gigi_shebabaw fans :
ይህ የአሰቱ ሙዚቃ😭❤️
2026-10-14 11:47:17
5
beye1919
Beya :
ፔንኪለር 👌👌👌
2026-10-14 19:53:50
4
hope04785
Hope :
ፎቶው🔥🔥
2026-10-14 11:40:30
3
tekeyemaryam
teke yemaryam lij :
ኢንትሮው ብቻ ሌላ አለም🥰🥰🥰 ጉሉኮስ የሆነ ሙዚቃ
2026-10-14 13:55:23
2
cateringandagelgel
ቤቲ አገልግል :
7ጥቁር አይደለም 10ነዉ
2026-10-14 19:14:21
1
lionardodicaprio71
DiCaprio :
ብዙ አመት ወደደደ.....ኋላ......ትዝታ በቻ
2026-10-14 17:40:46
2
genetu06
ገኒ የማርያም ልጅ157 :
ምርጦ🥰🥰🥰
2026-10-14 17:59:32
1
yfyiyezfjonvfd
ሸዋ :
አይ ጊዜ [Heartwarming]
2026-10-14 19:20:41
1
amaltad19
amaltad19 :
manat?
2026-10-14 15:23:05
0
graney79
M G GARAGE :
እውነት ነው
2026-10-14 17:59:37
1
mmuussiicc_12
Music Lover :
አስቴር❤️
2026-10-14 11:43:39
1
teddy.yo.yalme
Teddy Yo Yalme :
ቀጥልበት አገላለጽ ይልካል ጀግና
2026-10-14 18:27:39
4
zoran05874
zoran :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰 ወይኔ ወደ ሁዋላ መለስከኝ በትዝታ አስለቀስከኝ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-14 14:16:53
1
surafel079
sura Fel🤴✌️ :
ለዚ ሙዚቃ ቃላት የለኝም
2026-10-14 18:14:29
1
tizazuwujira
ሠው ሆይ ብርቱ ሁን :
1982
2026-10-15 05:43:54
0
abresh.tesfaye
Abreham TH :
አስቱካ!
2026-10-15 05:18:43
1
robelone
R.A :
ይሔ ዘፈን እኮ ፋርማሲ ነበር መሸጥ የነበረበት!
2026-10-15 04:26:10
1
To see more videos from user @jahmc1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About