@aynalem225: ''ለሰው እየሰራህ እንዴት ሰው ስላንተ የሚናገረውን አታውቅም?? ጋዜጠኛ ጌታሁን አሰፋ እንደጻፈው ''የ20-30 ዝግጅት እንደተጀመረ የስራ መመሪያ ለመቀበል ቢሮዋ ተገኘሁ. በመሃል ‘ሰዎች ስላንተ ምን የሚያስቡ ይመስልሃል?’ ብላ ጠየቀችኝ. ደፈር ብዬ '' ማክዳ እኔ ትኩረቴ ስራዬ ላይ ነው. ኮመንት ብዙም አላይም'' ብዬ መለስኩ. በእኔ ቤት በራስ መተማመኔን ማሳየቴ ነበር. ቀጥላ ግን የዛሬውን ጌታሁን የፈጠረውን ትልቅ ቁም ነገር ነገረችኝ. ''ለሰው እየሰራህ እንዴት ሰው ስላንተ የሚናገረውን አታውቅም?? ለሚድያ ባለሙያ ነዳጅ የሚሰጠው ስራውን የሚመለከትለት ህዝብ ነው. ህዝቡን መስማት ያቆምክ ቀን ስራህን ብታቆም ይሻልሃል. ስለስራህ ሰው ምንም አስተያየት ካልሰጠህ ገና ስራ አልጀመርክም ማለት ነው. ወይ የሚጠላህ ወይ የሚወድህ ሰው መኖር አለበት! ያኔ የተወቀስክበትን እያስተካከልክ የተመሰገንክበትን እያሳደግክ ስምህን ለማስጠራት ትበቃለህ'' አለችኝ. ከእርሷ ጋር 30 ደቂቃ ካወራህ ለ30 አመት የምታብሰለስለው አዲስ ነገር ልትሰማ ትችላለህ. በስራቸው የምናደንቃቸውን የምናከብራቸውን ጠንካራ ሰዎች በህይወት እያሉ እናድንቅ ካልን መጀመር ያለብን ከማክዳ አሰፋ ነው! ይህ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ለትክክለኛው ሰው እንደተሰጠ እኔም የስራ ባልደረቦቼም ምስክር ነን.'' እንኳን ደስ አለሽ አለቃዬ! በያፌት ገ/ህይወት #አይናለም

Aynalem Bezabh
Aynalem Bezabh
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 14 October 2026 14:15:36 GMT
7599
59
2
2

Music

Download

Comments

firehiwot.alemu
Firehiwot Alemu :
congra maki
2026-10-14 19:30:24
1
lonchris2
Lonchris :
ማኪ ጌታ እንኳን ረዳሽ እየሱስ ያድናል
2026-10-14 17:48:56
0
To see more videos from user @aynalem225, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About