@cinematic.grace_8:

Grace 🎬
Grace 🎬
Open In TikTok:
Region: US
Wednesday 14 October 2026 21:25:12 GMT
3909
139
4
6

Music

Download

Comments

norabae11
Nora :
Soo beautiful i followed u from instagram (now u need to make an X account)[Big LOL]
2026-10-16 01:33:57
2
jenna.carroll23
jenna.carroll23 :
💗💗💗
2026-10-15 02:25:54
1
To see more videos from user @cinematic.grace_8, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

###ዛሬ በጠዋት መገናኛ ሄድኩኝ...? # የማኅበረሰብ ቅርስ ሲዋረድ ዝምታ ለምን? የጉራጌ ማኅበረሰብ መገለጫ የሆነው «ቢጥር» (ጣባ) በካፌ ውስጥ የእጅ መታጠቢያ ሆኖ አገኘሁት! በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ብዙ ውይይት ሲያስነሳ የነበረው አንድ ጉዳይ ነበር። ይኸውም የጉራጌ ማኅበረሰብ ባህላዊ መገለጫ የሆነው፣ ክትፎ ለማዘጋጀት የሚያገለግለው «ቢጥር» (ጣባ) በአንድ ካፌ ውስጥ የእጅ መታጠቢያ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ የሚገልጹ መረጃዎች ነበሩ። ይህን መረጃ ካየሁ በኋላ፣ እውነት መሆኑን በራሴ ለማረጋገጥ ወሰንኩ። ስለዚህ በጠዋት የነበረኝን ሥራ ትቼ ወደ መገናኛ አመራሁ። የተጠቀሰውን ካፌ አግኝቼም ወደ ውስጥ ገባሁ። ካፌው የመጀመሪያ ፎቅ ላይ ጥቂት ደንበኞች ነበሩ። የተባለውን የእጅ መታጠቢያ ለማግኘት ዙሪያውን እያየሁ ሳለ፣ አንዲትን የካፌውን አስተናጋጅ በአክብሮት ጠራኋትና፣ «እህቴ፣ የእጅ መታጠቢያው የት ነው?» ብዬ ጠየቅኋት። እሷም፣ «ከላይ ባለው ካፌ ነው» ብላ መለሰችልኝ። ወደ ጠቆመችኝ ቦታም በደረጃው ወጣሁ። ደረጃውን ጨርሼ ስወጣ፣ ፊት ለፊቴ የጉራጌ ማኅበረሰብ ባህላዊ መገለጫ የሆኑትን፣ ክትፎ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉትን ሦስት ቢጥሮች (ጣባዎች) ተራ በተራ ተደርድረው የእጅ መታጠቢያ ሆነው አየኋቸው። ያንን ሁኔታ ሳይ ደነገጥኩ። በማኅበራዊ ሚዲያ ሲወራ የነበረው ነገር እውነት ሆኖ አገኘሁት። የማኅበረሰብ ታሪክና ባህል መደብዘዝ የሚጀምረው እንደዚህ ካሉ ተግባራት አይደለምን? ከዚያም እነዚህን የማኅበረሰብ መገለጫዎች እንዲህ ዝቅ ባለ አገልግሎት ለመጠቀም ምን እንዳነሳሳቸው ከራሴ ጋር መጠያየቅ ጀመርኩ። በድፍረት ወይስ በእውቀት ማነስ? በእውነቱ ባህላዊ ጠቀሜታውን ባለማወቅ ይሆናል እንጂ እያወቁ አያደርጉትም ብዬ ራሴን ለማሳመን ሞከርኩ ለዓለም መድረክ በዩኔስኮ ለማስተዋወቅ   የተጀመረው የክትፎ ማዘጋጃ የሆነው (ጢጥር) ጣባ በዚህ ደረጃ መመልከት ያማል። ከዚያም ወደ ካፌው ገብቼ ከተደረደሩት ወንበሮች አንዱን ስቤ ተቀመጥኩ። ትንሽ ቆይታ አንዲት አስተናጋጅ ወደ እኔ ቀርባ፣ «ወንድሜ፣ ምን ላምጣልህ? ምን ይቅረብልህ?» ብላ በለስላሳ ድምፅ ጠየቀችኝ። እኔም፣ «በጠዋቱ ትኩስ ነገር አለ?» ብዬ ጠየቅኋት። «አዎ፣ አለ። ምን ይሁንልህ?» አለችኝ። እኔም ፈገግ ብዬ፣ «እንደ እኔ ጠቆር ያለ አንድ ማኪያቶ አምጪልኝ» አልኳት። እሷም እየሳቀች፣ «እሺ፣ አንተ ግን ጠቁር አይደለህም!» ብላ በቀልድ መለሰችልኝና ሄደች። ቆይታ ማኪያቶውን አመጣችልኝ። አመስግኜ ጠጣሁት። ከዚያም ሂሳቤን እንድታመጣልኝ ጠየቅኋት። ሂሳቡን ከከፈልኩ በኋላም፣ «እህቴ፣ የካፌውን ባለቤት ወይም ማናጀሩን ላናግር እፈልጋለሁ። ጠርተሽ ታመጪልኝ?» አልኳት። እሷም ማናጀሩን ልትጠራ ሄደች። ብዙም ሳይቆይ የካፌው ማናጀር ወደ እኔ መጣች። «አቤት፣ ወንድም፣ ጠርተኸኛል?» አለችኝ። «አዎ፣ እንዴት አደርሽ?» ብዬ ሰላምታ አቀረብኩላት። ከዚያም፣ «ካፌያችሁ ያምራል» አልኳት። እሷም፣ «እሺ፣ እናመሰግናለን» ብላ መለሰችልኝ። እኔም በመቀጠል፣ «የካፌው ባለቤት የለም እንዴ?» ብዬ ጠየቅኋት። «አዎ፣ የለም» ብላ መለሰችልኝ። ከዚያም ወደ ዋናው ጉዳይ ገባሁ። «ቢጥር (ጣባ) ታውቂያለሽ?» ብዬ ጠየቅኋት። «አላውቅም» አለችኝ። «ክትፎ በልተሽ አታውቂም ወይ?» ብዬ ስጠይቃት፣ «ክትፎ አልወድም» ብላ መለሰችልኝ። እኔም፣ «እሺ፣ ይሁን» ብዬ በመቀጠል ቢጥር (ጣባ) ማለት የጉራጌ ማኅበረሰብ ባህላዊ መገለጫ መሆኑንና ክትፎ ለማዘጋጀት የሚያገለግል ባህላዊ ዕቃ መሆኑን አብራራሁላት። ከዚያም ወደ ካፌው የመጣሁበትን ዋና ዓላማ አቀረብኩላት። «በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲወራ የነበረው ጉዳይ ይህ ነው። የጉራጌ ማኅበረሰብ ክትፎ ለማዘጋጀት የሚጠቀምበትን ባህላዊ ጣባ (ቢጥር) በካፌያችሁ ውስጥ የእጅ መታጠቢያ አድርጋችሁ እየተጠቀማችሁበት ነው የሚል መረጃ እየተዘዋወረ ነው። ይህን ጉዳይ እንዴት ታዩታላችሁ? በስህተት ነው ወይስ ባህላዊ ጠቀሜታውን ባለማወቅ?» ብዬ ጠየቅኋት። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለጠፉትን መረጃዎችና በኮሜንት የተሰጡትን ምላሾችም አሳየኋት። እሷም ለተወሰኑ ደቂቃዎች መረጃዎቹን በጥንቃቄ አነበበች። ከዚያም ለሚመለከተው አካል ለማድረስ ፎቶ ማንሳት እንደምትችል ጠየቀችኝ። እኔም ፈቃዴን ሰጠኋት። ከዚያ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ስለ ቢጥር (ጣባ) በዝርዝር ተወያየን። እሷም ስልኳን አውጥታ ለሚመለከተው አካል ደወለች። እኔም ለጊዜዋና ለትብብሯ አመስግናለሁ ብዬ ከካፌው ወጣሁ። #የሚገርመኝ ጥያቄ፦ የባህልና የቅርስ ጠባቂዎች የት አሉ? እኔን ሁሌም የሚገርመኝ አንድ ጉዳይ አለ። የማኅበረሰብ ታሪክና ቅርስ እንጠብቃለን ብለው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚናገሩ ሰዎች የት አሉ? የማኅበረሰብ ታሪንና ባህልን ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት በልገሳ ማሰባሰብና በመልዕክት ማስተላለፍ ብቻ ሊገደብ ይገባልን? የማኅበረሰብ ባህላዊ ቅርሶች አግባብ ባልሆነ መንገድ ሲጠቀሙባቸው፣ ለምን ዝምታን እንመርጣለን? ለምንስ ወጥተን ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል አናደርስም? ባህልን መጠበቅ በቃል ብቻ አይደለም፤ በተግባርም ይገለጣል። ቅርስ የትናንት ታሪክ ብቻ አይደለም፤ ለነገው ትውልድ የምናስተላልፈው ውርስ ነው። ዛሬ የማናከብረውን ባህል ነገ እንዲጠበቅ መጠየቅ አንችልም። ስለዚህ የጉራጌ ማኅበረሰብን ጨምሮ የሁሉም ማኅበረሰቦች ባህልና ቅርስ እንዲከበር፣ እንዲጠበቅና ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል። .. ይህን መረጃ ለሚመለከተው አካል አድርሱት በተለይም ለባህል እና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም የጉራጌ ባህላዊ ዕቃዎችን ለሚሸጡ ግለሰቦች። #ባህልን_እንጠብቅ #ቅርስን_እናክብር #የጉራጌ_ባህል © Abera Wema

About