@taddy2022: በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ያጋጠመው ብልሽት ተስተካክሎ የኃይል አቅርቦት ሙሉ ለመሉ ተመልሷል በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቴክኒክ ባለሞያዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ከዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ 3፡00 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወደ አገልግሎት ተመልሷል፡፡ በትራንስፎርመር ብልሽቱ ምክንያት ከማከፋፈያ ጣቢያው ወጪ የሚሆኑ 12 የመካከለኛ መስመር ፊደሮች በመቋረጣቸው በተወሰኑ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኃይል በጊዜያዊነት በማበዳደር እየተሰጠ የቆየ ሲሆን፤ በአሁን ወቅት የተበላሸውን ትራንስፎርመር በሌላ ተተክቶ የኃይል አቅርቦቱ ወደ ነበረበት ተመልሷል፡፡ ከማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል ያገኙ የነበሩ አካባቢዎች 👉 ሉካንዳ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት፣ አባጃሌ፣ ኮልፌ 18፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ አጠና ተራ፣ ታይዋን፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ 👉 አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን አካባቢ፣ እህል በረንዳ፣ መሳለሚያ፣ አውቶብስ ተራ፣ አማኑኤል ቤ/ክ ፊት ለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣ ኳስ ሜዳ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ሰፈረ ሰላም፣ ግሩም ሆስፒታል፣ አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት ፣ሰባተኛ፣ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ 👉 ጦር ኃይሎች፣ ቀራንዮ፣ ቤተል፣ መንዲዳ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕና አካባቢዎቻቸው አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ወድ ደንበኞቹ ችግሩን ተረድተው ላሳዩት ቀና ትብብርና ለነበራቸው ትዕግስት ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ፤ለተፈጠረው መስተጓጎልም ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሞያዎች የኃይል አቅርቦቱ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሌትተቀን ላሳያችሁት ርብርብ አገልግሎቱ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት#ethiopiannews #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #foryou #fyppppppppppppppppppppppp
TEDA MEDIA
Region: ET
Thursday 15 October 2026 07:15:19 GMT
Music
Download
Comments
zuzu :
እናመሠግናለን መብራትዬ
2026-10-15 13:02:27
0
Weyneshet Kebede :
እግዚአብሔር ይመስገን
2026-10-15 13:31:48
0
user9218775782173kidest :
እናመሰግናለን
2026-10-15 12:14:53
0
Fozima spa :
እናመሠግናለን ቤተል
2026-10-15 11:48:52
0
To see more videos from user @taddy2022, please go to the Tikwm
homepage.