@ichege_eotc_wd_media: በ፵፭ኛው ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የወላይታ ሀገረ ስብከት በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው የሚደነቁ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ሪፖርቱ በዛሬው ዕለት አቅርቧል። በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አመራርና ጥብቅ ክትትል የወላይታ ሀገረ ስብከት በ2018 በጀት ዓመት በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ በመንበረ ጵጵስናው እና በ16ቱም ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኙ ገዳማት እና አድባራት በብፁዕነታቸው ጸሎት፣ ቡራኬ፣ መመሪያ ሰጪነት፣ ጥብቅ ክትትል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት:- - በመንፈሳዊ የአብነትና ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች በማስፋፋትና በማጠናከር፣ - ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋትና በማጠናከር፣ - አዳዲስ አማኒያንን አስተምሮ፥ አስጠምቆ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ፣ - አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት እና ሰ/ት/ቤትን በማስፋፋት፣ - መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ - ሰበካ ጉባኤን በማደራጀት፣ - ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎችን በማስፋፋት፣ - በገንዘብና ንብረት አስተዳደር፣ .....ወዘተ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ሀገረ ስብከቱ አበረታች ድሎችን አስመዝግቧል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! #እጨጌ_የወላይታ_ሀገረ_ስብከት_ሚዲያ ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ 👉 ለርቱዕ መረጃ የሚድያው ቤተሰብ ይሁኑ፤#FOLLOW_SUBSCRIB_LIKE_SHARE_ያድርጉ
እጬጌ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሚድያ
Region: ET
Thursday 15 October 2026 19:27:26 GMT
Music
Download
Comments
tata :
blessed you
2026-10-17 05:59:41
0
BAzzz :
geta kekifu yikelilachew
2026-10-16 08:04:08
0
sewalem :
jegna nachuhhh report endenante yekreb [Red heart][Red heart]
2026-10-16 05:37:27
0
Muler mk12 :
ጀግና አባታችን እድሜና ጤና ይስጥልን🥰🥰🥰
2026-10-16 02:08:30
34
Black diamond :
አንቱ ደግሞ ፖለቲካውን ነው አጋነውታል
2026-10-16 06:47:26
3
LEMA GUTEMA :
[Red heart]
2026-10-16 03:34:56
0
Obsi :
በእውነት ጵጵስናን ከነሙሉ ክብሩ ያየንባቸው አባታችን ቡራከዎ ትድረሰኝ ።በእውነት በሌሎች አባቶች ተስፋ ቆርጠን እንዳንቀር እግዝሐብሔር እርሶን አስነሳልን
2026-10-16 04:32:07
14
zagole Design :
እግዚአብሔር ይመስገን ተስፋ እንዳንቆርጥ ጥቂት አባቶችን አስቀምጦልናል
2026-10-16 09:05:43
4
jhon :
እንኮራባቸዋለን ከምር የክርስትና ማሳያ የሆኑ ድንቅ መሪ
2026-10-16 03:22:54
6
Melaku Hailu :
አባታችን ቡራኬያቸው ይድረሥብን
2026-10-16 04:54:58
7
yon :
የወላይታ አባት ብቻ ሳይሆን የመላዉ ኢቲዮጵያ ልዩ አባትናቸዉ
2026-10-16 04:54:09
7
ela.፳፯ :
እውነት በአደባባይ ሲመሰከር እንዴት ደስ ይላል [Pray]
2026-10-16 03:28:36
7
መምህር አኮ :
ሠናየ ዜና ተስምዐ በኀወላይታ ወላይታ
እስመይስሃቅ ኮነ ለቤተወላይታ ምህረታ
2026-10-17 08:35:13
1
kIYA🦋 :
እውነት ነው ብፁዕነታቸው በረከታቸው ይድረሰን🙏🙏🙏🙏❤️
2026-10-16 06:38:58
5
Sabom Tedi WTF :
ጀግና አባትእኮ ነው ያለን ታድለን
2026-10-16 08:39:02
3
Hena :
እኔ ጴንጤ ብሆንም አቡነ ይስሃቅ በጣም ነው ደስ የሚሉኝ
2026-10-16 08:37:07
2
firewderese :
የሰራ ሰው እንደዚህ በልበ ሙሉነት ይናገራል!!ፈጣሪ ይጠብቃችሁ
2026-10-16 08:09:58
3
Dakstar21 :
ይህ ሁሉ ተሠርቶም ብሩ አነሰ ተብለው አይሸለሙም🥺
2026-10-16 08:36:22
2
Snte Abebe :
የብፁዕነታቸው ረድኤትና በረከት ትደርብን
ዝምምምም ብለው በጣም ነው የሚመቹኝ የምወዳቸው።
ጫወታው የፖለቲካ የሪፖርት ሽኩቻ ሳይሆን የነብስ ማዳን እንደመሆኑ መጠን በተወጡት በሀዋርያዊ ተልዕኮ አንፃር ወላይታ ሀገረ ስብከት ትልቅ ማበረታቻ ኮሌጅ ነገር ሊሸለሙ ይገባል።
2026-10-16 00:09:28
9
Yitbe12🤍 :
የኔ አባት ቡራኬዎት አይለይን 🙌☺️
2026-10-16 09:50:07
2
jusy :
አባ አከበርኮት
2026-10-16 03:36:49
3
bob :
አባታች እድሜ እና ጤና ይስጦት 🙏🙏🙏🙏
2026-10-16 04:34:46
3
Telemos Tesfaye🇪🇹 :
የአባታችን ቡራኬ ይድረስብን♥️
2026-10-16 05:14:15
1
hanybager1 :
የሀገሪቷ ሊቀ ጳጳስ አድርጉልን
2026-10-16 05:23:28
1
እንዳላማው ደሳለኝ :
ትክክለኛ አባት እና ልጅ እናንተን አየን።እግዚአብሔር እድሜ እና ፀጋ ይስጣችሁ ።
2026-10-16 04:41:38
1
To see more videos from user @ichege_eotc_wd_media, please go to the Tikwm
homepage.