@theonlyunfulfilleddream: ‎ባልና ሚስት ናቸው መንፈሳቸውን ለማደስ ሲሉ የእንስሳት ፓርክ ውስጥ ጉብኝት እያካሄዱ ሳለ ዝንጀሮው ከሚስቱ ጋር ሲላፋ ተመለከቱት ። ይህንን ከስተት በሽቦ ከታጠረው አጥር ራቅ ብላ የምትመለከተው ሚስት ባለቤቷን “ ውዴ ሆይ ! እኝህ ዝንጀሮዎች ምንኛ የሚማርክ የፍቅር ታሪክ ነው ያላቸው ! ” አለችው ። ይህንን ትዕይንት እንደተመለከቱ ብዙም ሳይቆዩ ወደ ቀጣዩ አጥር አመሩ ። ደረቱን ገልብጦ በዝምታ የተቀመጠ አንበሳ ያያሉ ። ‎ ‎የአንበሳው ሚስት ደግሞ ከእርሱ በተወሰነ ርቀት ፈንጠር ብላ ቁጭ ብላለች ። የፀጥታ ድባብ የሰፈነበት አጥር ነበር ።ይህንን ሁኔታ ያስተዋለችው ሚስት ባሏን “ ውዴ ሆይ ! ምንኛ መራራ የሆነ ህይወት ነው እየገፉ ያሉት!” አለችው። ባል ሚስቱን “እስኪ በእጅሽ የያዝሽውን የጁስ መያዣ ባዶ ጠርሙስ ከአንበሳው ሚስት ላይ ወርውሪው እና ባሏ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ተመልከቺ ”አላት ጠርሙሱን ወደተባለችው ቦታ ስትወረውረው አንበሳው ከነበረበት ቦታ በመነሳት አጓራ ። ለሚስቱ ያለውን ፍቅር ለመግለፅ ከጥቃት ሊከላከልላት ተንጎራደደ ። ከለላ ከመሆን ባለፈ መልኩ ሹል ጥርሶቹን በመፈልቀቅ ወደ ሽቦው ተጠጋ ። ፀጉሩን እያርገፈገፈ ያጓራል ። ዘራፍ አለ ። እምቢ ላገሬ ሳይሆን እምቢ ለሚስቴ አለ ።በተመሳሳይ መልኩ አብረው እየተላፉ ወዳሉት ዝንጀሮዎች ክልል መጡ ። ሚስት አሁንም ሌላ ባዶ ጠርሙስ ወደ እነርሱ ወረወረች ። ዝንጀሮው ሚስቱን ትቶ ነፍሴ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ ። እርሷን ትቶ ከሩቁ ይጮሃል ። ጠርሙሱ ሚስቱን ሳይሆን እርሱን እንዳይመታው ነበር የሰጋው ። የዚህ ሽለላ እምቢ ለሚስቴ ሳይሆን እምቢ ለራሴ ነበር። ‎ ‎ሰዎች በሚያሳዩት ግልብ ፍቅር አትሸንገል ። አደባባይ ላይ አላፊ አግዳሚው የሚመለከታቸው ቅጥ ያጡ ልፊያዎች አሸዋ ላይ ከተገነባ ቤት የጠነከረ መሰረት የላቸውም ። ‎በጥበብና በማስተዋል ዛሬን ለነገ እንኑር 🙏

ህጋውይ ድሀ
ህጋውይ ድሀ
Open In TikTok:
Region: AE
Friday 16 October 2026 12:39:04 GMT
2656
63
6
14

Music

Download

Comments

adanach702
Adanach :
ታሪከኛ🥰
2026-10-16 17:25:26
0
nuryare03
yarehman :
👌👌👌
2026-10-17 12:49:26
0
zufan.shambe
Ozil :
🥰🥰🥰
2026-10-16 18:12:56
0
nimonalemesa4
@Nimoona Lammeessaa :
❤️❤️❤️
2026-10-16 14:18:38
0
seada.6464
ለዶፍ ነዉ ጉዞዬ ካፊያ አያስፈራኝም6464# :
🥰🥰🥰
2026-10-16 14:11:19
0
user2076234430081
ቡሩህ ተስፋ አለኚ :
🥰🥰🥰
2026-10-17 06:14:12
0
To see more videos from user @theonlyunfulfilleddream, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About