@layna.haywood: Just keeping it fun #foryoupage #fyp #xyzbca #crazy #jetblackhair

layna💋
layna💋
Open In TikTok:
Region: US
Saturday 17 October 2026 00:45:02 GMT
1567
125
2
2

Music

Download

Comments

beccalynn12cox
Beccalynn Cox :
2026-10-17 01:17:42
1
To see more videos from user @layna.haywood, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በክሕደቱ ምክንያት ንስጥሮስን የቀሰፈው መልአክ-ቅዱስ ዮናኤል! የረከሰና ተጣራጣሪ ስሙ ንስጥሮስ የተባለውን ከሓዲ ንጹሕና ኅቱም በኾነ ድንግልናዋ ላይ እና በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ያለ ወንድ በኅቱም ድንግልና ጸንሳ በኅቱም ድንግልና በወለደች በልጇ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በመሳደቡ በእውነት አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ዮናኤል እጅ እንደቀሰፈችው ተነገረ፡፡ የንስጥሮስ ክሕደቱ ፈጽሞ በበዛ ጊዜ ከበታቹ ያሉ ካህናት ከክሕደቱና ከስሕተቱ እንዲመለስ ይቈጡትና የታዘቡት ነበር፡፡ ሰይጣን በሽንገላ ምክሩ አስቶታልና እርሱ ግን ምንም አልተመለሰም፡፡ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፈቃድም ከእግዚአብሔርና ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ ተልኮ ይኽ የመላእክት አለቃ ዮናኤል መልአክ የቊጣ ሰይፍን በመያዝ ንስጥሮስን ገሠፀው፡፡ ያን ጊዜም ንስጥሮስ ከአልጋው ተነሣና ከምድር ላይ ወድቆ፤ አንገቱ ከጀርባው ተጣበቀ፤ ፊቱ ወደ ኋላ፤ ጆሮዎቹም ወደ ፊት፤ ራሱም ወደታች፤ እግሮቹም ወደላይ ኾኑ፡፡ ልሳኑም አንድ ክንድ ያህል ተጎለጎለ፤ ልቡም ጠፋ፡፡ የዐይኑ ብርሃንም ተሠወረና የወይን ስካር እንዳሰከረው ኾነ፡፡ ያን ጊዜም ይኽ ንስጥሮስ በክፉ አሟሟት ሞተና መላእክት ተቀብለው ወደ ሲኦል ጥልቅ ውስጥ ወረወሩት፡፡ ይኽ ኹሉ የኾነው በእውነት አምላክን በወለደች በኹለት ወገን ድንግል በኾነች በእመቤታችን ማርያም ድንግልና ላይ ስለተሳደበና የመላእክት አለቃ ይኽ መልአክ ቅዱስ ዮናኤል በቊጣ ሰይፉ ስለቀሰፈው ነው፡፡ በሰው ላይ የተሳደበ ኹሉ ኀጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይና አምላክን በወለደች በኹለት ወገን ድንግል በኾነች በእመቤታችን ድንግል ማርያም በንጽሕናዋና በድንግልናዋ ላይ የተሳደበ ግን በዚኽ ዓለምም ኾነ በሚመጣውም ዓለም ኀጢአቱ አይሰረይለትም፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ዮናኤል ምልጃና ልመና ኹላችን የጥምቀት ልጆችን ከሁከትና ከክሕደት ዘመን ያድነን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ✝️ ይኽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል ከከመላእክት አለቃ ከጓደኛው ከቅዱስ ፋኑኤል ጋር ከሰማይ የተገኘ ኅብስትንና ከሰማይ የተቀዳ ጽዋን ለክብርት እመቤታችን የመገባት ነው፡፡ ✝️ ይኽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል ቅዱሳንን ከዋሊ በረሓ በአንበሳ ከሚጫነው ከብፁዕ አባ ሳሙኤል የቅድስናው ቦታ ከኾነች አብረንታት ከዋልድባ ገዳም የመጡ ቅዱሳን ከብዙ የሕግ ታቦታት ጋር የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ታቦት ይዘው ወደ ጐረጐር ገዳም እስከ ደረሱ ድረስ የመራቸው ነው፡፡ ✝️  ይኽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል ለሐዋርያው ፊልጶስ ተገልጦለት ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው በበረሓው መንገድ በቀትር ጊዜ ‹‹ተነሥተህ ሒድ›› ብሎ ፊልጶስን ወደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የላከው ነው፡፡ ✝️  ይኽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል በብርሃን ክንፎቹ ፈጽሞ እየበረረ የተሳለ ጦርንና ሰይፍን በመያዝ በዋሻዎችና በዛፎች፤ በምድር ጉድጓድ ውስጥም ለሚኖሩ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ምግባቸውን የሚያመጣላቸው ነው፡፡ ✝️  አምላካችን ኖኅን ከጥፋት ውኃ የጠበቀው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ዮናኤል እጅ ነው፡፡  ✝️  ከጌራራ ምድር ንጉሥ ከአቤሜሌክ እጅ አብርሃምንም ያዳነው እርሱ ነው፡፡ ✝️  ይሥሐቅንም ከተሳለ ሰይፍ (ካራ) ያዳነው እርሱ ነው፡፡ ያዕቆብንም ከወንድሙ ከዔሳው ያዳነው እርሱ ነው፡፡  ✝️  በኮቦር ወንዝ ሳለ ለነቢዩ ሕዝቅኤል ተገልጦለት ምሥጢራትን የነገረው ይኽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል ነው፡፡  ✝️  የጻድቅ አቤልን ነፍስ ወደ ሰማይ ያሳረገው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዮናኤል መልአክ ነው፡ ወደ ጌታ ዙፋን አደረሰውና የገነት ደጃፍ ከሚጠብቅ ከሱራፌል ጋር በገነት እግር ሥር አስቀመጠው፡፡ ✝️  ከዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት አንዱ የኾነ፤ ምሕረትን የሚለምንና የሚማልድ ክቡርና ኀያል የኾነ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የቅዱስ ዮናኤል ስለ ቀናች ኃይማኖት ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ የተሰደዱትንና የተንከራተቱትን፤ በክፉዎች አጋንንት ማሰሪያ የታሰሩትንና በክፉ አገዛዝ የተያዙትን፤ በሰንሰለት የታሰሩትንና ኀላፊና ጠፊ የኾነች ይኽችን ዓለም በመናቅ ከአባታቸው ቤት የወጡትንም የሚረዳቸው እርሱ ነው፡፡ ✝️  የቂሣርያ ሀገር ሰው ለኾነ ኢጣልቄ ለሚሏት የሰጲራ ሕዝብ የመቶ አለቃ ለኾነ ስሙ ቆርኔሌዎስ ለተባለ ሰው በዘጠኝ ሰዓት ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ቅዱሳንን የሚረዳ ይኽ የእግዚአብሔር መልአክ ዮናኤል ተገለጠለትና ወደ እርሱ ገብቶ ‹‹ቆርኔሌዎስ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይኹን! የእግዚአብሔር ሰላም ከአንተ ጋር ይኑር፤ እነሆ ጸሎትህና ምጽዋትህ በጐ ሥራህም ወደ ፈጣሪህ ፊት ዐርጓል፤ በጐ ሥራህን አስቧልና›› ብሎ አበሠረው፡፡ በድጋሚ የመልአኩ የቅዱስ ዮናኤል ምልጃና ልመና ኹላችን የጥምቀት ልጆችን ከሁከትና ከክሕደት ዘመን ያድነን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

About