@mewi.media: "የምሥራቅ ጉራጌና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት በ፪ሺ፲፰ በጀት ዓመት በብፁዕ አባታችን አቡነ ኤጲፋንዮስ በሳል አመራር አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል" (ክቡር ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሰሎሞን አባይነህ ) በ፵፭ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ የምሥራቅ ጉራጌና ማረቆ ሀገረ ስብከት የ፪ሺ፲፰ ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፊት በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሰሎሞን ዐባይነህ በኩል ቀረበ። ++++++++++++++++++ Mewi ሚዲያ ጥቅምት ፬ ቀን ፪ሺ፲፱ ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በ፵፭ኛው (45ኛው) አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የምሥራቅ ጉራጌና ማረቆ ሀገረ ስብከት የ፪ሺ፲፰ ዓ.ም አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅርስ ጥበቃና የማህበራት ማደራጃ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ ሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆችና የመምሪያ ክፍለ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሰሎሞን ዐባይነህ በኩል ቀርቧል:: በዕለቱ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሰሎሞን ዐባይነህ በቀረበው የበጀት ዓመቱ አጠቃላይ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያስረዳው፤ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ በተያዘው በጀት ዓመት በሀገረ ስብከቱ ሥር በሚገኙ ገዳማትና አድባራት በመገኘት በመሠረት ላይ ለሚገኙ ፴፫ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናት አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው በታላላቅ የዓመቱ ክብረ በዓላት ላይ በምሥራቅ ጉራጌና ማረቆ ልዩ ወረዳ በመገኘት ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም በቡታጅራ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሕግ ታራሚዎችን በመጠየቅ ለትንሣኤ በዓል መዋያ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ በቡኢ ሆስፒታል ለሚገኙ ታማሚዎችም ጸሎትና ድጋፍ አድርገዋል። በብፁዕነታቸው መሪነት በቡታጅራ ከተማ የጂ+፪ (G+2) መንበረ ጳጳስና የፓትርያርኩ ማረፊያ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ተባርኮ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኝ ሲሆን፣ የተጠናቀቁ ሦስት አብያተ ክርስቲያናት ተባርከው ቅዳሴ ቤታቸው ሲከበር ለሌሎች ሦስት አዳዲስ ሕንፃዎች ደግሞ የመሠረት ድንጋይ ተኖሯል። ሀገረ ስብከቱ አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚያደርግበት የራሱ ሚዲያ እንዲኖረውም ተደርጓል። በስብከተ ወንጌልና ትምህርት ዘርፍ በበጎ ፈቃደኞች አስተባባሪነት ለ፶፭ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ያልተቋረጠ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ፪፻፶፭መንፈሳዊ ጉባኤያት በተለያዩ በከተማና በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተከታታይ ቀናት የታላቅ አደባባይ ጉባዔ ተካሂዷል። በተሠራው የተቀናጀ አገልጋዮችን የማንቃት ሥራ ፪፻፭፭ አዳዲስ ነፍሳት ተጠምቀው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተጨምረዋል። ተተኪ መምህራንን ለማፍራትም በአኖሁዳድ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ገዳም ለ፵ ካህናትና ዲያቆናት የሁለት ወር ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ በየደረጃው ለሚገኙ አገልጋዮች በሦስት ዙር ሥልጠና ተፈጽሟል። በሰበካ ጉባኤና በሰንበት ትምህርት ቤት በኩል የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ ፴፰ አብያተ ክርስቲያናት አዲስ ምርጫ አከናውነው ወደ ሥራ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፣ ፹፮ አጥቢያዎች አዲሱን የሰንበት ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርት በተግባር ላይ በማዋል ላይ ይገኛሉ። የመማሪያ መጻሕፍትም ተገዝተው ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ተሰራጭተዋል። በመልካም አስተዳደር ረገድ በሀገረ ስብከቱ ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ዕጦት የሰላምና የፍቅር አባት በሆኑት በብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ በሳልና አባታዊ አመራር፣ ትዕግሥትና ጽናት ተወግዶ ሀገረ ስብከቱ ወደተረጋጋ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ ተደርጓል። ችግር ፈጥረው የነበሩ ሠራተኞችም ስህተታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቅ ወደ ሥራ ገበታቸው የተመለሱ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሀገረ ስብከቱ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት ነግሦ የልማት ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛሉ። በአሁን ሰዓት ጉባዔው የሌሎች አህጉረ ስብከቶችን ሪፖርቶች በማዳመጥ ላይ ይገኛል። Mewi ሚዲያ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንተጋለን !! ጥቅምት ፬ ቀን ፪ሺ፲፱ ዓ.ም

መዊዕ ሚዲያ - Mewi Media
መዊዕ ሚዲያ - Mewi Media
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 17 October 2026 04:47:27 GMT
4640
457
6
55

Music

Download

Comments

user9233819931101
user9233819931101 :
እውነት ነው አባታችን እድሜና ጤና ያድልልልኝ
2026-10-17 10:44:15
1
habtamushimekt
ሀብታሙ :
አባታችን እድሜና ፀጋ ያብዛልን
2026-10-17 08:48:15
1
user9233819931101
user9233819931101 :
❤️
2026-10-17 10:44:35
1
eyobgezahagn
ሊቀ ዲያቆናት ኢዮብ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-17 06:03:51
1
.1255590
ፈጣጤ king :
🥰🥰🥰
2026-10-17 09:17:58
1
dawit.miratu4
Dawit mihratu :
💚💚💚
2026-10-17 11:02:38
0
To see more videos from user @mewi.media, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About