@jahmc1: ~መልካሙ ተበጀ በጣም ጎበዝ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጎበዝ አንጋፋ ድምፃዊ ነው! ~በርካታ ተወዳጅ ዘፈኖችና አልበሞች አሉት አሉት ~እኔ በተለይ ቆየት ያሉ ስራዎችን እንደ አዲስ አበጋዙ ሺዎታ ጋ ሆነው "በ1987" የለቀቁት አልበምን በጣም ነው የወደድኩት ደጋግሜም ነው የምሰማው! ~የዘፈኖች ድምፅ ጥራት ይገርመኛል በዛ ላይ የመልካሙ ድምፅ ተጨምር ምስጋና ለአበጋዙ.. ሌላ ታሪክ ነው አልበሙ! ~አልበሙ በውስጡ ፦ ተጫዋች ነች ቸብ ቸብ ፣ ደህና ሁኝ ፣ ልቤ በረሀ ነው ፣ በዕንባ ተለያየን ፣ አንድ አመት ወደድኳት ፣ ነኝ ወይ ላንቺ ክፉ ፣ ታቦት ይመስል ፣ አንቺ ተማሪ ፣ሌላ እንዳይገባበት ፣ ስንቱን አሳለፍነው ፣ እንታረቅ ፣ አልጓጓምና አኩሪ ባህል አለኝ የሚሉ ተወዳጅ ዘፈኖችን ይዟል! ~"ታቦት ይመስል" የሚለውን ዘፈን በጣም የምወደው ዘፈን ነው እኔ! ~የዘፈኑ መነሻ... ~መልካሙ ተበጀ ከአንዲት ወጣት ሴት የከረመ ፍቅር ይዞታል....ከአንድም አመት አልፎ ሶስት አመት የሞላው! ~ታዲያ መልካሙ ሶስት አመት ያስቆጠረ ፍቅር ቢይዘውም ደፍሮ ፍቅሩን አልገለፃላትም....በዙሪያዋ ላይጠፋ ይችላል ግን ፍቅሩን በውስጡ ነው አፍኖ የያዘው! ~እንደ ታቦት ያጅባታል በልቡ ምናልባት አገኛት ይሆን? እያለ እየተመኘ....በአጠቃላይ ለሷ ያለውን ፍቅርና ያለበትን ሁኔታ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል... . . . . መልካሙ ተበጀ ~"ታቦት ይመስል"❤ ~ዘፈኑን መልካሙ ተበጀ እንዲህ ሲል በቆንጆ ድምፁ ይጀምረዋል.... "ታቦት ይመስል ፤ ታቦታ ይመስል ፤ታቦት ይመሰል አጀባት አጀባት....... አገኛት እያለ ልቤ ..ምናልባት ምናልባት" ~ታዲያ በላይኛው ስንኝ ያፈቀራትን ሴት ድንገት ለኔ ብትሆንና ባገኛት ብሎ በልቡ በማሰብ.. ስትወጣ ስትገባ እየጠበቀ ከኋላ ሆኖ ልክ ታቦት ከማደሪያው ወጥቶ ሲሄድና ሲመለስ ታጅቦ እንደሚሸኘው መልካሙም ይቺን ሴት እንደሚያጅባት ይነገርናል! . . . . ~ይቅጥልና " ውበትና ፀባይ አሟልቶ የሰጣት እጅግ ተውባና አምራ ላያት ሁሉ የፍቅር ፀዳል ተላብሳ ስትሄድ...የኔ ልብም ያጅባታል ውበቷን እያሞገሰ ...መንፈሴም አብሯት ነው የሚገሰግሰው...ድንገት ያ የተለኮሰው የፍቅር ደመራ ወደኔ አጋድሎ በእኔ አቅጣጫ ቢወድቅ" ብሎ እየተመኘ...የእሱ እንድትሆን አጥብቆ በመሻት እንዲህ ይላታል ከታች ባለው ስንኝ.... "የፍቅር ደመራ ለኩሳለች እኮ ወደኔ ቢያጋድል የዚያች የደም ገቦ አክሊል እየደፋ ካባ እያለበሰ መንፈሴ በመሉ አብሯት ገሰገሰ ውበትና ፀባይ አሟልቶ የሰጣት ለመፈቀር ነው ወይ እኔኑ ለመርታት" . . . . "እህህህ እንደ ክራላይሶን ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እህህይ እንደ አርብ ስቅለት ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እሆሆይ ከፍቅር መቅደሷ ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እሆሆይ ብታስገባው ገነት ሰዲቅ ሰላም" ~ከላይ ባሉት ስንኞች ደግሞ "እንደ አርብ ዕለት ስቅለት እና እንደ ኪራራይሶን ቀን ስግደት ...እሱም ለፍቅሯ መስገዱን ፣ መንበርከኩን ፣ መሸነፉን ይገለፃል... ስታየው ሲያገኛት ከአንገቱ ጎንበስ ያለ የአክብሮት መገለጫ የሆነ ሰላምታ በማቅረብ ...ፍላጎቱ ሰምሮ ገነት ከሆነው ከፍቅሯ መቅደስ ብታስገባው ይመኛል .....("ሰዲቅ ሰላም " የሚለው ቃል~በሙስሊሙ አማኞች እውነት ወይም ትክክል የሚል ትርጉም ቢኖረውም በዘፈኑ ውስጥ ግን መነጠፍ ፣ መዘርገት ፣ መጎንበስ ፣ እጅ መሰጥትና መስገድ የሚል ትርጓሜ ነው ያለው) . . . . ~ከታች ባሉት ስንኞች ደግሞ መልካሙ የያዘው ፍቅር ከሰሞኑ የጀመረ አልመሆኑን እንደውም አምናም ከዛ በፊት የነበረ የፍቅር ስሜት መሆኑን...ከታች አምናው አምና ተሽሎኛል ፍቅሯ ሊለቀኝ ነው ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም...ለካ ውስጥ ውስጡን ተዳፍኖ ኖሯል...ዘንድሮ ይባስ እንደባሰበት ደግሞ እንዲህ ይገልፃል... ከታቻምናው አምና ተሻላኝ ብየ ነበር ድንገት ሲመስለኝ ተቃጠለ ተዳፍኖ ኑሮ እየባሳ መጣ ዘንድሮ . . . ~ይቀጥልና ከታች ሰልፍ እንደሚያጅብ ማርሽ ባንድ አጃቢ አድርጋ ከኋላ እያስከተለችው በናፍቆቷና በፍቅሯ ከጥልቁ ገሃነም እንደገባ ሰው እየነደደ እየተቃጠለ ስላለ...ብታፀድቀው የፈለገውን ፍቅሯን ብትለግሰው በማሰብ ካአንጀቱ ሰገደ ፤ ከልቡ ተመኘ ...እስከሄደችበት ጥግ ድረስ አብሯት ፍቅሯን ብሎ ልቡ መዝለቁንና መሄዱን እንዲህ ሲል ይገልፃል.. "እንደ ሰልፈኛ ማርሽ ፍቅሯን እያጓለ ታስከትለዋለች ከኋላ ኋላ ኋላ ከናፍቆት ጀሃነም ገብቶ እየነደደ ብታፀድቀው ብሎ ካንጀቱ ሰገድ በድሬ አሽሞንሙን አልቦ እያጠለቀ እስከ እየሩሳሌም ሄደ አብሯት ዘለቀ" . . . "እህህ እንደ ሁዳዴ ፆም ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እሆሆይ በዱአ ምርቃት ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እሆሆ እንደ መናኝ ፀሎት ሰዲቅ ሰላም ይላታል ሰዲቅ ሰላም እሆሆይ ብታስገባው ጀነት ሰዲቅ ሰላም" ~ከላይ ባለው ስንኝ ደግሞ እንደ ሁዳዴ ፆም በረከት ፣ እንደ ዱኣ ምርቃትና እንደ መናኝ ፀሎት ዋጋቸው ተቆጥሮ ገነት እንደሚያስገቡት... ልክ እንደዛ ሁሉ ልጅቱ ልቡን ከሚነድበት ከሚቃጠልበት ስቃይ አውጥታ ...ረፍት ወደሆነውና ገነት መስሎ ወደታየው ወደሷ ፍቅር እንድታስገባው ይመኛል! ከታቻምናው አምና ተሻላኝ ብየ ነበር ድንገት ሲመስለኝ ተቃጠለ ተዳፍኖ ኑሮ እየባሳ መጣ ዘንድሮ . . . "እሷ ጅንን ያለ እንደ አገር አርበኛ እኔ እንደ ሰላባ የፍቅር ምርኮኛ አንቺ እመ ፍቅር የፍቅር መድህን ኧረ እንዴት ኧረ እንዴት ታደርጊኝ ይሆን አዱኛ ቢኖርም የጉድ ነው የጉድ ነው በፍቅር በመውደድ ለካ ሰው ለማኝ ነው" ~በመጨረሻም "እሷ እንደ ሀገር አርበኛ የተጀነነች እኔ ደግሞ በፍቅሯ የተማረኩ ምርኮኛ ነኝ...አንቺ የፍቅር መድህን እባክሽ አታሰቃይኝ...ሰው ለካ ሀብታምና ባለ ፀጋ ቢሆንም በፍቅርና በመውደድ ደካማ ነው....እሱን ለማግኘትም መለመኑ አይቀርም" ይለናል ሀብትን ፍቅርን እንደማይገዛ እየነገረን! . . ግጥምና ዜማ ~ፅጌ ገ/አምላክ ቅንብር ~አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ ✍️ Jah Mc #Jahmc1 #melkamutebeje #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #music @gigi_shebabaw fans @Ba mu
Jah Mc
Region: ET
Saturday 17 October 2026 07:17:21 GMT
Music
Download
Comments
Ba mu :
መልካሙ ተበጀ ዜማን የመንከባከብ ብቃቱ ልዩነው
2026-10-17 07:56:45
2
ዕድል2112🦅 :
2026-10-17 07:34:54
1
addika :
2026-10-17 08:45:15
0
መንገደኛዉ :
እዉቀት ቢኖረዉማ አያ ሙሌ የሰራለትን ግጥም ህዝቡ አይገባዉም ብሎ አልሰራም አይልም ነበር! ?
2026-10-17 09:06:02
1
paparazzi :
ye abegazin ayimeslim gn kinbru
2026-10-17 09:29:37
0
Hope :
👏👏👏
2026-10-17 07:20:06
1
To see more videos from user @jahmc1, please go to the Tikwm
homepage.