@serawite_gedeon: • ካህኑን ፍቱአቸው ‼ • ጀግናውን ውባንተንም አታሰድቡ "…የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምሕረት በደቡብ ጎንደር በሚገኙ ፋኖዎች አማካኝነት መታገታቸው ተሰምቷል። ወፎቼም ይሄንኑ አረጋግጠዋል። ወፎቼንም የመታሰራቸውን ምክንያትም አረጋግጧል እንድትመጣም ልኬያት ነበር። እሷም አረጋግጧል መጥታለች። "…ሥራስኪያጁን ያሳሰራቸው ቂም በቀል ነው። እዚያ ላይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የጄነራል ውባንተን ልጆች እስከአሁን የተከበረ ስም እና አይደፈሬ ማንነት አፈር ደቼ ለማብላት፣ ጭቃም ለመቀባት የተወጠነ ሴራ እንደሆነ ነው ወፌ ተረድታ የመጣችው። "…ፀቡ በግል የተፈጸመ ነው። ቄስ ይባቤ አየለ ፋኖ ሆኖ የእነ ውባንተን ልጆች እነ ፋኖ አርበኛ ተመስገን ውባንተን ከመቀላቀሉ በፊት በቤተ ክህነት በሥራ ላይ በነበረ ጊዜ ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር ተቀያይመው ነበር። እናም ያ ቂም አድጎ ፋኖ ቄስ ይባቤ አየለ አሁን ፋኖ ሆኖ ፈላጭ ቆራጭ ሲሆን ቀን ጠብቆ የሌለ የክስ ድሪቶ ደርቶ ሊቀ ካሕኑ እንዲታሠሩ አድርጓል። ይሄ ፍፁም ሕገወጥ ድርጊት ብቻ ሳይሆን አደገኛ ወንጀልም ነው። ፋኖነት ቂምበቀል መወጫ መድረክ አይደለም። ይሄ ከወዲሁ ሊታወቅ ይገባል። "…ታይሚንጉ ደግሞ ትላለች ወፌ፣ ጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊው የሰበካ ጉባኤ ጠቅላላ ስብሰባ በሚደረግበት፣ ከመላው ዓለም የሚመጡ ካህናት እና ጳጳሳት ለስብሰባ በሚቀመጡበት፣ ቀጥሎ ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በሚደረግበት ሰዓት ጠብቀው ነው ያፈኗቸው። ይሄ የሚያመጣውን የፖለቲካ ኪሣራ ጠንቅቀው የሚያውቁ የዐማራ ፋኖ ጠላቶች ናቸው ይሄን አደገኛ ቁማር የተጫወቱት። "…ደግነቱ ሊቀ ካህኑን ያስያዙት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ ግለሰቡች፣ ካህናት ጭምር ስምዝርዝራቸው ደርሶኛል። ለውባንተ ልጆች ካህኑ ከተያዙ በኋላ የሰጧቸው መመሪያ "በአስቸኳይ አስወግዱት" ቶሎ ይገደል" የሚል ጥድፊያ የተሞላበት ከወዳጅ የማይጠበቅ ውትወታ ነበር የቀረበላቸው። ነገር ግን እነ ፋኖ ተመስገን እና ጓዶቹ "ይሄ ነገር ምንድነው እንዲህ የተጣደፈው? ቆይ ይመርመሩ፣ ነገርየውም ይዋል ይደር በማለት ነው እስከ አሁንም ሊቀ ካህኑ በሕይወት የቆዩት። "…ታላላቅ የገዳማት እና አድባራት አበምኔቶች፣ የጉባኤ መምሕራን በሙሉ ወደ 30 የሚጠጉ አባቶች ለሽምግልና ወደ አርበኞቹ ዘንድ የሄዱ ሲሆን፣ ይሄ ቄስ ግን ሽማግሌዎቹን አበሻቅጦ ከመንገድ ሊመልስ እንደነበረ ሁላ ነው ወፌ ሰምታ የነገረችኝ። "በቃ የእሱ ነገር አልቋል፣ አይፈታም፣ ለምን መጣችሁ? ለምን ትደክማላችሁ? እያለ ሲያጓራ ነበርም ተብሏል። እና እኔ ብሆን ይሄን ሃማ የሆነ ሰው ነበር አስሬ የምመመረምረው። "…አሁን ሊቀ ካህኑ በሚፈለገው ፍጥነት ባለመገደላቸው፣ የሀገር ሽማግሌዎችም ነቅለው በመሄድ በሽምግልና ከፋኖዎች ጋር መቀመጣቸው ያበሳጨው እና ያስፈራው የዐማራ ብልፅግና በደቡብ ጎንደር የመሸገው ተረፈ ወያኔ ሕወሓት በአካል የሆነው ቡድን እየተወራጨ ነው። እናም ነገ በመላው ጎንደር ሕዝቡ በግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ አገዛዙ አዟል። "…የግዳጅ ሰልፉም የታወቀ ነው የምትለኝ ወፌ። የግዳጅ ሰልፉ አንደኛውና ዋነኛው ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል እና ዳይ ጉዞ ወደ አሰብ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ፋኖ ሃይማኖታችንን እያረከሰ፣ የሃይማኖት አባቶቻችንን እየገደለ፣ እያገተ" ነውና በአስቸኳይ እንዲህና እንዲህ ይደረግልን የሚል እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ፌክ የመንግሥት ፋኖዎች በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ ሕዝቡን በማስመረራቸው ሕዝቡ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርግ አስገድደውታል። "…እስከዛሬ በንፅሕናው የሚታወቀው የእነ ጀነራል ውባንተ፣ የእነ ሳሚ ባለድል፣ የእነ ውባንተ ልጆች በመጨረሻ ሰዓት ማኖ ሊያስነኳቸው ቢሞክሩም ሳይቸኩሉ፣ ይገደል፣ ይገደል፣ ይሰቀል የሚለውን የሰቃልያነ ክርስቶሶችን ድምጽም ሳይሰሙ፣ እስከዘሁን ይዘው ማቆየታቸውም፣ ግራ ቀኝ ሰምተው ካህኑንም ራቅ ወዳለ ቦታ ማሸጋገራቸው አደጋ እንዳይደርስበት ጥንቃቄ ማድረጋቸው የሚያስመሰግናቸው ነው ባይ ነኝ። • የእኔ ምክር… "…የጄነራል ውባንተ ልጅ ተመስገን ውባንተ እና ጓዶቹ እኚህን አባት በአስቸኳይ ትለቋቸው ዘንድ በትህትና ዝቅ ብዬ እግራችሁ ላይ ወድቄ እማፀናችኋለሁ። እኔ በዚህ መጠን እንዲህ ያለ ጥያቄ አቅርቤ አላውቅም። ይሄ የመጀመሪያዬ ነው። ብዙ ነገር ነው የምታበላሹት። የሴራ ፖለቲካን በሩን ዝጉበት። ጠላትንም አሳፍሩ። በሃይማኖት ጉዳይ እጃችሁን አታስገቡ። ተቆጠቡ፣ ተጠንቀቁም። ቶሎ ፍቱአቸውና የነገው ሰልፍ የአብይ ጎንደሬ፣ አማቺዝሙ፣ የሰሊጥ ነጋዴው ቡድን እንደፈረደበት "የዛሬ 8 ዓመት ጨርቁን ጥሎ፣ አቅሉን ስቶ፣ መሰንቆውን እየገዘገዘ፣ ትከሻው እስኪወልቅ እስክስታውን እየተርገፈገፈ፣ የኤርትራን እና የኢትዮጵያን ባንዲራ፣ የኢሳያስ አፈውርቂን እና የአቢይ አሕመድን ፎቶ ይዞ ሲርገፈገፍ የከረመው ብአዴን አሁን ደግሞ አሰብ እንግባ፣ ኢሳይያስ ይደምሰስ፣ አቢይ ዓማታችን ሺ ዓመት ይንገስ ብለው ሰልፍ ይውጡ። • በመጥፎ አጀንዳ አትሁኑ ‼ • በሃይማኖት ቀልድ የለም ካሕኑን ፍቱአቸው ‼ "…ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።
ሠራዊተ ጌዴዮን
Region: ET
Saturday 17 October 2026 16:10:19 GMT
Music
Download
Comments
DXN CHERNET :
እግዚአብሔር ፍረድ
2026-10-18 09:02:59
0
temesgen :
አረ ምን አደረጉ ይፈቱ
2026-10-18 10:15:06
0
user6716071163991 :
አረ ለምን አባቶችን ማንገላታት ፍቷቸው🥰🥰🥰
2026-10-18 09:03:47
0
ቤተ ቅዱሳን :
ፍቷቸው ፍቷቸው ጥሩ አደለም
2026-10-17 18:53:48
0
❤❤❤ :
እውነተኛ ፍርድ
2026-10-17 19:51:36
0
አባይነሽ ሲሳይ :
ለምንአባቶችንግን
2026-10-17 17:39:07
0
sewasew :
የሰራው ካለ
2026-10-18 05:17:36
0
kidest :
ፈጣሪ ፍርድ ስጥ
2026-10-17 18:20:22
0
M.N/A.N018 :
ገና ዛሬ በአይናችን በእምነት በማተባችን መጣችሁ እዲታገት ትዛዝ የሰጠው አካል በእርግጠኝነት ከብልፅግና ተልኮ ተቀብሎ መሆን አለበት ይህ ደግሞ ህዝቡ በፋኖ ላይ ጥላቻ እዴያሣድር ታሥቦ የተሰራ ሴራ እደሆነ ግልፅ ነው።
2026-10-17 20:24:08
0
Aba wldekirkos :
ታላቁን የቤተክርስቲያን ልጅ ሊቀ ስዩማን ምሕረትን እንዲያዙ እንዲገላቱ ያደረገው ይባቤ አየለ ነዉ ። ከወላጅ እናታቸው ለቅሶ እንኳ ቁመው አልቅሰው ዳዊት ደግመው እንዳይቀብሯት ነዉ ያደረገው ።እግዚአብሔር ይፍረድ በእውነት ።
2026-10-17 18:00:24
1
ለመኑ እነግር ሀዘነ ልብየ :
ስራው ያውጣው😁😁😁😁😁
2026-10-18 04:12:49
0
Mikiyas Emre :
የከተማ ልጅ
2026-10-18 00:35:05
0
ዋርካው :
አፋን ለምን ከፈተ
2026-10-18 03:16:26
0
habtemaryamgenberu3 :
ወገን ከሸኔና ከእንዲህ አይነቱ ፋኖ ማን ይሻላል?ሸኔ ግን ወገኖቹን አይነካም የኛ ደግሞ እንዲህ አይይይይይ
2026-10-17 20:20:01
0
mulat yebata lij :
የሰራው ስራ ከሌለው አይነኩትም ይለቁታል
2026-10-18 09:02:33
0
love is war :
😁😁😁😁😁😁😁
2026-10-17 19:05:03
0
To see more videos from user @serawite_gedeon, please go to the Tikwm
homepage.