@the.ethiopian.daily: ❓ቢቢሲ(BBC) የአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመቃወም  ለመጨረስ እየተማጸኑ ያደረጉት ንግግር ነበር። በወቅቱ የተሰማዎት ምን ነበር? 🗣አቶ ገዱ፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጊዜ ሲያውጅ እና ያንን ወደ ፓርላማው ሊያጸድቅ ይዞ ሲቀርብ በሕዝብ ላይ የጅምላ ሞት እንደታወጀ አድርጌ ነበር የተመለከትኩት። ከዚያ ውጭ ላደርግ የምችለው ነገር አልነበረኝም፤ ማስቀረት አልችልም። ❓ቢቢሲ(BBC): ከምክር ቤቱ እንደወጡ ማንን ነበር ያገኙት? 🗣አቶ ገዱ፡ እዚያው ፓርላማው ወስጥ ተሳታፊ ናቸው እና "ክልሉ እንዲፈርስ ነው ወይ የምትፈልገው" ያሉኝ ሰዎች አሉ። እኔ ክልሉ በወታደራዊ መንገድ ይጠገናል ብዬ አላስብም። የእኔ ጥያቄ የነበረው መከላከያ ከክልሉ ይውጣ ወይም ወደ ካምፑ ይግባ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ንግግር ተደርጎ ይፈታ የሚል ነበር። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ በምክር ቤቱ መረር ብለው ሲናገሩ ይህ ይመጣብኛል የሚል ስጋት አልነበረዎትም? 🗣አቶ ገዱ፡ አንድ ምክንያት እየተፈለገልኝ እንጂ የሆነ ነገር ልደረግ እንደምችል ግምቱ ነበረኝ። እኔም ራሴን አሳምኛለሁ። እናም ምክር ቤቱ ውስጥ ለመናገር ሳስብ ግድያን ጨምሮ እስር ወይም ሌላ ነገር ሊመጣ ይችላል ብዬ ራሴን አሳምኘ ነው የተናገርኩት። የሚመጣውን መቀበል የህሊና እረፍት ነው ብዬ ነበር የማስበው። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ የቁም እስር ውስጥ የቆዩት በተፈጠረበዎት ስጋት እንቅስቃሴዎን ስለገደቡ ወይስ መንግሥት እንዳይንቀሳቀሱ ስለከለከለዎት? 🗣አቶ ገዱ፡ ከቤቴ ግራ እና ቀኝ ሁለት መኪናዎች ሁልጊዜ ይመጣሉ። የፀጥታ ሰዎችን እናውቃቸዋለን፤ ይመላለሳሉ። ዋናው ፍላጎታቸው ከሰዎች ጋር እንዳልገናኝ ማድረግ ነው እንጂ እንሰርህ ቢሉ፣ እንግደልህ ቢሉ በእጃቸው ነው። ማን ከልካይ አላቸው። ሕግ የለ፤ ሥርዓት የለ፤ በእኔ ምክንያት አንድ ነገር ከሚሆኑ ብዬ ጠባቂዎቼንም ወዲያው ነበር ያሰናበትኳቸው። አምስት ስድስት ወር በዚህ ሁኔታ ቆየሁ። ❓ቢቢሲ(BBC) ፡ እንዴት ከአገር ሊወጡ ቻሉ? 🗣አቶ ገዱ፡ ከአገር የወጣሁት ሌሊት ነው። አሁን ልነግርሽ በማልችልበት ሁኔታ ሰዎች አግዘውኛል። ❓ቢቢሲ(BBC) ፡ የስደት ሕይወት እንዴት ነው አሁን? 🗣አቶ ገዱ፡ ስደት ስደት ነው። እንደ እኔ ያለ በተለይ ዕድሜ ከፍ እያለ በሚሄድበት ጊዜ ስደትን ለማንም የማልመኘው ነገር ነው። በፖለቲካው ዘርፍ አገር እና ኅብረተሰብን እለውጣለሁ ብዬ የኖርኩ ሰው ለዚህ መዳረጌ የሚያሳዝን ገጽታ አለው። በሌላ መልኩ ደግሞ የእኔ አኗኗር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ከማንኛውም ሰው የተሻለ ነው። አሜሪካ የነጻነት አገር ነው። ሕግ እና ሥርዓቱን ተከትለሽ እስከኖርሽ ድረስ፣ እዚህ አገር ከሚኖር ሰው ያልተለየ ኑሮ እየኖርኩ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው፣ ባለሥልጣናትም ቢሆኑ ሁሉም ስጋት አለባቸው፤ ሃብታምም ድሃም በስጋት ውስጥ ነው ያለው። እናም እግዚአብሔር ይመስገን በጥሩ ሁኔታ ነው ያለሁት። ❓ቢቢሲ(BBC) ፡ በቅርቡ በፓርኪንግ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚያሳይ ቪዲዮ ተሠራጭቶ ነበር።  እንዴት ወደዚህ ሥራ ተሰማሩ? 🗣አቶ ገዱ፡ ወደ እዚህ አገር ስመጣ ባዶ እጄን ነበር የመጣሁት። ምንም ነገር አልነበረኝም። ለመኖር የሚያስፈልገኝን ሠርቼ ማግኘት ነበረብኝ። ይኼ ሥራ ደግሞ ለእኔ በወቅቱ ያገኘሁት ሥራ ነው። ይህ ብቻም ሳይሆን በተወሰነ ደረጃ ኢትዮጵያ ከምኖረው በተሻለ መንገድ እንድኖር እያደረገኝ ያለ ነው። በሌላ በኩል ሰው የተለያየ ነገር ሊያነሳ ይችላል። የአማራ ክልልን በምመራበት ጊዜ በቢሊዮን ብር በጀት የሚመድብ ክልል ነው። የውጭ ጉዳይም ትልቅ መሥሪያ ቤት ነው፤ የአገር ሃብት ጭምር የሚያንቀሳቅስ ነው። ሆኖም እነዚህ ሁሉ ለእኔ የተመደቡ ገንዘቦች አይደሉም። ደመወዝተኛ ነኝ። ስደተኛ እሆናለሁ ብዬም አስቤ አላውቅም። ከሕዝብ ሃብት ወስጄ ኑሮዬን አሻሽላለሁ ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም። ሰው ላያምን ይችላል። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ ለውጡ ሲመጣ ብዙ ተስፋ ነበረ። ለዚህ ለውጥ መምጣት 'ቲም ለማ' በዋናነት ይጠቀሳል። አሁን እርስዎ በስደት ነው ያሉት። አቶ ለማም ዝምታን መርጠዋል። ያንን ቲም የሰበረው ምንድን ነው? 🗣አቶ ገዱ፡ ያ ለውጥ የመጣው በጥቂት ሰዎች አይደለም። የሕዝብ ፍላጎት የወለደው ነው። የተወሰኑ ሰዎች የዚያ ለውጥ መሪዎች ነበርን ብዬ አልወስደም። ያ ስህተት ነበር ባይ ነኝ። በኋላ በውጤቱም ስንመለከተው ያ እንዳልሆነ አይተነዋል። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ አሁን ከአቶ ለማ ጋር ትገናኛላችሁ? 🗣አቶ ገዱ፡ እንዲሁ አልፎ በስልክ እንገናኛለን። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ በአገሪቷ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ነገሮች አሉ? 🗣አቶ ገዱ፡ አይ አልተነጋገርንም። አሁን እሱ ብዙም ፍላጎት ስለሌለው ከሰላምታ በዘለለ ወደ ፖለቲካ አጀንዳ ውስጥ ብዙም አንገባም። 🗣ቢቢሲ(BBC)፡ ከትግራይ ጦርነት በኋላ እርስዎ የተቃወሙት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ፣ ሲመሩት የነበረው የአማራ ክልል ግጭት ውስጥ ከገባ ሦስት ዓመቱን ደፍኗል። ግጭቱ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት እያስከተለ ነው። እነዚህን ሁለት ክልሎች እንዲህ ያለ ቀውስ ውስጥ የከተታቸው ምንድን ነው? 🗣አቶ ገዱ፡ በትግራይም፤ በአማራም ያለው ሁኔታ በሰላማዊ ውይይት የማይፈታ ችግር አይደለም። በድርድር፣ በንግግር መፍታት የሚቻል ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ያሉበት ነው፤ መፈታት የሚችል ነው። ነገር ግን አገዛዙ በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን ለመፍታት ዝግጁነት የለውም። በጦርነት አጋጣሚውን ተጠቅሞ አካባቢውን ማድቀቅ ነው የሚፈልገው። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ መንግሥት በአገሪቷ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ በተደጋጋሚ ጥሪ ያቀርባል እኮ። 🗣አቶ ገዱ፡ ምክንያት አለን ብሎ ለትግል የወጣን ኃይል እንዴት ብሎ ነው እጅ ስጡ የሚባለው። እጅ ስጡኝ እና የእኔን ተቀብላችሁ በሰላም ኑሩ ነው የሚላቸው። ያነሱትን ፖለቲካዊ ጥያቄ ለመፍታት የሚያስችል የድርድር እና የሰላማዊ ውይይት ሃሳብ የለውም። 'ተውትና ኑ ነው'፤ እንደዚያ ደግሞ ሊሆን የሚችል አይደለም። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ ከዚህ ቀደም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሥራትዎ እንደሚያፍሩበት እና እንደሚያዝኑበት ገልጸዋል? 🗣አቶ ገዱ፡ እኔ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መሥራቴ በፖለቲካ ታሪኬ የማዝንበትም፣ የማፍርበትም ነው። ምክንያቴም ያ ለውጥ መቀልበሱ እና ለውጡ ለመጥፎ ዓላማ መዋሉም ብቻ አይደለም። ለአገር መሪነት የማይበቃ ኃይል፣ አገርን የሚያፈርስ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አሁን ላለው ምስቅልቅል የዳረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የተወሰነ ጊዜም ቢሆን መሥራቴ ያሳፍረኛል። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣኑን የሚቆጣጠርበት፣ ሲፈልግ የሚሽርበት፣ ሲፈልግ የሚያወርድበት ተቋማዊ የሆነ ሥርዓት መኖር አለበት ብዬ አምናለሁ። ❓ቢቢሲ(BBC)፡ ከዚህ በኋላ የፖለቲካ ሃሳብዎን እንዴት ነው ማሳካት የሚፈልጉት? 🗣አቶ ገዱ: ለጊዜው የማደርገው ይጠቅማል ብዬ የማስበውን የፖለቲካ ሃሳቤን ማጋራት ነው፤ ነገር ግን ፓርቲ ማቋቋምም ሆነ ፓርቲ ውስጥ የመግባት ሃሳብ የለኝም #gedu_abdargachew #fyp #viral

ኢትዮጵያ ዛሬ Ethiopia Today 🇪🇹
ኢትዮጵያ ዛሬ Ethiopia Today 🇪🇹
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 18 October 2026 05:40:12 GMT
25761
824
15
510

Music

Download

Comments

the.ethiopian.daily
ኢትዮጵያ ዛሬ Ethiopia Today 🇪🇹 :
ጠላት ከሩቅ አይመጣም ማለት ይሄ ነው🤔🤔🤔
2026-10-18 05:42:25
8
user7771016051113
Menelik :
አይይ አብይ...
2026-10-19 01:59:50
4
lalew_yichemerewal
ላለው ይጨመረዋል🤴 :
ቢቢሲ(BBC) ፡ እንዴት ከአገር ሊወጡ ቻሉ? አቶ ገዱ፡ ከአገር የወጣሁት ሌሊት ነው። አሁን ልነግርሽ በማልችልበት ሁኔታ ሰዎች አግዘውኛል።
2026-10-18 05:56:08
10
magna8947
Magna :
@1
2026-10-18 21:42:06
3
myviewonevents
MyViewOnEvents :
ቢቢሲ(BBC)፡ መንግሥት በአገሪቷ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ በተደጋጋሚ ጥሪ ያቀርባል እኮ። አቶ ገዱ፡ ምክንያት አለን ብሎ ለትግል የወጣን ኃይል እንዴት ብሎ ነው እጅ ስጡ የሚባለው። እጅ ስጡኝ እና የእኔን ተቀብላችሁ በሰላም ኑሩ ነው የሚላቸው። ያነሱትን ፖለቲካዊ ጥያቄ ለመፍታት የሚያስችል የድርድር እና የሰላማዊ ውይይት ሃሳብ የለውም። 'ተውትና ኑ ነው'፤ እንደዚያ ደግሞ ሊሆን የሚችል አይደለም። ለሰላም ምንም ዓይነት ዝግጁነት የሌለው አገዛዝ እንደሆነ ነው በተግባር እየታየ ያለው።
2026-10-18 05:48:28
7
cat.world828
Cat.world :
ቢቢሲ(BBC)፡ ከዚህ ቀደም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሥራትዎ እንደሚያፍሩበት እና እንደሚያዝኑበት ገልጸዋል? አቶ ገዱ፡ እኔ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መሥራቴ በፖለቲካ ታሪኬ የማዝንበትም፣ የማፍርበትም ነው ብያለሁ። ምክንያቴም ያ ለውጥ መቀልበሱ እና ለውጡ ለመጥፎ ዓላማ መዋሉም ብቻ አይደለም። ለአገር መሪነት የማይበቃ ኃይል፣ አገርን የሚያፈርስ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አሁን ላለው ምስቅልቅል የዳረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የተወሰነ ጊዜም ቢሆን መሥራቴ ያሳፍረኛል። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣኑን የሚቆጣጠርበት፣ ሲፈልግ የሚሽርበት፣ ሲፈልግ የሚያወርድበት ተቋማዊ የሆነ ሥርዓት መኖር አለበት ብዬ አምናለሁ። አንድ ግለሰብ ሥልጣኑን ተቆጣጥሮ የፈለገውን የሚያደርግበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዳግም ላይመለስ በሚያደርግ መንገድ መዘጋት አለበት ብዬ አምናለሁ።
2026-10-18 10:05:51
10
abeti63
Abenet :
❤️❤️❤️
2026-10-18 08:19:22
5
cat.world828
Cat.world :
🤔🤔🤔🤔🤔
2026-10-18 06:01:38
5
cat.world828
Cat.world :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-18 13:39:40
5
gebremedhinn
አነ ዘ ክርስቶስ🙏🙏🙏 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-18 05:43:56
5
mubarek6533
Mubarek :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-18 13:12:05
4
endeshawkebede7
Endeshaw Kebede :
🥺
2026-10-18 17:05:06
4
To see more videos from user @the.ethiopian.daily, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

কি রাগ করলেন..? 🙂 Maksudnya baju mahal kebesaran 2. *Warna gelap & netral*: Hitam, navy, abu, olive = atau tegas 3. *Rapi dari ujung rambut*: Rambut, kuku, sepatu bersih. Berantakab = wibawa drop 4. *Jangan kebanyakan aksesoris*: 1 jam tangan cukup ### *Hashtag #BadDay Edition* kalau mau post OOTD pas lagi bad day rapi tetep berwaibawa: #BerwibawaDuluBadDayKemudian #OutfitTagas #CleanLook #MenlnBlack ` Mau dijadiin versi nongkrong, kondangan, atau kampus? Kasih tau aja acaranya, biar ku-racikin yang pas" width="135" height="240">
কি রাগ করলেন..? 🙂 Maksudnya "outfit cowok berwibawa" buat ngatasin _bad day_ ya?😎 Biar tetep keliatan tegas + pede walau lagi _bad mood_, kuncinya: simpel, rapi, dan warnanya netral. Outfit yang berwibawa = bikin orang auto segan. ### *3 Formula Outfit Cowok Berwibawa Anti Bad Day* *1. Smart Casual CEO Mode* Buat kuliah, kerja, atau nongkrong tapi tetep disegani - *Atasan*: Kemeja oxford polos warna navy, hitam, atau putih. Gulung lengan dikit. - *Bawahan*: Celana chino/ankle pants warna khaki, charcoal, atau hitam. No sobek-sobek. - *Sepatu*: Loafers, chalsea boots, atau sneakers putih bersih. - *Extra*: Jam tangan kulit/steel + kacamata hitam. *Vibes*: Tenang tapi dominan. Bad day langsung minggir. *2. Monokrom Minimalist* Paling gampang tapi efeknya kuat - *Atasan*: Kaos crew neck/henley hitam fit di badan jangan kebesaran - *Bawahan*: Celana bahan hitam atau jeans black wash slim fit - *Outer*: Overshirt atau chore jacket warna senada - *Sepatu*: Boots atau sneakers full black *Vibes*: Misterius, fokus, nggak banyak drama. 3* Old Money Clean Look* Keliatan mahal tanpa logo gede - *Atasan*: Polo shirt rapi atau kemeja linen warna earth tone: olive, cream, mocca - *Bawaham*: Celana bahan steaight cut warna beige/off-white - *Sepatu*: White sneakers premium atau penny loafers - *Extra*: lkat pinggang kulit, rambut klimis rapi *Vibes*: Dewasa, berkelas, bad day jadi nggak berani ganggu, ### *Kunci Berwibawa Biar Bad Day kalah:* 1. *Fit is king*: Baju yang pas di badan > baju mahal kebesaran 2. *Warna gelap & netral*: Hitam, navy, abu, olive = atau tegas 3. *Rapi dari ujung rambut*: Rambut, kuku, sepatu bersih. Berantakab = wibawa drop 4. *Jangan kebanyakan aksesoris*: 1 jam tangan cukup ### *Hashtag #BadDay Edition* kalau mau post OOTD pas lagi bad day rapi tetep berwaibawa: #BerwibawaDuluBadDayKemudian #OutfitTagas #CleanLook #MenlnBlack ` Mau dijadiin versi nongkrong, kondangan, atau kampus? Kasih tau aja acaranya, biar ku-racikin yang pas

About