@bellmvlxart: Sube una foto para crear el video. Mira el mismo video. La plantilla en la esquina inferior izquierda está lista para usar. Sube una foto para crear contenido. Basta con subir una foto para crear un video completamente idéntico. Solo sube una foto y podrás hacer una copia exacta del video. #capcut #capcutpioneer

Dawn
Dawn
Open In TikTok:
Region: US
Monday 19 October 2026 14:28:33 GMT
36
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @bellmvlxart, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

እንደ መዳኒት ፋርማሲ ላይ ቢሸጡ ከምላቸው ዘፈኖች አንዱ ነው!❤ ~ዘፈኑ ለኔ ከፍቅርአዲስ ስራዎች ውስጥ የፈለኩትን ያህል ብደጋግመው የማይሰለችኝ ሁሌ እንደ አዲስ የምሰማው በጣም የምወደው ዘፈን ነው! ~በአንድ ሙዚቃ ላይ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አንዴ ብቻ ሊገናኙ የሚችሉ 4 ፈርጦች አንድ ላይ ጥበባቸውን አሳርፈው የሰሩት ሙዚቃ ነው! (በድምፅ ፍቅርአዲስ ፣ አበበ ብርሃኔ በዜማ  ፣ ይልማ ገ/አብ በግጥም ፣ ኤሊያስ መልካ በቅንብር ) ~ዘፈኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትሰሙት አንዴ በሙዚቃው ግጥምና ዜማ ፤ አንዴ ደግሞ በፍቅራ አዲስ ተሰርቃራቂ ድምፅ ፤ አንዴ ደግሞ  በኤልያስ መልካ የሚገርም ቅንብር እየተገረማችሁ ዥዋዥዌ ውስጥ ነው የምትገቡት በአድናቆት! ~ትዝታ ባይኖርህም ይሄን ዘፈን ስትሰማ ተገደህ ብዙ ትዝታ ይኖረህና ወደ ኋላ ትነጉዳለህ! ~ዘፈኑን ስትሰመው ብዙ ስህተቶችህ ብዙ ነገሮችህ ትዝ ይሉህና
እንደ መዳኒት ፋርማሲ ላይ ቢሸጡ ከምላቸው ዘፈኖች አንዱ ነው!❤ ~ዘፈኑ ለኔ ከፍቅርአዲስ ስራዎች ውስጥ የፈለኩትን ያህል ብደጋግመው የማይሰለችኝ ሁሌ እንደ አዲስ የምሰማው በጣም የምወደው ዘፈን ነው! ~በአንድ ሙዚቃ ላይ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አንዴ ብቻ ሊገናኙ የሚችሉ 4 ፈርጦች አንድ ላይ ጥበባቸውን አሳርፈው የሰሩት ሙዚቃ ነው! (በድምፅ ፍቅርአዲስ ፣ አበበ ብርሃኔ በዜማ ፣ ይልማ ገ/አብ በግጥም ፣ ኤሊያስ መልካ በቅንብር ) ~ዘፈኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትሰሙት አንዴ በሙዚቃው ግጥምና ዜማ ፤ አንዴ ደግሞ በፍቅራ አዲስ ተሰርቃራቂ ድምፅ ፤ አንዴ ደግሞ በኤልያስ መልካ የሚገርም ቅንብር እየተገረማችሁ ዥዋዥዌ ውስጥ ነው የምትገቡት በአድናቆት! ~ትዝታ ባይኖርህም ይሄን ዘፈን ስትሰማ ተገደህ ብዙ ትዝታ ይኖረህና ወደ ኋላ ትነጉዳለህ! ~ዘፈኑን ስትሰመው ብዙ ስህተቶችህ ብዙ ነገሮችህ ትዝ ይሉህና "ምን አለ ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ ቢቻልና ብዙ ስህተቶችን ባስተካከልኳቸው "ያስብልሀል ~ይሄ ዘፈን ብዙ የማንተዋወቅ ሰዎችን በትዝታ ያገናኝና ጥልቅ ወደ ሆነ የትዝታ ውቅያኖስ ይውስደናል ፣ አንዳንዴ ደግሞ ጭው ያለ በረሃ ላይ ይጥለናል! ~ዘፈኑ በፍቅር አዲስ 1997 ላይ በተለቀቀው "ልዑል አስወደደኝ" አልበም ውስጥ Track 8 ላይ የሚገኝ "አንድ ሰው" የሚለው ዘፈን ነው! ፍቅር'አዲስ ነቃጥበብ ~"አንድ ሰው"❤ ~ዘፈኑ የምትጀምረው ፍቅርአዲስ በተሰርቅራቂው ድምጿ እንዲህ በማለት ነው.... "እንደ ሰው እንደ ሰው አወጋለሁ እያልኩ እንደ ሰው እንደ ሰው ትዝታዬን ለሰው እንደ ሰው እንደ ሰው ያነጉደኛል ሀሳብ እንደ ሰው እንደ ሰው ወሶዶ ማይመልሰው . . ወስዶ ማይመልሰው እኔስ ምን አለበት ወስዶ ማይመልሰው ብተው መተንፈሴን ወስዶ ማይመልሰው ባፌ ስጫወት ነው ወስዶ ማይመልሰው የሚጎዳት ነፍሴን አሃሃ ሆሆሆ የሚጎዳት ነፍሴን አሃሃ ሆሆሆ የሚጎዳት ነፍሴን" ~ታዲያ በላይኞቹ ሰንኞች አንዲት ሴት እንደ ሌሎች ሰዎች የራሷን ትዝታ ለሰዎች ለማውጋት ስታስብ ..ወስዶ የማይመለስ ሀሳብ ይዞት እንደሚጠፋ በሀሳብ እንደምትነጉድ ትነገረናለች...ታዲያ ይች ሴት ይዟት ከሚነጉደው ሀሳብ ጋር ግብግብ ገጥማ ትዝታዋን መተንፈስ ፣ መናገርና መጫዋት ስትጀምር ደግሞ ጉዳቱ ነፍሷ ድረስ ዘልቆ እንደሚሰማት መልሳ ታስደምጠናለች! . . . "አነሳውህ ደግሞ እያልኩኝ ትዝታ የትንፋሼን ውበት የልቤን በሽታ ከሰማያት ወዲያ ካድማሱ ባሸገር ከጨረቃው አምባ ከክዋክበት ሀገር.. . . አስረክቦኝ ሲሄድ ብርሀን ለጨለማው ጥሎኝ ጠፋ ብዬ ጊዜን እንዴት ልማው? ትንፋሼን ሰብስቤ እነሳለሁ ማታ ሌት ላሰላስለው የቀኑን ትዝታ" ~ይቺ ሴት ከላይ እንዳለችው "ለትንፋሿ ፣ ለአንደበቷ ውበት እና ለልቧ ደግሞ በሽታ የሆነውን ትዝታ ማንሳት ጀምራለች ...ታዲያ ይሄ ትዝታዋ በቀን ሩቅ ቦታ ከአድማስ ባሸገር ፤ ከሰማያት ወዲያ ፣ ከክዋክብት ሀገር ጥሏት ይመጣል...እሷም ከሀሳብ ከትዝታዋ ሳትመለስ እያየችው ቀኑ ጨለማ ይሆናል...የዚህን ጊዜ ነው "የማላውቀው ሀገርና የማላውቀው ስፍራ ላይ ጊዜ በትዝታ ወሶዶኝ ጠፋ ብዬ ለማን ልማው?" የምትለን!.....ከዛ ማታ ላይ ደግሞ ይቺ ሴት እንደምንም አቅሟን ሰብስባ መልሳ የቀኑን ትዝታ እያሰላሰለች ታድራለች!😥 . . . ~ከታች ባሉት ስንኞች ደግሞ " መጀመሪያ ላይ እንደ ሰው ብላ የጀመረችው ትዝታ ሙሉ ለሙሉ የአንድ ሰው ትዝታ መሆኑን ሳትደብቅ ትናገረናለች... ይሄ የዚህ የአንድ ሰው ትዝታ በየጨዋታ መሀል ባይመጣበት ኖሩ እሷ ለደስታ ለጨዋታ ባቲ ቅኝትን ነበረ የምትቃኘው!....ነገር ግን ዛሬዋ ላይ ትላንቷ ስለመጣ በትዝታ ...የባቲ ቅኝቱን ትታ ዛሬ ለትናንቷ ትዝታን ማንጎራጎር መጀመሯን ትነገረናለች! "አሃሃን አንድ ሰው አሃሃ በየጨዋታው ላይ አሃሃ አንድ ሰው ባይመጣ ትዝታ አሃሃን አንድ ሰው አሃሃ እቃኘው ነበረ አሃሃ አንድ ሰው ባቲን ለደስታ አሃሃን አንድ ሰው አሃሃ በጊዜው ባይገኝ አሃሃ አንድ ሰው የቀን ደግነቱ አሃሃን አንድ ሰው አሃሃ አንጎራጎርኩለት አሃሃ አንድ ሰው ዛሬ ለትላንቱ" "ደግሞ ላይመለስ ርቆ ከሄደበት ለጊዜም ምስጋና ቃሌ ረፈደበት ክራሬን አንስቼ ትዝታን ስቃኘው ከቃላት ጋራ ነው ልቤን የማገኘው . . . ባለጊዜው መጥቶ ዋውዬ ዛሬ ባለቀኑ ተሽኝቷል ትላንት ዋውዬ ቀርቶ ሰቀቀኑ ከርሞ ሲመጣበት ዋውዬ ዘንድሮም ይረሳል እንዲህ ያልፋል እንጂ ዋውዬ ቀን መች ይመለሳል" ~ትቀጥልና ከላይ "ጊዜ ላይመለስ አንዴ ከሄደና ከራቀ ..ያሳለፍኩትን ትዝታዬን በወቅቱ ማመሰገን ሲገባኝ እኔ ግን አረፈድኩ "ትላለች......ከዛም ትላንት በዛሬ ፣ ዛሬ ደግሞ በነገ እየተተካ ቀንን ቀን እየወለደው ወራት ሲሆን ፣ ወራቶች ደግሞ ቀስ በቀስ ዓመታትን ይወልዳሉ!...ትላንት በዛሬ ሲተካ የሚቀረው ሰቀቀኑ ብቻ ነው ...ከርሞ ያልነው ሲመጣ ዘንድሮም ይረሳል ..ታዲያ እንዲህ እያሉ ቀናቶች ያልፋሉ እንጂ መች ይመለሳሉ " ትለናለች! . . . ~በመጨረሻም "ትላንት በዛሬ ፣ዛሬ ደግሞ በነገ ተትከተው ሲያልፉና ዘመናት ሲቆጠሩ...የሰው ልጅ የአፍላነቱ እድሜው ፣ የጉብዝናው ወራት አልፈው ትዝታ ይሆናሉ!...በሀሳብ በትካዜም እናስባቸዋለን ካለፉ በኋላ" ትለናለች!....."የሰው ልጅ ያሰለፈው ነገር በሀዘን በደስታ አልፎ ዘመናት ሲቆጠሩ ትዝታ ሆነው ይቀራሉ እንጂ መች ይረሳሉ" ስትል ነው ከታች የምናደምጣት... "አሃሃን እንደ ሰው ኣሃሃ የአፍላነት ስዓት አሃሃ አንድ ሰው የጉብዝናው ጊዜ አሃሃን እንደ ሰው ኣሃሃ ይመጣል ሁሉም ላይ አሃሃ አንድ ሰው በሀሳብ በትካዜ አሃሃን እንደ ሰው ኣሃሃ በክፉም በደጉ አሃሃ አንድ ሰው በሀዘን በደስታ አሃሃን አንድ ሰው አሃሃ አለኮ ያ ትናንት አሃሃ አንድ ሰው ዛሬም በትዝታ" . . . ~ግጥም ~ ይልማ ገ/አብ ~ ዜማ ~አበበ ብርሃኔ ~ቅንብር ~ኤልያስ መልካ ~ዘፈኑ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ያለው የፍቅር አዲስ እንጉርጉሮ ብቻ ብቻውን ልብ ይሰርቃል ..ጫጫታ መሀል ብትሆን እንኳን የሰከነ ፀጥታ ውስጥ ይከትሃል . . ✍️ Jah Mc #ፍቅርአዲስነቃጥበብ #eliyas #jahmc1 #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok @gigi_shebabaw fans

About