@usernam33562: የመከላከያ እና የክልሉ ፖሊስ አመራሮች በሰሜን ሸዋ ዞን የአንኮበር ቀጠና የጥምር ጦሩን የግዳጅ አፈጻጸም ተመለከቱ። ከፍተኛ የመከላከያ እና የአማራ ክልል ፖሊስ አመራሮች በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ቀጠና በመገኘት የጥምር ጦሩን የግዳጅ አፈጻጸም ምልከታ አደረጉ። የግዳጅ ምልከታውን ያደረጉት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ6ኛ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በጋራ በመሆን ነው። አመራሮቹ በመስክ ምልከታቸው ወቅት በአካባቢው ወጣ ገባ እያለ የሚንቀሳቀሰውን ሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን በዘላቂነት ለማምከን የሚያስችል በቂ ወትሮ ዝግጁነት መኖሩን አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ በበኩላቸው የተደረገው የመስክ ምልከታ በግዳጅ ላይ የሚገኘውን ጥምር ጦር የማድረግ አቅምና ቁርጠኝነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። አካባቢውን በዘላቂነት ከሕገ-ወጥ ታጣቂዎች ነጻ በማድረግ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በብቃት ግዳጃቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በቀጠናው ሕግ የማስከበር ግዳጅ ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች እና የሸዋ ቀጠና ክላስተር አስተባባሪ ረዳት ኮሚሽነር አንዷለም አስረስ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የ31ኛ ሻለቃ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት የአንኮበር ከተማ አስተዳደርን ማዕከል በማድረግ አካባቢውን ከህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማድረግ ሕብረተሰቡን ያሳተፉ የሕግ ማስከበር ተግባራትን በስፋት እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።

Username 🔵
Username 🔵
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 19 October 2026 19:14:12 GMT
15132
317
10
8

Music

Download

Comments

zewudu049
ዘውዱ መንገሻ :
ያገሬልጆችበርቱ🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-20 15:45:26
0
mekdesaschalew669
mekdesaschalew669 :
ሐገሬ🥰🥰
2026-10-20 11:41:59
0
lema.mola
Lema Mola :
ሀገሬ
2026-10-20 11:11:33
0
beleteshumie
BBB :
የኔጀግኖች
2026-10-20 05:01:21
0
beyanemulate
ተንሹ 💋ነኝ❤ ወሎየው⛪ ባለማተቡ ✟ :
ትናት አብረን ነበር የኔጀግኖች አብረን ወደፊት
2026-10-20 08:25:35
0
abeba.0224
ሃገሬ 🇪🇹በደሜ 🇪🇹ውስጥ 🇪🇹 ናት :
የቁርጥ ቀን ጀግኖቻችን
2026-10-20 07:06:38
0
user4526612398463
አበበ ደረጀ :
ጀግኖች በርቱ
2026-10-20 09:22:03
0
user1810461432127
ጊዜ # ነዉ :
[Power][Power][Power]
2026-10-19 20:36:59
0
tenshu18
Tinshu 𝑑𝑒𝑠𝑠𝑖𝑒 🇪🇹 🔥💫 :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-20 09:53:35
0
kiberetu
ኩራት :
🥰🥰🥰
2026-10-20 10:59:54
0
To see more videos from user @usernam33562, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About