@scott_tattoo_mombasa:

SCOTT TATTOOS
SCOTT TATTOOS
Open In TikTok:
Region: KE
Tuesday 20 October 2026 05:05:59 GMT
1077
109
1
1

Music

Download

Comments

gabz.br0vulating
_type5h11 :
Treasure?? Ama naona zangu 😂
2026-10-20 07:54:36
0
To see more videos from user @scott_tattoo_mombasa, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

🌻ነገን አልናፍቅም            ➤ ነገን አልናፍቅም። ምክንያቱም ነገ ገና አልመጣም። ➤➤ዛሬ በእጄ ያለውን ቀን ትቼ፣ ገና ያልደረሰን ቀን ለመናፈቅ አልፈልግም። ➤➤ምናልባት ነገ የምመኘውን ነገር ይዞ ይመጣ ይሆናል። በተቃራኒው ደግሞ  ዛሬ ያላሰብኩትን ነገር ይዞ ይመጣ ይሆናል። ግን ያንን ለመጠበቅ ዛሬን አላባክንም። ➤➤ምክንያቱም ብዙዎቻችን የምንኖረው በዛሬ አይደለም። ያለፈውን እያሰብን እንኖራለን። ወደፊት የሚመጣውን እያሰብን እንጨነቃለን። እና በመካከላቸው ያለችውን ዛሬን እንረሳታለን። ➤➤ነገን መመኘት ችግር  ነው ብዬ አላስብም። ስለነገ ማለምም  ችግር አይደለም። ግን ነገ እንዲሻል በመጠበቅ ዛሬ ያለንን ሕይወት መርሳት ነው የሚያሳዝነው። ➤➤ዛሬ ያለን ሰው ምናልባት ነገ ከእኛ ጋር አይኖርም። ዛሬ ያለን ጊዜ ነገ አይመለስም። ዛሬ የምንሰማው ደስታ ነገ ተመልሶ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ➤➤ስለዚህ ነገን እንጠብቃለን፤ ግን ዛሬን መጥላት የለብንም። ነገን እናልማለን፤ ግን ዛሬን አንርሳም። ➤➤ነገ ራሱ ሲመጣ እንገናኘዋለን። ዛሬ ግን የእኛ ነው። ለመኖር የተሰጠን ቀን ይህ ነው። ➤➤ለመውደድ የተሰጠን ጊዜ ዛሬ ነው። ለመለወጥ፣ ለመሞከር፣ ለመሳቅ፣ ለመማር እና እንደገና ለመነሳት የተሰጠን እድል ዛሬ ነው። እኔ ነገን አልናፍቅም። ➤🍒🍒ነገ እንሚመጣ እጠብቀዋለሁ፤ ዛሬን ግን አልሰዋውም። ምክንያቱም ነገ የሚመጣው ዛሬን ከኖርን በኋላ ነው::      ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link እንዳይረሳ

About