@ddhagersebeketmedia: የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ #አብዱላሂ አደምና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ጕብኝት አደረጉ። "ተኣኀዉ ዘምስለ ኵሉ = ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ!" ሮሜ. ፲፪፡፲፰ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ #አብዱላሂ አደም፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ አብዱልጀዋድ መሐመድ'ና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬ ጥቅምት ፲/፳፻፲፱ ዓ/ም በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአካል ተገኝተው ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የሥራ ኀላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል። በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤትም የሀገረ ስብከቱ የየክፍሉ ኀላፊዎችና ሠራተኞች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሓፊያን፦ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ #አብዱላሂ አደም'ንና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችን በክብር ተቀብለዋል። የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሠናያት ቀሲስ #ኀይለማርያም ገብረ ሚካኤል ለክቡር ከንቲባ አቶ #አብዱላሂ አደም'ና ለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የእንኳን ደኅና መጡ መልእክትን ያቀረቡ ሲሆን የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ልዩ መልእክትንም አድርሰዋል። ክቡር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም'ም በመቀጠል ንግግር ያደረጉ ሲሆን "ድሬዳዋ ሁሉም ሰው በእኩልነት የሚኖርባት የፍቅር ከተማ መሆኗን አውስተው የሃይማኖት አባቶችን በማነጋገር አስፈላጊውን ነገር ሁሉ በማድረግ ከጎናቸው ለመቆም ቃል የምንገባበት ነው።" ብለዋል። በመቀጠልም "የሃይማኖት አባቶች ሀገርን ለመገንባትና ሰላምን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና ስላላቸው አንድ ላይ አመርቂና ውጤታማ ሥራዎችን እንሠራለን" ብለዋል። በማያያዝም ስለ ተደረገላቸው ቀና የሆነ አቀባበል ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መመሪያ ሰጪነት በዐጭር ጊዜ ተሠርቶ የተጠናቀቀውን የሀገረ ስብከቱ ሁለገብ አዳራሽ፣ ዕድሳት የተደረገላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ ቢሮዎች፣ ቀደም ሲል ተመርቆ ሥራ ላይ የሚገኘውን የሀገረ ስብከቱ ሀብት የሆነውንና ለከተማው ማኅበረ ሰብእ እጅግ ሰፊና አመርቂ አገልግሎትን እየ ሰጠ የሚገኘውን ኢስተርን ሆስፒታልን ጐብኝተዋል። 📢 ለፈጣንና ተአማኒ መረጃዎች ➩የፌስ ቡክ ገጻችን 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61563382452089 ➩የቲክቶክ ገጻችን👇 https://www.tiktok.com/@ddhagersebektmedia ➩የቴሌግራም ገጻችን👇 https://t.me/ddhageresebket @አንቀጸ ሕይወት ሚዲያ @ምክሐ ደናግል official ሚድያ @መሠረተ ሕይወት ሚዲያ @ሐመረ ኖኅ ሚድያ @Fre Amde Haymanot @ውሉደ ብርሀን Official @ዐምደ ሃይማኖት ሚድያ @ጽርሐ ጽዮን @ፍኖተ-ጥበብ @ፍኖተ ሰማዕታት ሰ/ት/ቤት

ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሚድያ
ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሚድያ
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 20 October 2026 09:51:16 GMT
3033
278
2
9

Music

Download

Comments

asegid.gudeta0
asegid Gudeta :
enate wushicho nachu zimi bilachi 😁😁😁😁😁😁😁
2026-10-20 11:23:45
1
user985386384591
ቶኒ ቶኒ :
🙏🙏🙏
2026-10-20 10:21:16
0
To see more videos from user @ddhagersebeketmedia, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About