@dinuwang: chinese මැණිකෙ 😫❤️. #theuntamed #weiwuxian #xiaozhan肖战 #tiktok #viral

DINU-王 𓆉
DINU-王 𓆉
Open In TikTok:
Region: LK
Tuesday 20 October 2026 16:10:38 GMT
169
34
5
2

Music

Download

Comments

da_shi12
se_di<3 :
මැණික....!
2026-10-20 16:14:25
1
jing.lin_
Jing_Lin :
වස්තුව❤️👉👈
2026-10-21 13:39:53
1
chethana.aththana8
Chethana Aththanayaka :
❤️❤️❤️
2026-10-20 16:40:48
1
To see more videos from user @dinuwang, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይጠናቀቅ በአርሲ የምእመናን ግድያና መፈናቀል መቀጠሉ ተገለጸ:: ጃንደረባው ሚድያ | ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በርካታ ክርስቲያኖች እየተገደሉና እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ሲል ሀገረ ስብከቱ አስታወቀ።  ሀገረ ስብከቱ “በአርሲ ሺርካ ክርስቲያኖች ላይ በታጠቁ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መጥቷል። ይህም ትልቅ ኀዘን ፈጥሮብናል። ይህንን ችግር ለመፍታት ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ እና የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ውይይቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል” ብሏል ። የሚደረገው ጥረት  ግን ችግሩን እንዳልቀረፈና ተባብሶ መቀጠሉን ሀገረ ስብከቱ ገልጾ “ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለዚህ ችግር ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቷቸዋል፤ ለዚህም ሲሉ ከታች ካሉት የመንግሥት አካላት እስከ ሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጉዳዩን በተደጋጋሚ እያሳወቁ ይገኛሉ፤  እስካሁን ድረስ ግን የተሰጠ መፍትሔ የለም” ብሏል። አያይዞም  የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ  ለዚህ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ከባድ ሀዘን ውስጥ በመግባት ማነጋገር የሚገባቸውን አካላት ሁሉ በማነጋገር እና ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል:: የአርሲ ሀገረ ስብከት  ፣  ቅዱስ ሲኖዶስ ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው  የመንግስት አካላትም ይህንን የከፋ የጸጥታ ችግር በመቆጣጠር ለችግሩ እልባት እንዲሰጡት ሀገረ ስብከቱ መጠየቁን የአርሲ ሀገረ ስብከት መግለጫው አስታውቆአል ። ይህ በእንዲህ አንዳለ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሔደ ባለው ምልዓተ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ላይ በመላው ሀገሪቱ የካህናትና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰላም ችግር  አስመልክቶ በቀዳሚ አጀንዳነት መወያየቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ጥቅምት 12 ቀን በሠጡት መግለጫ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል ::  ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ሀገረ ስብከትን የሚደርሰውን የምእመናን ግድያና መፈናቀል ያወገዘ ሲሆን ችግሩ እንዲቀረፍ ከመንግሥት ጋር ውይይት እንዲደረግ መመሪያና አቅጣጫ መሥጠቱ ተገልጾአል::  ይሁንና በመጀመርያ አጀንዳ ላይ የቀረበው ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይጠናቀቅ ተባብሶ መቀጠሉና ምእመናን በግፍ እየተገደሉና እየተፈናቀሉ መሆኑ ተገልጾአል:: ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት በደረሰበት ወቅት ሀገረ ስብከቱ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ፣ ደጆችሽ አይዘጉን ጨምሮ ጥቂት ማኅበራትን በመጥራት ችግሩን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የልጅነታቸውን ግዴታ እንዲወጡ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል::  ሆኖም ችግሩ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ውስብስብ መሆኑን በመግለጽ በዘላቂነት ካልተፈታ ምንም ዓይነት የተራድኦ ሥራዎች ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም በመባሉ የተገታ ሲሆን ማኅበራቱ ግን ችግሩን ለመቅረፍ ቤተ ክርስቲያን በምታዝዘው ማንኛውም ሥራ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ሆነው የሀገረ ስብከቱን መመሪያ እየተጠባበቁ ይገኛሉ::  ምልዓተ ጉባኤው ሲጠናቀቅ በሚያወጣው ዝርዝር ውሳኔ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ የሚጠበቅ ሲሆን የምእመናን ሞት እስከ አሁንም ባለመቆሙ ጉዳዩን ጊዜ የማይሠጥ ያደርገዋል :: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህን አጀንዳ ዘንድሮ በቀዳሚነት ማስቀመጡ እጅግ ተስፋ ሰጪ ሲሆን ቀዳሚነቱ በስብሰባ አጀንዳ ላይ እንደሆነው ሥራውም ቅድሚያ እንዲሠጠው እንዲያደርግ ይጠበቃል:: “የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን” መዝ. 79:11

About