@jahmc1: የኩኩ 1998 "ትዝታ" አልበም one My favorite Album ❤ ~ ዘፈኖቹ ወደ ኋላም ይስባሉ የዘፈኑ ግጥሞች የሚፈጥሩት ምስልና የሚነግሩን ታሪክ እንደ ፊልም በአዕምሯችን እንድንስል ያደረገናል! ~ታዲያ ከአልበሙ ውስጥ "ወሎ" የሚለው ዘፈኗም ምስል ከሳች ነው....ከልጅነት አብሮ አደጓ ጋር ያሳለፉትን ጊዜና ያደጉበትን ሰፈር ከዛ እየተፋቀሩና እየተዋደዱ እንዴት እንደተለያዩ...ከእሱ ተለይታ ለሌላ እንዴት እንደተዳረች... ~ከዛም ሲናፍቃት እንዴት እንደምትብሰለሰልና በመጨረሻም ስላሰለፉት ነገር ሁሉ አመሰግናው እሱም ጥሩ ትዳር እንዲገጥመው እንዴት እንደምትመኝ ይነግረናል… ~ዘፈኑን በደምብ ስትሰሙት ታሪኩ እንዲህ ነው... . . ኩኩ ሰብስቤ ~ “ወሎ”❤️ ~ኩኩ በዘፈኑ ወሎ ያደገች አንድ የልጅነት ወዳጅ የነበራት ሴት ናት....ታዲያ አሁን ሌላ ህይወት ላይ ብትሆንም ድንገት የልጅነት ወዳጇ ትዝ ብሏታል ፣ የተሯሯጡበት ሜዳና የተራጩበት ምንጭ ውሃ ሳይቀር በሀሳቧ መጥቷልና ለልጅነት ወዳጇ እንዲህ ስትል ሰላምታ ትልካለች..... “በተሯራጥንበት በሰፊው መስካችን በተራጨንበት በምንጩ ውሃችን እንዴት ነህ ልበልህ አንተ የወሎ ልጅ በልጅነት እድሜ የሆንከኝ ወዳጅ" . . . ~ታዲያ ኩኩ ለልጀነት ወዳጇ ሲያድጉ ጎረቤት ወይም ካንድ ሰፈርና ካንድ አካባቢ መሆናቸውን ታስታውሰዋለች....ይሁን እንጂ ቢሯሯጡ ፣ ቢጫወቱና ቢታገሉም ጨዋታቸው ከከንፈር ወዳጅነት እንዳላለፈ ትነግረዋለች...ግን ደግሞ አሁን ድረስ እንደምታስታውሰውም ሳትደብቅ በታችኛው ስንኝ እንዲህ ትለዋለች... "ካንድ አምባ ተፈጥረን አድገን ባንድ ሰፈር ጨዋታችን ሁሉ መች ያልፋል ከከንፈር ጨዋታችን ሁሉ መች ያልፋል ከከንፈር" . . . ~አሁን ላይ የልጅነት ወዳጇም በምን አይነት ሁኔታ እንዳለ ስለማታውቅም እንዲህ ትጠይቀዋለች... “ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ታዲያ ትዝ ሲላት እሱ ለማማር ለመዋብ ጋቢ ማሰራት ኩታ ማስፈተል እንደማይጠበቅበት...በወሎው በባህሉ ልብስ በጉራራ ጊታ እንደሚያምርበት... ከዛም አልፎ በአልባሳቱ በባህሉ ልብስ ሲዋብ ግርማ ሞገሱ እንደሚጨምር….እጀ ጠባብ ለብሶ ጃኖ ከደረበው ጋር ሲወዳደር እሱ ሞገሱ ተፈጥሮው እንደሚበልጥ አስታውሳ እንዲህ ትለወላች... “አታሰራ ጋቢ አታስፈትል ኩታ ትዋብበታል በጉራሯ ጊታ እጀ ጠባባ ልብሶ ጃኖ ከደረበው ይምጣልኝ ያንተ አካል የተከናነበው” . . . ~ከታች ባለው ስንኝ ይሄ የከንፈር ወዳጇ እሷ ለሌላ ተድራ ወይም ባል ካገባች በኋላ እሷ ባለችበት መጥቶ እንደማያውቅና ለአይኗ እንደተራበችው እንዲህም ትላለች... “የፍቅር አስተማሪ የከንፈር ወዳጄ ባል ጋገባው ወዲያ አትመጣም ደጄ ባል ጋገባው ወዲያ አትመጣም ደጄ” . . . ~አንድም ቀን ከተደራች በኋላ በደጇ እሷ ባለችበት የማይመጣው በደህናው መሆኑን ለማወቅ ፈልጋ እንዲህ ትጠይቀዋለች... “ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ለሌላ መዳሯ እውነት የሆነው ይች አፍቃሪ የሰርጓ ቀን ቢሆን የልጅነት ወዳጇ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አቅፏና ስሞ እንዲለያትም ትፈልጋለች....ከዛም በኋላ በአመቱ ከባሏ ጋር ዘመድ ለመጠየቅ ወደ አደገችበት ሰፈር ስትመልስ የልጅነት ፍቅሯ ትዝ ብሏት ሆዷ እንደሚባባ ቀደማ አውቃዋለች …እሱን ማሰቧ እንደማይቀርና እንደማትረሳው ትነገረዋለች.... “ሲድሩኝ በጓሮ በድብቅ ስመህኝ ትመለስ የለም ወይ ለባል ሸልመህኝ ዘመድ ለመጠየቅ ስመጣ በአመቱ አይቀርም በፍቅር ሆዴ መባባቱ” . . . ~ጀግና ጎበዝ ቆራጥ የነበረው ወንድ ለእሷ ሲሆን እንደማይችልና እንስፍስፍ እንደሆነ አንጀት በግልፅ ትነገረዋለች.. “ከሽርጥህ መሀል ጊሌህን ሰክተህ ስፍስፍ ያልከው ለኔ ጀግንነትክን ትተህ ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ከእሷ ውጭ ሌላ አስቦ የማያውቀው የልጅነት ጓደኛዋ ከከንፈር ወዳጅነት ውጭ ሌላ ሳያስብ ክብሯንና ገላዋን የጠበቀላት ወዳጇን... ዛሬ እሷ ሌላ ስታገባ...የወደፊት የእሱ እጣፈንታው ከእሷ ውጭ የማያውቀው እሱ ምን ይገጥመው ?…ማንንና ምን አይነት ሴት ያገባ ይሆን ? ብላ ማሰቧን መጨነቋንም እንዲህ ስትል ከታች እንረዳለን.... “ይመጣል ፊቴ ላይ የጥንት ሁኔታህ ትዳርህ ማን ትሆን ያንተስ አለኝታህ በልጅነት ጊዜ ከኔ የታፈቀርከው ገላዬን ባደራ ይዘህ የጠበከው” . . . ~ታዲያ ይሄን መልካም የልጅነት ወደጇን ጥሩ ሚስት እንዲገጥመው ከልቧ እንዲህ እያለች ትመኝለታለች... “እህል ውሃ ባላት ኑሮን ባወቀችው ይከፍልህ ብድሩን በተጠበቀችው ይካስህ ፈጣሪ ኑሮን ባወቀችው ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~እሷንም ካገባች በኋላ መጥቶ እንማያያት …እሱ ሆኖ ሳለ አብሮ አደግ ወዳጇ በቤተሰብ ተድራ ከሌላ ሰፈር የሚመጣው ባሏ አቅፎ እንደሚወስዳትና...የእሷና የእሱ ግንኙነት እዚህ ላይ ሊቋረጥ እንደሆነ ገብቷት እንዲህ ትላለች... “ከተዳርኩኝ ወዲያ መጥተህ ላታየኝ ላጨኝ ሰጥተህኝ ነው የምትለየኝ ሳለህ አብሮ አደጌ ካንድ ወንዝ የምንጠጣው ይወስደኛል አቅፎ ከማዶ ሚመጣው . . . “የፍቅሬ መድመቂያ ባትሆንም ቀለሜ መቼም ወንድሜ ነህ እስከ ዘላለሜ መቼም ወንድሜ ነህ እስከ ዘላለሜ” ~ታዲያ ፈጣሪ ፈቅዶ አንድ ላይ ትዳር ባንቀለስ አብረን መሆን ወይም መጋባት ባንቺል እንኳን...አንተ ለኔ ለዛላለም መልካም ወንድሜ ነህ ትለዋለች ስንብት በሚመስል ሁኔታ.... ግጥምና ዜማ ~የህዝብ አጃቢ ~ኤክስፕርስ ባንድ ✍️ Jah Mc #jahmc1 #kukusebsebe #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok #music @gigi_shebabaw fans

Jah Mc
Jah Mc
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 20 October 2026 16:48:20 GMT
43539
1973
51
269

Music

Download

Comments

dogalibb
ማን ልበል?🤔 :
who say kuku is underrated singer?[Tears of joy][Tears of joy][Tears of joy]
2026-10-21 04:28:39
1
gigi_shebabawfan2
gigi_shebabaw fans :
ብእርህ አይንጠፍ ጓድ😌🫶🙏❤️
2026-10-20 17:19:37
4
mohammed.yesuf184
Mohammed Yesuf :
ወደኋላ የሚስብ ግጥም
2026-10-21 09:44:26
1
v_family8
v_family :
ተድረሽ ነበር ኩኩዬ
2026-10-20 20:49:13
2
biosoniclab
BioSonic Lab :
lovely
2026-10-20 20:16:49
1
user694285biruk
ⒷⒾⓇⓤⓚ🅱️ :
2026-10-21 12:41:26
1
user1810387012573
yitu :
እውነት ነው። ግን ግን እንዴት ከ 1 እስከ 13 ሳላዳምጠው እህት
2026-10-21 14:59:03
1
waza22355
WAZA :
kukusha mirtua
2026-10-20 21:08:18
1
mmuussiicc_12
Music Lover :
ሙሉ ዘፈኑ?
2026-10-20 16:52:27
2
daniel.tinsae1
Daniel Tinsae :
abet webet
2026-10-21 06:13:56
1
hope04785
Hope :
የኩኩ ውበት❤️🔥
2026-10-20 16:50:08
3
aeba144
mekelle semnawit kokob :
አበየት ቁንጅና ኩኩየ ፁሩይት ጌዜ ዘይሓልፎ ሙዝቃ ፈጣር ነውሕ ዕድሜ ምስጥዕና ገይሩ ይሃብኽ
2026-10-21 16:52:06
1
ashenafihussen
Ashenafi :
wow lijinaten astawoseny lelam amtaliny💪👍
2026-10-21 14:26:02
1
seni68157
seni :
ኩኩዬ
2026-10-21 18:18:46
0
999836d_
999836d :
ጀግና፡ያንበረክካል፡ማለት
2026-10-21 11:46:40
1
user8010309618369
Almighty God :
እውነት ነው
2026-10-21 16:59:49
0
meleseassefa2127
Melese Assefa2127 :
👌👌✌️
2026-10-21 06:51:09
1
edel2112_
ዕድል2112🦅 :
2026-10-20 17:24:31
2
ayshe740
user6170139305756 :
ሞት የሚባል ነገር ባይናር ምን አለ.........ይጨንቃል ኩኩዬ
2026-10-22 12:28:43
0
alex.abyssinia
Alex Abyssinia :
2026-10-21 09:27:59
1
user1600900544686
user1600900544686 :
ኩኩአወድሻሎህ
2026-10-22 05:00:28
0
bitsemezpsp
faith wins :
💯
2026-10-21 12:46:56
0
gedionber
ጌድዮን :
ችርስ
2026-10-21 18:44:52
1
999836d_
999836d :
ኩክሻ፡ፈንድሻ፡፡
2026-10-21 12:04:02
0
yibeltalatalay159
yibeltal :
Ere endeneshi ,,endeneshi,,,kukuye
2026-10-21 14:03:35
0
To see more videos from user @jahmc1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About