@trangxinhbandonu: Combo 2 quần legging đùi nữ #Trangxinhshop #quanlegging

Trang Xinh Shopp
Trang Xinh Shopp
Open In TikTok:
Region: VN
Wednesday 21 October 2026 09:58:50 GMT
432
1
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @trangxinhbandonu, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ልናገር እናንተም አንብቡልኝ ይሄ ቤተክህነት ግን ወዴት እያመራ ነው? የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው አሁን ስለተገፉ አባቶች ጥቂት እናገራለሁ  1ኛ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ብፁዕነታቸው የኢሉባቦር ምድር ያፈራቻቸው እንቁ የቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ናቸው :: ቀርቦ ለተረዳቸው የዋህ :ቅን : ሰው እንዲበደል የማይወዱ : ደሐን የሚረዱ : ችግርን ጆሮ ሰጥተው የሚሰሙ ሰምተውም የሚቀርፉ አባት ናቸው ::ብፁዕነታቸው ከድቁና እስከ ጵጵስና አገልግሎታቸው የሰመረላቸው ተናግረው የምይሳምኑ ሰርተው የሚያሰሩ በጂንካ :በቦረና :እና በሸካ ዞን ቴፒ አካባቢ እና በጋምቤላ አካባቢ ይሄ ነው የማይባል ተጋድሎ ፈፅመዋል :: ከሰሯቸው ስራዎች መካከል  1ኛ, እስከዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ከወለጋ እስከ ጂንካ ከጋምቤላ እስከ አሶሳ ድረስ 250 ቤተክርስቲያን አሳንፀዋል  በጋምቤላ ክልል ብቻ 100 በላይ አብያተክርስቲያናት  አሳንፀዋል  2ኛ የጋምቤላ ክልል እርስ በእርስ ጦርነት በነበረበት ጊዜ የክልሉን ባለስልጣናት በማነጋገር እንዲታረቁ እና ሰላም እንዲፈጠር አርገዋል  3 ኛ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስሩም አብያተ ክርስቲያናት የራሳቸው መተዳደርያ እንዲሆናቸው ሰፊ የይዞታ መሬት እንዲሰጣቸው አድርገዋል  4 ጋምቤላ ጀጀቤ አቡነ አረጋዊ ገዳም ተራራው ሙስሊሞች ሊወስዱት 7,000.000 ብር ከፍለው ጨርሰው ሊሰሩ ሲሉ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ጋር በመወያየት በአስቸኩአይ ገንዘቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያን እንዲሰራበት አድርገዋል  ይሄ ቤተክርስቲያን ሲሰራ መጀመሪያ ዋጋ የከፈሉት ብፁዕነታቸው ናቸው መሳርያ ሳይቀር ተተኩሶባቸው ከሞት አምልጠዋል  5, የጋምቤላ ሃገረ ስብከት ከኢሉባቦር ሃገረ ስብከት ተገንጥሎ እራሱን ችሎ ሃገረ ስብከት እንዲሆን እና የተሟላ ሰራተኛ ኖሮት በቂ ደሞዝ እንዲከፈላቸው አድርገዋል:: 6 ታላላቅ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች ባለስልጣናት ምሳሌ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ሌሎችም የክልሉ ተወላጆችን በማጥመቅ እምነታቸውን እንዲያውቁ ከ 50 በላይ ሰባኪያን እና ዲያቆናት እንዲፈሩ አድርገዋል  ምሳሌ መጋቤ ስርዓት ዴንግ ረስ የሀገረስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩ  መምህር አንድነት ድድሙ ሌሎችም  7 ጥምቀት በዓል በጋምቤላ ክልል በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ለተከታታይ 5 ቀናትእንዲከበር ታላላቅ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባክያን ዘማርያን በተገኙበት ጉባኤ ተዘጋጅቶ ህዝቡ እንዲማር እና በሊቃነ ጳጳሳት እንዲባረክ አድርገዋል በአሉላይም መንግስት አምስቱም ቀን ልዩ ቀን አድርጎ እንዲያከብረውበክልሉ ካላንደር እንዲዘጋ አድርገዋል  የጋምቤላ ክልል እሳቸው ከወጡ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሰላም ጠፍቷል  8 በደቡብ ሱዳን አሁን ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ያሳነፁት ብፁዕነታቸው ናቸው  9 የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ የተጣላውን በማስታረቅ ነጋዴዎች እንኩአን መንግስት ግብር ሲጨምርባቸው ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ፍትሃዊ ሥራ እንዲሰራ በማድረጋቸው ስራቸውን እና ድካማቸውን የተመለከተ መንግስት የክልሉ የሰላም አምባሳደር አድርጎ ሾሟቸዋል :: 10 የወለጋ አብያተ ክርስቲያናት በአገልጋይ እጦት እና በነዋዬ ቅድሳት እጥረት የተዘጉ ከ 213 ቤተክርስቲያን በላይ በራሳቸው ወጪ ደሞዝ ከፍለው እና ንዋየ ቅድሳት ገዝተው አስከፍተዋል :: ለመጀመሪያ ጊዜም በኦሮሚኛ ቋንቋ ቅዳሴ እንዲቀደስ እና ወንጌል እንዲሰበክም ወለጋ ላይ ሰርተዋል  11,ቄለም ወለጋ ሃገረ ስብከት ፅሕፈት ቤት ያልነበረው ሃገረ ስብከት ስለነበር ፅሕፈት ቤት ሰርተው አስረክበዋል እንዲሁም ሃገረ ስብከቱ እራሱን ችሎ እንዲተዳደር G+4 ህንፃ በደምቢ ዶሎ ከተማ ገዝተው አስረክበዋል 11,000.000 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ በደምቢ ዶሎ በገርጄዳ እና በጊዳሚ ከተማ መንበረ ጵጵስና ሰርተዋል  ብፁዕነታቸው እያንዳንዱ በአገለገሉበት ቦታ ሁሉ የሰሩትን ሥራ ብንናገር ጊዜም ሰዓትም አይበቃንም ነገር ግን ህዝቡ እውነቱን ማወቅ ስላለበት አቡነ ሩፋኤል ከፀሎት የማይለዩ :ለራሳቸው መኪና የሌላቸው እንደሌላው ጳጳስ ቤት የሌላቸው ቀሚስ መስቀል እና መፅሐፋቸው ብቻ ሀብታቸው የሆነ ታላቅ አባት ናቸው :: ታድያ ስለምን ይገፋሉ ብላችሁ ጠይቃችሁ እንደሆነ ከዚህ በታች እንደሚከተለው አቀርባለሁ  1ኛ ብፁዕነታቸው ብዙውን ጊዜ በወለጋ አካባቢ እየተዙዟሩ ሐዋርያዊ ጉዞ ያደርጋሉ በዚህም ምክንያት በአካባቢው ካሉ የሸኔ ታጣቂዎች እና በመንግስት በኩል በተፈጠረ ችግር ህዝቡ እየተሰቃየ ስላዩ መንግስት እና ሸኔን ለማስታረቅ ሲጀምሩ ነገሩ ያልተዋጠላቸው ጥቂት ሰላም ጠል አካላት ስማቸውን አጥፍተው ከወለጋ ምድር እንዲወጡ አደረጉ :: በዚህም በታቦቱ ጉዳይ አንዲት ነገር ልበል ብፁዕነታቸው ታቦቱ ያስረከባቸው አካል የለም እሳቸው ታቦት ባርከው የሚሰጡ እንጂ የሚወስዱ አይደሉም :: እሳቸው አሁን ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰባቸው ከመንግስት ጎን ሆነው በመስራታቸው ምክንያት ብቻ ነው አዳንድ ኦሮሞ ጠል የሆኑ አካላት የኦሮሞ ጳጳስ አንፈልግም በማለት ከአሶሳ እስከ ጋምቤላ ድረስ ህብረት በማድረግ እሳቸው እንዲገፉ አደረጉአቸው ዘረኛ ያልሆኑትን ጳጳስ ዘረኛ ናቸው ብለው ስማቸውን አጠፏቸው :: አሁን እንኩዋን እስከጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ 40 ቀን ሱባኤ ይዘው በገዳም ይገኛሉ ምን አልባት ስብሰባው ይበላሽብኛል ብለው ያሰቡ አንዳንድ ሰዎች እስካሁን ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ ቀኑም ደርሷል እግዚአብሔር ም አድርሶናል በዚሁ አጋጣሚ በብፁዕነታቸው ጉዳይ የተላኩ አጣሪ ኮሚቴዎች የማጣራት ስራው ትክክለኛ ስላልሆነ ቁአሚ ሲኖዶስ ተቀባይነት እንዳይኖረው እና በምልዓተ ጉባኤ እንዲታይ አድርጉአል እናመሰግናለን ቁአሚ ሲኖዶስ የቄለም ወለጋ ሕዝብ የአሶሳ ሕዝብ እና የጋምቤላ ሕዝብ ብፁዕነታቸው ተመልሰው እንዲሰሩ ይፈልጋል የህዝቡ ድምፅ ቢታፈንም የህዝቡ ሪፖርት ወደ መንግስት አካላት ደርሷል ::

About