@quy271187: Cầu thang xoắn ốc lan can cầu thang sắt một mình cân tất #Quyinox #xuhuongtiktok #viral #reels

nguyễn Đình quý 75
nguyễn Đình quý 75
Open In TikTok:
Region: VN
Wednesday 21 October 2026 13:23:15 GMT
212
4
0
2

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @quy271187, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

‎🌱የሰው ልጅ ሕይወት በምቾትና በጸጥታ ብቻ የሚገነባ ቀላል ሐውልት ሳይሆን ‎     🌿 በጊዜ መዶሻ እየተወቀረ ‎         🌿 በፈተና እቶን እየተፈተነ ‎🌿 በመከራ ወንፊት እየተነፋ የሚገነባ ውድ ቅርስ ነው። ‎        🌿ተፈጥሮ ራሷ ለዚህ እውነት ቋሚ ምስክር ናት ‎🌿 ዘር መሬት ውስጥ ተቀብሮ ካልበሰበሰ ፍሬ አያፈራም ንጋትም የሚወለደው ከጥቅጥቅ ጨለማ ማኅፀን ነው። ‎ ‎🌿ወተት በረጋበት ሳይነካ ቢቀመጥ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታው  መበላሸት ብቻ ነው። ‎🌿 ነገር ግን  በእጅ ሲናጥ ‎   🌿 ሲገለባበጥና ሲታመስ በውስጡ ተሰውሮ የነበረውን ክቡር ቅቤ ይወልዳል። ‎🌱 የሰውም ልጅ እንዲሁ ነው ‎   🌿 ያለ ሂዎት ንቅናቄ ያለ ትግል እና ያለ ፈተና በምቾት ቀጠና ውስጥ  ከተቀመጠ በውስጡ የተቀበረው ታላቅ እምቅ ኃይል ሳይገለጥ ያልፋል። ‎🌿 የሕይወት ውጣ ውረድ የሚያናውጠን ሊያፈርሰን ሳይሆን ከውስጣችን የላቀውን ማንነት ጨምቆ ሊያወጣ ነው። ‎ ‎🌿በተመሳሳይ መልኩ በምድር ጥልቀት ውስጥ የሚገኝ ተራ ካርቦን ወደ ውብና የማይበገር አልማዝ የሚቀየረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታትን በሚፈጅ ከፍተኛ ሙቀትና  ግፊት ውስጥ ሲያልፍ ነው። ‎🌿ያንን ጫና ባይቋቋም ኖሮ ተራ ድንጋይ ሆኖ ይቀር ነበር። ‎🌱አንተም በሕይወትህ የሚገጥሙህ ‎       🌿 ድካሞች ‎          🌿 የልብ ስብራቶች ‎            🌿 የገንዘብ እጥረቶችና የሰዎች አለመረዳት ተራ ክስተቶች ሳይሆኑ ማንነትህን ከተራነት ወደ አልማዝነት የሚያሸጋግሩ የመቀረጫ መሳሪያዎች ናቸው። ‎ ‎ ‎ ‎🌱ህመም የእድገት መነሻ ነው🌱 ‎🌿 ጡንቻ የሚጠነክረው በክብደት ሲወጠር እንደሆነ ሁሉ ‎🌿አእምሮና መንፈስም የሚሰፉት ከባድ ኃላፊነትና ፈተና ሲሸከሙ ነው። ‎🌿ምቾት ዛሬን ያስደስታል ፈተና ግን ነገን ይገነባል። ‎🌱ሂደቱ ከውጤቱ ይበልጣል🌱 ‎🌿 ብዙዎች የሚመኙትን የአልማዝነት ክብር ይፈልጋሉ ‎🌿 ነገር ግን ወደዚያ የሚያደርሰውን የመቀጥቀጥ ሂደት ይሸሻሉ። ‎🌿 ሆኖም ያለ ሂደት የሚገኝ ድል መሠረት የሌለው ቤት ነው ንፋስ ሲነፍስ ይፈርሳል። ‎🌿 እውነተኛው ማንነትህ የሚታየው ሁሉም ነገር ሲሳካ ሳይሆን ነገሮች ሲጨልሙና ተስፋ የሚያስቆርጡ ሁኔታዎች ሲከቡህ በምታሳየው ትዕግስትና የአቋም ጽናት ነው። ‎🌿 እያንዳንዱ እንቅፋት የራስህን ድክመት እንድታርም ስልትህን እንድታሻሽልና ያልተገለጠ ጥበብህን እንድታወጣ የሚላክ የሕይወት መምህር ነው። ‎ ‎🌱ስለዚህ🌱 ‎🌿ዛሬ ላይ የገጠመህ ጫና ሲበዛብህና መንገዱ ሲከብድብህ ተስፋ አትቁረጥ። ‎🌿 እየተናጥክ ያለኸው ቅቤው ማንነትህ እንድወጣ ነው 🌿እየተቀጠቀጥክ ያለኸውም አልማዝ ሆነህ እንድታበራ ነው። ‎🌿 በትዕግስት ጽና ‎🌿 ሂደቱን ተቀበለው ‎🌿 ከእሳቱም በኋላ የሚጠብቅህን የላቀ ክብር አሻግረህ ተመልከት። ‎ ‎Telegram👉👉👉https://t.me/misgie123456(አንድ እርምጃ) ‎

About