@muhamedmuhamed636: ራስን የማግኘት ድል አንዳንዴ ለሰዎች የምንሰጠው ቦታ ልክ የለውም፡፡ በምናባችን ከፍ አድርገን እናነግሳቸዋለን ሕይወታችንን ያለ እነሱ ትርጉም አልባ ጉዟችንን ያለ እነሱ ምሉዕ የማይሆን ይመስለናል። ነገር ግን ጊዜ የተባለው ታላቅ መምህር የሰዎችን የውሸት ካባ ገፎ እውነተኛ ማንነታቸውን ሲገልጥልን ትናንት የጓጓንለት ስማቸው ዛሬ ባዶ ጩኸት ሆኖ ያርፋል። እና ዛሬ ትኩረታችንን የነፈግናቸው በጠላትነት ሳይሆን በትናንቱ የተሳሳተ እይታችን ላይ የነቃ አእምሮ ስለነገሰ ነው፡፡ ስማቸውን መስማት ያስጠላን ለነሱ የገበርነውን ውድ ጊዜና ንጹህ ስሜት በማስታወሳችን ነፍሳችን እረፋት ስለምታጣና ሰለምትሸበር ነው ፡፡ እኛ ዛሬ ከስማቸው በላይ ለራሳችን ሰላም ቀዳሚ ዋጋ ሰጥተናል። ትናንት ከልባችን የነበሩትን ዛሬ ከትዝታችንም እንዲወጡ መፍቀድ የውሳኔያችን ጥንካሬ እንጂ የልባችን ክፉነት አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንዳንዴ ሰዎችን ማጣት ሳይሆን ራስን ማግኘት ትልቁና የመጨረሻው ድላችን ስለሆነ ነው፡፡ ትናንት በናፍቆት የምንጠራው ስም ዛሬ የባይተዋርነት ድምፅ ሲሆን ትልቅ የሕይወት ትምህርት ነው፡፡ ለራሳችን ሰላም ስንል ትናንትን በትናንት መቃብር ላይ ጥለን ወደ ራሳችን ብርሃን እንጓዛለን። በቃ ሰላም ለራሳችን!

(1)ብቻ
(1)ብቻ
Open In TikTok:
Region: AE
Wednesday 21 October 2026 21:00:32 GMT
1042
20
1
2

Music

Download

Comments

m4a1m4e0
ኢንሻአላህ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-22 02:17:00
0
To see more videos from user @muhamedmuhamed636, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About