@nejashihawassa: #ለሌሎች_እንዲደርስ_ሼር #የእዉነት_ድምፅ በቋንጤ አቡበክር መስጂድ ጉዳይ የተፈጸመ የሕግ መጣስና የእስራት ግፍ! በቋንጤ አቡበክር መስጂድ ጉዳይ በተለያዩ ቦታዎች ተይዘው የታሰሩ ንጹሃን ዛሬ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቢኖራቸውም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ከጥቅምት 17 ጀምሮ ከታሰሩ አቅራቢያ ወር ሊሞላቸው ነው፤ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡም አላስፈላጊ ጫና እየተደረገባቸው ይገኛል። 🔹 አብዱል አዚዝ (የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ) 🔹 አብዱል ሀሚድ (የጤና ኃላፊ) 🔹 አልሀምዱ (የፍትሕ ኃላፊ) በዋናነት የተሰጣቸውን የመንግሥት ሥልጣን ለረባሽ ቡድኖች ሽፋንና አደረጃጀት በመስጠት የወረዳውን ሰላም የሚያደፈርሱ አካላት ናቸው። ለጊዜው እነዚህን እንጠቀሳለን፤ ወደፊትም ሌሎችን በየተራ ይፋ የምናደርግ ይሆናል። በተለይም የማዘጋጃ ኃላፊው አብዱል አዚዝ ሁለቱ ወንድሞቹ የብጥብጡ ዋና አካል ሆነው ሳለ እንዳይታሰሩ ከላላ በማድረግ፣ ሌላውን ሰላማዊ ማኅበረሰብ ግን በሞተር እየዞረ እያሳደደ አሳስሯል። የታሰሩትንም "በግድ መስጂዱን አስረክቡ" በሚል ማስፈራሪያና ጫና እያደረጉባቸው ይገኛል። አካባቢው 98% ሱፍይ ማኅበረሰብ የሚኖርበት ቢሆንም፣ የወረዳው አስተዳደር የሕዝቡን መብት ሊያስከብር አልቻለም። ይልቁንም ከወረዳው ጎን ሆኖ ለልማት የሚለፋው ማኅበረሰብ በዚህ ልክ እየተገፋ ይገኛል። የሚገርመው ነገር፣ ምንም ያላጠፉ ሕፃናት መድረሳቸው ተዘግቶባቸው ከቂርዓት ታግደዋል። ጉዳዩን በሰላም ለመጨረስ የሀገር ትላልቅ ሽማግሌዎችና መሻይኾች "ጉዳዩን እኛ እንየው" ብለው ቢመላለሱም፣ አመራሮቹ አሳፍረው የሸኟቸው ሲሆን ሽማግሌዎቹም ድርጊቱን በጽኑ ተቃውመው ቅር ተሰኝተዋል። የሚመለከተው አካል ሁሉ የሕግ የበላይነት እንዲከበርና ለታሰሩት ንጹሃን ፍትሕ እንዲሰጥ እንጠይቃለን! #ፍትሕ #breaking_news @ነጃሺ ሚዲያ @Engr/Sheikh Fekhrudin Mohammed @የኮ/ቀ ክ/ከ ነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር
ነጃሺ ማህበር ሃዋሳ Nejashi hawasaa
Region: ET
Thursday 22 October 2026 05:34:23 GMT
Music
Download
Comments
ahmed :
a1
2026-10-22 17:37:52
0
To see more videos from user @nejashihawassa, please go to the Tikwm
homepage.