@yohanesbekeel: #ማን_እንደ_ሚካኤል ስለ መታዘዙ ፤ ስላለው ትህትና ከእግዚአብሔር ያገኘ ፤ ከፍ ያለ ልእልና። በሥነ ባህሪው ፤ እጅግ የረቀቀ ከመላእክት ሁሉ ፤ በክብር የላቀ። የፈጣሪን ትዕዛዝ ፤ ሊፈጽም የሚላክ በስሙ መስካሪ ፤ ገናናውን አምላክ ። የምክሩ አበጋዝ ፤ መልአከ ሀይሉ ምህረት ርህራሄ ፤ የሆነ ክፍሉ ። በእጁ መዳፍ ላይ ፤ ፍጥረት የጸናበት ስመ እግዚአብሔር ፤ የተቀረፀበት። ከመላእክት ወገን ፤ ከሚባሉት ዋና ማን እንደ ሚካኤል ፤ ይገኛል ገናና ። ስለ ብሩሃኑ ፤ ስለ እጽወ ገነት ስለ ብሔሞትና ፤ ሌዋታን ምንነት ለጻድቁ ሄኖክ ፤ የተመረጎመለት። ኢያሱን ከአማሌቅ ፤ ዳዊትን ከጎልያድ ዳንኤልን ያወጣ ፤ ከአንበሳ ጉድጓድ። ፈርዖንን በእሳት ፤ አውታር እያጠረ እስራኤልን ከግብፅ ፤ መርቶ ያሻገረ። የሰይፉን ነፀብራቅ ፤ ብቻ ባሳረፈ የሰናክሬምን ጦር ፤ ምድር ያረገፈ። ከእሳታውያኑ ፤ ልዑላን አገልጋይ ማን እንደ ሚካኤል ፤ ይገኛል ተራዳይ። ሕዝበ እግዚአብሔርን ፤ ከአጋንንት ጦርነት እንዲጠብቃቸው ፤ የተሰጠው ሹመት። ምእመናንን ሊያድን ፤ ከኃጢአት ፍርጃ በልዑል መንበር ፊት ፤ የሚቆም ለምልጃ። በጎና ይቅርባይ ፤ ከመዓት የራቀ ሰይጣንን ድል መንሻ ፤ ሃይል የታጠቀ። ሰይፉን ከሰገባው ፤ መዞ እያወጣ የእግዚአብሔርን ጠላት ፤ በሃይሉ የሚቀጣ። የሃይማኖት አርበኛ ፤ ሰዳዴ ሳጥናኤል ማን አለ ባለሟል ፤ ልክ እንደ ሚካኤል። ስሙን በአደባባይ ፤ የሚመሰክሩት ፍቅሩ የገዛቸው ፤ ብዙ ልጆች ያሉት ። ሰይጣንን ሊዋጋ ፤ በእለተ ምፅአት ስለ ሕዝብ ልጆች ፤ የሚነሳ አባት። የተቸገሩትን ፤ የተጨነቁትን ዘወትር የሚራዳ ፤ ወዳጄ ያሉትን። ያዋዩትን ምስጢር ፤ ሳይረሳ ፈፃሚ ከሚካኤል በላይ ፤ ማነው ስለት ሰሚ። #ቅዱስ #ሚካኤል #አባቴ ✝️✝️
yohanes የተክልዬ ልጂ🇪🇹🇪🇹
Region: ET
Thursday 22 October 2026 08:53:23 GMT
Music
Download
Comments
alem :
1212👍🙏🙏🙏
2026-10-22 10:14:42
0
Hawi :
🙏🙏🙏
2026-10-22 10:00:43
0
Adu 121921 :
🙏🙏🙏
2026-10-22 12:09:18
0
To see more videos from user @yohanesbekeel, please go to the Tikwm
homepage.