@yayaye917: ✅ወንድ ሆይ ለትዳርህ ምንጊዜም ብቁ ሁን!! 🌱ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች።ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች።ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው።ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም። 🌱ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች።ስትናደድ ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም። 🌱ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ሳም፣ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር።ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም። 🌱ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት።ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ደስታን፣ሀዘንን፣ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ።ሀዘኑን ተፅናኑ፣ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ።ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም። 🌱ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም በላይ መጀመሪያ ሚስትህ፣አንተና ልጆችህን ብቻ አስቀድም።ቤተሰብ፣ጓደኛ፣ጎረቤት እና ሌላው ከትዳርህ ቀጥሎ ናቸው።ይህን ማስተዋል ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም። ✅ሴት ሆይ ለትዳርሽ ምንጊዜም ብቁ ሁኝ 🌱ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም።ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ካልወሰድሽለት ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም።ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው እውነት ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም።ከባለቤትሽ አጠገብ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ እንድሆን ራስሽንና የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽና እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም፤ከባልሽ ጋር በተጣላሽ ወቅት በፀሎት አምላክሽ ጋር ከመነጋገር ይልቅ ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም።ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የእሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ እመኝኝ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም። በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማታበረታችው ከሆነ፣ ለራሱና ለቤተሰቡ የማይጠቅሙ አመሎቹን በፀባይ አግዘሽ እንዲተው የማታደርጊ ከሆንሽ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም።ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽለት ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም። ✅ ትዳርን ማክበር ራስን ማክበር ነው።ፈጣሪ የራሳችሁ የሆነ የልባችሁ ማረፊያ ሰው ባርኮ ይስጣችሁ ፡፡ፈጣሪ ላገባነውም ላላገባነውም የትዳርን ዋጋ የምንረዳበት ጥበቡንና ማስተዋል ይስጠን እላለሁ።በትዳር ዓለም ውስጥ ላላችሁም ሆነ ላልሆናችሁ(ወደፊት ትዳር ለምትመሠርቱ) ሁሉ ትዳራችሁ የአምላክ ፀጋ፣በረከት ሰላምና ፍቅር የበዛበት ያድርግላችሁ! 🤌🏾ሁሉም ሰው ይማርበት ዘንድ ሸር አድርጉት🫶🏽 እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።

🗣13🎉𝕪𝕒𝕪𝕒🎉21🌹
🗣13🎉𝕪𝕒𝕪𝕒🎉21🌹
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 22 October 2026 10:45:03 GMT
3840
99
2
19

Music

Download

Comments

muleyemariyam21
Mule ye mariyam :
👌👌👌
2026-10-22 10:49:42
0
user411857834490255
ቃል/የማረያም ልጅ :
🙏🙏🙏
2026-10-24 15:46:21
0
To see more videos from user @yayaye917, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About