@abduhussien1: #የባል እና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም 🌹ባል :― አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ 🌹ሚስት― አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ ፍቅርክ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነክ ፍቅርክን መግበኝ ካጠገቤ ሁነክ። 🌹ባል:― የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ነች ጌታየ ይመስገን እሷን አድሎኛል ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል። 🌹ሚስት:― የልጆቼ አባት የትዳሬ አጋር ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር መኖርክ መኖሬ መጥፋትክ መጥፋቴ ሳጣክ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ 🌹ባል:― የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል! 🌹ሚስት:― የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ የፊትክ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ አንጀቴ ይርሳል ድምፅክን ስሰማ 🌹ባል:― ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር 🌹ሚስት:― እኔ እንክትክት ልበል እኔ ልሰባበር እሾክ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና 🌹ባል: እኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ 🌹ሚስት:― ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ በርሬ እንዳልመጣ ያለክበት ድረስ ውዱ ባለቤቴ ፍቅርክ ለበለበኝ አሁንስ ከብዶኛል በዱአክ አስበኝ።ማሜነኚ ይመቻችሁ፡፡ #creatorsearchinsights
abduhussien779
Region: ET
Thursday 22 October 2026 20:47:12 GMT
Music
Download
Comments
አቡ ሰአድ :
አለህ አለህ
2026-10-23 14:58:09
1
hsbunallh :
❤️❤️❤️
2026-10-25 04:07:23
0
kormicha mohammed :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-25 15:03:41
0
ዝምተኛዉ :
🥰🥰🥰
2026-10-25 09:05:24
0
⚔️🗡❤king of life🖇🤞💊⚖ :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-24 14:13:42
0
hussenmohammed1557 :
[Red heart][Red heart][Red heart]
2026-10-24 05:24:17
0
abdi :
🥰😁🥰😁
2026-10-23 06:20:12
0
hone megetati :
👍👍👍
2026-10-22 22:09:17
0
seya man :
😍😍😍
2026-10-25 18:42:15
0
To see more videos from user @abduhussien1, please go to the Tikwm
homepage.