@mergattedalu: የጥላ ወጊ መተት በየትኛው ሕመም እራሱን ይደብቃል? ተወዳጆች ሆይ በዚህ በሳይንስ ዘመን አጋንንት እራሱን በተለያየ በሽታ በመሰወር እንዳይታወቅበት እና በምናውቃቸው፣ በሳይንስ ምርምር በተደረሱባቸው በሽታዎች እራሱን በመደበቅ ይጫወትብናል፡፡ ለምሳሌ ዛር፣ ዓይነ ጥላ እና መተት የሴት ልጅ ወገብ ላይ በመቀመጥ ሊያሰቃያት ይችላል፡፡ በወገብ ሕመም የምትሰቃይ ሴት ሐኪም ቤት ብትሄድ የዲስክ መንሸራተት ተብላ ምናልባትም ኦፕራስዮን ተደርጋ ሳትድን ትቀራለች፡፡ በዲስክ መንሸራተት ስም የተደበቀው አጋንንት ስውር የሕመም ጥቃት እያደረሰ ሳይታወቅበት ወገቧን እንደጠፈረ ይኖራል፡፡ በአንድም በሌላም፣ አውቀነውም ይሁን ሳናውቀው፣ በራሳችን ይሁን በቤተሰባችን ምክንያት ወደ ሕይወታችን ሰርጎ የገባው የዛር አጋንንት ጀርባችን እና እግራችን ላይ ይቀመጣል፡፡ እኛም ዛር መሆኑን ስለማናውቅ ሐኪም ቤት እንሄዳለን፡፡ የዛር አጋንንቱ እራሱን በነርቭ በሽታ ስም እራሱን ይደብቃል፡፡ በሐኪምም የነርቭ ችግር ነው እንባላለን፡፡ መድኃኒት እንውጣለን፣ በፊዚዮ ቴራፒም እንታከማለን ግን ለውጥ የለም፣ ሕመሙም እንዳለ አለ፡፡ በነርቭ ስም የተደበቀው አጋንንት በቁርጥማት፣ በውጋት፣ እግራችንን በመሸምቀቅ፣ እንዳንራመድ እንዳንተኛ በማድረግ በግልጽ እና በስውር ይዋጋናል፡፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ ጥላ ወጊም ወይም የሞት አጋንንትም እራሱን በተለያየ በሽታ ይሰውራል፡፡ የጥላ ወጊ አጋንንት እኛን ለሞት ለማብቃት በልብ ሕመም እራሱን ይሰውራል፡፡ የጥላ ወጊ ወይሞ የሞት አጋንንት የተላከበት ሰው አጋንንቱ ልቡ ላይ ቁጭ ብሎ በድንገት ልቡን ከሥራ/ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ ሰውዬው በድንገት ‹‹ልቤን›› በማለት ሊሞት ይችላል፡፡ በሟቹ በድንገተኛ ሞቱ የተገናገጡ ቤተሰቦቹ አስከሬን ምርመራ ብለው ሆስፒታል ይወስዱታል፡፡ እዛም ድንገተኛ የልብ ሕመም ነው ተብሎ ይነገራል፡፡ ቤተሰብም ሟች በጠላቱ በጥላ ወጊ ሳይሆን በልብ ሕመም እንደ ሞተ ሰምቶ ይቀራል፡፡ ገዳይም በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ ሳይታወቅ ይቀራል፡፡ እዚህ ላይ ልብ የምትሉት በልብ በሽታ የሚሞተውን ሁሉ በጥላ ወጊ ነው ብላችሁ እንዳትደመድሙ፡፡ ምክንያቱም የጥላ ወጊ ሞት የራሱ የሆነ አጋንንታዊ ብልሃት አለው፡፡ ሌላው የጥላ ወጊ ወይም የሞት አጋንንት እራሱን በከፍተኛ እራስ ምታት እና ውጋት ሊደብቅ ይችላል፡፡ የጥላ ወጊ አጋንንት የተቆራኘው ሰው በድንገት በጤንነት ‹‹ወጋኝ፣ እራሴን አመመኝ›› በማለት ለሐኪም ቤት ደጃፍ ሳይደርስ በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ ስለዚህ የጥላ ወጊ ወይም የሞት አጋንንት ወደ ሕይወታችን ሲመጣ፣ ለሞት ሲቃጣ እራሱን በየትኛውም እና በምናውቀው በሽታ እራሱን ሰውሮ ለመቃብር ጓሮ ሊዳርገን ይችላል፡፡ ጥላ ወጊ ወይም የሞት አጋንንት ፖሊስ የማይደርስበት የማያውቀው፣ የተጎጂ ቤተሰብም የማይገነዘበው ነው፡፡ ሰውን በግልጽ የገደለን የአገሪቱ ሕግ ይዳኘዋል፡፡ ሰውን በጥላ ወጊ የገደለን እንኳን ሰው ሊዳኘው ሰውም ስለማያውቀው የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው ፍርዱንም የሚሰጠው፡፡ ወዳጆቼ ስንቱ በጥላ ወጊና/በሞት አጋንንት ሕይወቱም በማጣት ለቤሰተቦቹ የዘላለም ጸጸት ሆኗል፡፡ በክፍል ፫ የጥላ ወጊ ወይም የሞት አጋንንት ሁነኛ #መፍትሔ ምንድነው? የሚለውን በቀጣይ እናየዋለን። ይቀጥላል 09,34,71,63,36 ያማክሩኝ
መርጌታ ፀዳሉ የባህል መዳኒት ቀማሚ
Region: ET
Friday 23 October 2026 05:25:23 GMT
Music
Download
Comments
silkuw :
አሰራሩስ፣እዴነዉ
2026-11-13 15:32:46
0
Hancho :
አጠቃቀሙን
2026-11-12 09:47:25
1
አባ አለም ለምኔ :
ቡና እያለ አይነጥላ አይወጣም ቡና ዋናው የዛር ቀለብ ነው።
2026-11-08 13:43:42
1
getachew21-23 :
@
2026-11-04 16:03:58
1
Adugna Teso :
@
2026-11-05 11:13:17
1
To see more videos from user @mergattedalu, please go to the Tikwm
homepage.