@asse1219: የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት የሥራ ስንብት ክፍያ አፈጻጸም እና መግለጫ የሥራ ስንብት ክፍያ መብት (አንቀጽ 39)፦ የሥራ ውል ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሲቋረጥ (ለምሳሌ ድርጅቱ ሲዘጋ ወይም በሠራተኛ ቅነሳ)፣ አሰሪው ሕገ-ወጥ ስንብት ሲፈጽም፣ ወይም ሰራተኛው በአሰሪው ጥፋት ምክንያት ሥራውን ሲለቅ የስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። በሠራተኛው የዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት ለሚከሰት ስንብት ግን ክፍያ አይፈጸምም። የክፍያ መጠን ስሌት (አንቀጽ 40)፦ ለመጀመሪያው አንድ ዓመት አገልግሎት፦ የ1 ወር ሙሉ ደመወዝ ይከፈላል። ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ አገልግሎት፦ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት የደመወዙ 1/3ኛ (ሲሶ) እየታሰበ ይታከላል። ለአገልግሎት ገደብ፦ አጠቃላይ የሚከፈለው የስንብት ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም። የግብር አያያዝ፦ በገቢ ግብር አዋጁ መሠረት የስንብት ክፍያ ላይ የሚጣለው ግብር ከታችኛው የደመወዝ እርከን ጀምሮ ሠራተኛው በየዓመቱ እንዳገኘው ተደርጎ (Spread ተደርጎ) በልዩ ስሌት የሚታሰብ ሲሆን፣ ይህም ሰራተኛው ከፍተኛ ግብር እንዳይከፍል ይረዳል። Stay Tuned For More Information!
asse1219
Region: ET
Friday 23 October 2026 10:31:13 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @asse1219, please go to the Tikwm
homepage.