@debreberhanuniversity: 🎯 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም አዲስ ለተቀበላቸው ከ3ሺ በላይ ተማሪዎች የገለፃ እና የኦሬንቴሽን መድረክ አካሄደ ----------------   ጥቅምት 13/2019ዓ.ም፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ለገቡ ከ3ሺ በላይ አዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ገጽታ፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲሁም የውጤት አሰጣጥ ሥርዓትን በተመለከተ በሚመለከታቸው ባለሙያዎች አማካኝነት አጠቃላይ ገለፃ አደረገ።   በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ጌትነት አሸናፊ (ዶ/ር)፣ አዲስ የገቡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲውም ሆነ የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ ልጅ ተቀብሎ እንደሚንከባከባቸው ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በ2019 ዓ.ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ከ10 ሺህ በላይ ነባርና አዲስ ተማሪዎችን እንደሚያስተናግድ የገለጹት ዶ/ር ጌትነት፣ ተቋሙ «ትንሿ ኢትዮጵያ» በመሆኑ ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የተለያዩ ባህሎችንና ቋንቋዎችን ማወቅና መማር እንደሚችሉም ጭምር አስረድተዋል።   በተያያዘም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ለማ ንጉሴ (ዶ/ር) ተቋሙ ከዋናው ግቢ በተጨማሪ ሁለት ካምፓሶች እንዳሉት ጠቅሰው፣ በነዚህም የሚሰጡ የትምህርት ክፍሎችን፣ የመማር ማስተማር ሂደትን፣ እንዲሁም የውጤት አሰጣጥና የፈተና ሥርዓት እና ደንቦችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።   የተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ቆይታ የተሳለጠና ምቹ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ገለፃ የተደረገ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ዲን መምህር ስንታየሁ አምባቸው ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች፣ የሕግና ሥርዓት መመሪያዎችን አብራርተዋል። የላይብረሪ አጠቃቀምን በተመለከተ በአቶ ዋሱ በላይነህ፣ የዩኒቨርሲቲውን ሰላምና ደህንነት በተመለከተ በሳጅን አበበ መንግስቱ፣ እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ በመምህር ላቃቸው ያየህራድ ገለፃ ቀርቧል። በሌላ በኩል የተማሪዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ድጋፍን በተመለከተ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ኃላፊ ወ/ሮ አዲስ አስፋወሰን ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን፣ የተማሪዎች መረጃ አስተዳደር ባለሙያ መምህር ቢለው አለሙ ደግሞ የሬጅስትራር ሲስተምና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን በዝርዝር አቅርበዋል። #DebreBerhanUniversity #DBUPosts #DBUNEWS #DBUOfficial #DBUFreshStudents

Debre Berhan University
Debre Berhan University
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 23 October 2026 23:28:10 GMT
2795
148
2
15

Music

Download

Comments

user139061379406
Tade Bethy :
🙏🙏🙏 Respect
2026-10-24 03:37:32
0
_esb_19
𝓔𝓼𝓪𝔂𝓪𝓼_SB. :
ere remedial meche new mterun koy
2026-10-24 06:59:06
3
To see more videos from user @debreberhanuniversity, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About