@adugnakuma: ንጉሱ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚገኙትን ሦስት ሚኒስትሮች ሚኒስትሮች አስጠርቶ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ባዶ ጆንያ ሰጣቸው። ከዚያም "ወደ ቤተ መንግሥቱ ትልቅ አትክልት ቦታ ሂዱና የሚበሉ ምርጥ ፍሬዎችን ለቅማችሁ ጆንያችሁን ሞልታችሁ አምጡ።" አላቸው። ... የመጀመሪያው ሚኒስትር ፣ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ረጅም ሰዓት በማሳለፍ በጣም ምርጥ፣ የበሰሉና ንጹሕ ፍሬዎችን በጥንቃቄ መርጦ ጆንያውን ሞላ። ሁለተኛው "ንጉሡ እኮ እያንዳንዱን ፍሬ አይመረምርም። ዋናው ጆንያው መሙላቱ ነው" ብሎ በማሰብ ጥሩዎቹንም፣ የበሰበሱትንም፣ የወደቁትንም ፍሬዎች አደባልቆ በፍጥነት ጆንያውን ሞላ። ሦስተኛው " ንጉሡ ሥራ ስለሚበዛበት ጆንያውን ጭራሽ አይከፍተውም፤ በሩቁ አይቶ ብቻ ያልፋል" ብሎ በማሰብ ፍሬ ከመልቀም ይልቅ ሳር፣ ደረቅ ቅጠልና ድንጋይ በመሙላት ጆንያውን ሞላው። በማግስቱ ሦስቱም ሚኒስትሮች የተሞሉትን ጆንያዎች ይዘው በንጉሡ ፊት ቀረቡ። ንጉሡ ግን ጆንያዎቹን አልከፈታቸውም። ይልቁንም ዘበኞቹን ጠርቶ "እነዚህን ሦስት ሚኒስትሮች እያንዳንዳቸውን ከያዙት ጆንያ ጋር ብቻ ለየብቻቸው ወደታሰሩበት ጨለማ እስር ቤት ውሰዷቸው። ለሦስት ሳምንታት ያህል የሚመገቡት ነገር አይሰጣቸውም፤ ይዘውት የገቡትን ጆንያ ብቻ እየተመገቡ እንዲቆዩ አድርጉ!" ብሎ አዘዛቸው። ... የመጀመሪያው ያዘጋጀው ምርጥ ፍሬ ስለነበር ለሦስት ወራት ያህል በደስታና በጥሩ ጤንነት በላው። ሁለተኛው ደግሞ በጥሩና በበሰበሰ ፍሬ መካከል እየተቸገረና እያሰቃየውም ቢሆን በሕይወት ሰነበተ። ሦስተኛው ግን ጆንያው ውስጥ ሳርና ድንጋይ ብቻ በመሙላቱ በረሃብና በምግብ እጥረት ሕይወቱ አለፈች። ... በሕይወታችን የምንሠራው መልካም ወይም ክፉ ሥራ ሁሉ፣ በስተመጨረሻ እኛ ነገ የምንመገበውና የምንኖርበት ውጤታችን ነው፤ ዛሬ የዘራነውን ነገ በእርግጥ እንበላዋለን። ••••𝔸𝕕𝕦𝕘𝕟𝕒•••• #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #onthisday #creatorsearchinsights #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇦 🇩 🇦
Region: ET
Saturday 24 October 2026 11:38:14 GMT
Music
Download
Comments
obsinet shugute :
🥰🥰🥰
2026-10-24 11:53:08
1
neser 1 DLD :
✍️🥰🥰🥰🥰
2026-10-24 13:43:12
1
jeri :
🥰🥰🥰
2026-10-24 17:38:59
1
To see more videos from user @adugnakuma, please go to the Tikwm
homepage.