@girma.yimer_official: የእረኞች ዝምታ እስከ መቼ? ድምፅ ማሰማት የሞራልና የሕሊና ግዴታ ነው! ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳትና የአስተዳደር መሪዎች፦ 👉 ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ - ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 👉 ይድረስ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ - የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ 👉 ይድረስ ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ - የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ 👉 ይድረስ ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ - የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በእጅጉ በሚዘገንንና ልብ በሚሰብር ሁኔታ በአርሲ ምድር የሚገኙ ንጹሐን የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች በመጨፍጨፍ ላይ ናቸው። የእናንተ የእረኝነት ዘመን በታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍረው በዝምታ ወይስ በድምፅ? ሕዝባችን ዕለት ዕለት በግፍ እያለቀ እያለ የእናንተ የአባቶች ዝምታ ሕመማችንን አብሶታል። አንች አርሲ ነገሌ ህዝቦችሽ የሚያልቁት ሁሉም በየተራ ተሰየምልሽ ወይ የግልሽ ባንዲራ ደመከል የሆነ በደም የተሰራ 😭 አፉን ባልፈታ ልጅ ራሱን ባልቻለ አቅመ ቢስ አዛዉንት አይኑ የሰለለ በጨካኞች ጥይት ዛሬም ተገደለ 😭 👉 ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር ተባብሮ የመሥራቱ ትርጉሙና ፋይዳው ምንድን ነው? የመንግሥት ዋናውና ቀዳሚው ኃላፊነት የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ ካልሆነ ምን ዋጋ አለዉ? ቤተ ክርስቲያንና ልጆቿ ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ግፍና መከራ ሲወርድ ቀረብ ብሎ የሕዝብን እንባ መጥረግ እና ግድያዉን ካላቆማችሁ ምን አባት ሆናችሁ? «የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል» (ዘፍጥረት ፬፡፲) ይህንን ግፍ በዝምታ ማለፍ የታሪክ ትልቁ ተጠያቂነት ነዉ! ☑ «ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው» የሚለው አባባል፦ በአሁኑ ዘመን ጠላት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ፣ ካህናትን በግፍ ለመጨፍጨፍ እና ምእመናንን ከቀያቸው ለማፈናቀል በሚነሳበት ወቅት «ታገሱ፣ ጸሎት አድርጉ» የሚለው ብቻውን መፍትሄ ሊሆን አይችልም፤ ይህ አባባል አሁን ባለው የህልውና አደጋ ውስጥ መቅረት ያለበት ንግግር ነው። እምነትን፣ ንብረትንና ህይወትን መጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታ ነው። እኛ መሣሪያ ታጥቃችሁ ግጠሙ አላልንም፤ ነገር ግን የዜጎችን ሞት ችላ ያለውን መንግሥት፣ ዜጎቹን እንዲጠብቅና ፍትሕ እንዲያመጣ የአባትነት አደራችሁን ተወጡ ነው የምንለው! እኛ የምንፈልገው የገዳዮች የውስጥ ተላላኪ ሥራ አስፈጻሚ አባቶችን ሳይሆን፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያሉ ሕዝባቸውን እስከ ሞት የሚከላከሉ ቆራጥ እረኞችን ነው። እግዚአብሔርም ታሪክም እንዳይወቅሳችሁ የእረኝነት አደራችሁን እስከ መስዋዕትነት ድረስ ልትወጡ ይገባል። አምላከ ቅዱሳን በግፉ ለተገደሉ ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ነፍሳቸውን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ዕቅፍ ያሳርፍልን፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መጽናናትን ይስጥልን። ፍትሕ ለንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን! ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ይህንን መልዕክት ሸር (Share ፣ repost ) በማድረግ ለአባቶቻችን እንዲደርስ አድርጉ! #ፍትህለአርሲኦርቶዶክሳውያን#ድምፅ_ለሰማዕታት #የቤተክርስቲያን_ልጆች #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #ቅዱስሲኖዶስ
ነገ መሞት አለ 🕯️ትጉና ፀልዩ ማቴ 26፥41
Region: ET
Sunday 25 October 2026 08:35:38 GMT
Music
Download
Comments
Nahom 21 @ :
😭😭😭😭😭😭😭ፍትህ ለኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ
2026-10-25 09:28:15
0
ጌታ ሆይ የንስሀ ዘመን አድርግልኝ🙏❤️💔 :
😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-25 09:49:23
0
የተዋህዶ ፍሬ💗⛪ :
ፍትህ😭😭😭😭😭🙏
2026-10-25 11:53:24
0
ኪዳንምህረት እናቴ :
2026-10-25 10:03:52
0
💥ευλογία🔴🔴 :
ፍትህ ለ አርሲ ኦርቶዶክስ 🙏🙏🙏
2026-10-25 09:03:32
0
ህይወትያለእናትባዶናት💔😢 :
አህህ😢😢
2026-10-25 08:59:59
0
ኪዳንምህረት እናቴ :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-25 10:04:44
0
Keep your life private😎💒💝 :
[Teary eyed][Teary eyed][Teary eyed]
2026-10-25 11:23:12
0
A.Y23 :
🙏🙏🙏
2026-10-25 09:15:40
0
የጥበብ መጀመሪያ እግዚያብሔርን መፍራት ነው⛪️ :
🥺😭
2026-10-25 08:48:08
0
Tiz :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-25 14:14:56
0
To see more videos from user @girma.yimer_official, please go to the Tikwm
homepage.