@zekaryaskiros: እግዚአብሔር አምላክ ደማችሁን ያፍስሰው ! ምንም በማያውቁ ህጻናት ላይ የጭካኔ በትራችሁን የምትዘረጉ ምናምንቴ ሰዎች የቀን ጉዳይ ነው የሚሆነው እንጂ የዘራችሁትን የክፋት ማሳ እራሳችሁ ታጭዳላችሁ ። ለጭካኔያችሁ የምትሰጡት ቀፋፊ ትርክት የገዛ ክንዳችሁን አድክሞት ያሳየናል ። እንኳን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ደም አፍስሶ የእንስሳትን ደም በብላሽ ያፈሰሰ ሰው የገዛ ኅሊናው ተቅበዝባዥ ነው ። የቃየን ልጆች ሆይ አድምጡኝ ! የእግዚአብሔር ሰውን አቤልን የገደለ ቃየንን በምድር ያቅበዘበዘ አምላክ ዛሬም አለ ። በክርስቶስ አማናዊ ስጋ እና ደም የተንቆጠቆጠውን ክቡሩን የኦርቶዶክሳዊውን ወገናችንን ደም እንዳፈሰሳችሁ አትቀሯትም ። እናንተ የምድሪቱ እርግማኖች ለእናንተ የሚያሸበሽብ እጅ የሚቆራመድበት ጊዜ ፤ እናንተን ያጀገነ ጀሌ በሃፍርት የሚሸማቀቅበት ጊዜ ይመጣል ! ። የእነዚህን ምስኪናን ወገኖቻችንን ደም እየነከራችሁ ቆሻሻ የሆነ ፖለቲካችሁን እና ጸረ ኦርቶዶክስ ትርክታችሁን የምትጽፉ ፣ ሰው ሆናችሁ ተፈጥራችሁ ከአውሬ የከፋችሁ ደካሞች ሆይ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ስለ እናንተ ግፍ የሚጮኸ ጩኸት አለ ! "በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ ራእ 6 10 እኛ ከተበቀልናችሁ ቅጣታችሁ ውስን ነው የሚሆነው ። እንዳያዳግም አድርጎ ፣ ለሰው መተረቻም አድርጎ የሚበቀል ስሙ እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለን ! ። ጊዜው አጥሮ የእጃችሁን ታገኙ ዘንድ በጸሎት እንተጋለን። "ዕውቀትን እሱን መፍራትንም እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ ስለመኳንንትና ሥልጣን ስላላቸው እንማልዳለን" እያለች ዘወትር በቅዳሴዋ የምትጸልይላችሁ ባለሥልጣኖቻችን ሆይ ! እግዚአብሔር ሰፍሮ እና አትሞ የሰጣችሁን ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ካላደረጋችሁ ሹመታችሁ ሺ-ሞት እንደሆነባችሁ አታውቁምን !? ። ባለሥልጣን ማለት በV8 ተሳፍሮ በሕዝብ መካከል እየከነፈ መንጎድ ብቻ ሳይሆን ሕዝብን ከልብ መውደድ ጭምር እንደሆነ እኔ ስነግራችሁ እደነቃለሁ ! ። በአርሲ ላይ ስንት ጊዜ ? የኦርቶዶክሳዊያን ደም ፈሰሰ !? ፣ በአርሲ ላይ ለፈሰሰው ኦርቶዶክሳዊያን ደም የትኛው የወረዳ አስተዳዳሪ "ኃላፊነትህን አልተወጣህም" ተብሎ ተወቀሰ !? በህግስ ተጠየቀ !? ። አዝናለሁ ! በእውነት በጣም አዝናለሁ 💔 ቃልም ንግግርም የለኝም ! ለህጻንም አልራሩ ፣ የሽማግሌውንም ገጽ አላፈሩም 😥 Zekaryas Kiros

zekaryas kiros
zekaryas kiros
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 25 October 2026 15:11:52 GMT
81006
14282
442
1845

Music

Download

Comments

user744930443879
መአዛ :
[Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying]ፈጣሪ ሆይ በቃችሁ በለን
2026-10-26 04:49:21
0
zedsiyoum
@zed :
ጌታ ሆይ አረ በቃ በለን[Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying]
2026-10-26 06:00:37
0
mimi631495
mimi :
የነዚህ ህፃናት አምላክ ይፈርዳል ያኔ የት ይገቡ ይሆን!!!!
2026-10-26 05:01:58
61
tizitatedla2
@tizita tedla :
Err Fetari derseln🥺😥
2026-10-25 20:23:03
0
eyoba602
Eyob United :
lemn beseferachin anijemrm gn
2026-10-25 18:59:30
0
yemikael05
®+NATANEM+ :
አንዲት እንቁራሪት ኩሬ ውስጥ ሆና ማዶ ላይ ቤት ሲቃጠል ታያለች።ወዲያው የሆነ ሰው በአጠገቧ ሲያልፍ ታይና ለፖሊስ ስልክ እንዲደውል ትነግረዋለች። እሱም ተገርሞ እሳቱ ያለው ማዶ አንችን ምን አስጨነቀሺ በማለት ጠየቃት? እሷም እንዲህ መለሰችለት:- 'አየህ እሳቱ እዚያ እያለ ካላቆምነው እዚህ ይመጣል። እሱም ቀጠል አድርጎ ታዲያ አንች ያለሺው ውሃ ውስጥ እንዴት ያገኝሻል ቢላት እሷም ለእሳቱ ውሃ ሲቀዱ እኔንም አብረው ሊወስዱኝ ይችላሉ ብየ ነው በማለት ስጋቷን ነገረችው። ሰውየውም ጥሏት እንደሄደ ወደጫካው ሲጋባ ድንገት የቤቱ እሳት ወደጫካው ገብቶ መሃል ላይ ይከበዋል። የእንቁራሪቷ ሃሳብ ትዝ ቢለውም ምንም በማይጠቅምበት ጊዜ ሆነ። . . . እኛም ዛሬ የአንድ ሰው ሞት ምንም ካልመሰለን፣ዛሬ የአንድ ሰው ቤት ሲፈርስ ምንም ካልመሰለን፣ ዛሬ የሌላ ቤተ እምነት ሲፈርስ ምንም ካልመሰለን. . . ነገ እንደ ሰውዬው የማንሆንበት ምክንያት አይኖርም።
2026-10-26 14:42:56
5
neba4redi
NebyuXRedet :
😭😭😭orthodox
2026-10-26 07:24:10
0
minilikdesta
Minilik Desta :
God God
2026-10-26 08:12:41
0
zinu5136
zinu :
ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክስ
2026-10-25 17:49:25
30
kuloha81
kuloha81 :
ጌታ ሆይ በቃ ናልን😭😭😭😭😭👏👏
2026-10-25 15:27:47
46
user71529753838012
ኮኪ ባለማህተቧ :
:ምን ዋጋ አለው ባለፈውም እንዲህ ሰው በሰው ተበልቶ ምን መፍትሄ ተፈጠረ ምንም አሁንም የ1ቀንና የ2 አጀንዳ ቢሆን ነው ከዛ ይረሳሉ እረ በሰምአብ ፈጣሪ ሆይ ድረስላቸው😭😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏አርሲ የፍትህ ያለህ እ
2026-10-26 10:50:34
7
user5732269906815
fikr :
ምን እንደምል አላቅም እኔን
2026-10-26 13:43:09
2
haymanot016
haymi ሄይሚ :
😥😥የኛ ጌታ አምላክ ገዳዮችን የፀፀት ልቦና ስጣቸዉ ሰማዕታት በረከታችሁ ይደርብን በሀይማኖታችሁ ፀንታችሁ ወደ አባታችሁ እቅፍ ነዉ የሄዳችሁት
2026-10-25 16:27:42
21
meskerem.tliaye
Meskerem Tliaye :
እኔ ድፍት ልበልል የኔ አባት 🥺🥺አንተ በምን እዳህ
2026-10-26 07:15:09
7
nolawi35
nolawi :
ኦርቶዶክሶች አታልቅሱ ማልቀስ አይጠቅመንም እንነሳ ሰላማዊ ሰልፍ እንዉጣ አዲስ አበባ ላይ እስከመቼ ነዉ ፈርተንም ሞተንም የምንዘልቀዉ እረ ተዉ ባካችሁ ተዉ 😭😭
2026-10-25 22:06:34
6
maza4361
maza@4361 :
ፈጣሪሆ በቃችሁ በለን
2026-10-26 09:48:18
3
makbellulittesfay
makbellulittesfay :
ጌታ ሆይ ማረን😭😭😭😭
2026-10-25 21:21:13
4
hanatakkele1
paramera :
ይድፋኝ
2026-10-26 07:44:14
3
ferweyn
ፍረወይኒ ሀብቴ :
ምን ይሻላል 😢😢😢😢
2026-10-25 16:18:41
8
with1944
with :
ባዕድ አገር ኢትዮጵያ ውስጥ ቢገባ ከዚህ የከፋ ምን ያደርገናል? ሉአላዊነት ትርጉሙ ምንድን ነው? ሃገር ማለትስ ምን ማለት ነው? ማንንስ ይይዛል? መንግስትስ የማን ነው? ምንድን ነው አስፈላጊነቱስ?
2026-10-25 16:47:25
2
tabotetsionmariam21
Axsum Tsion Mariam :
የኔ ፍቅር😭😭😭😭😭😭
2026-10-25 18:08:17
3
bitaniya6121921
ቢታኒያ yemsihu liji☦️ :
እግዚአብሔር ሆይ አው እኔ በጣም ነቆሸሽሁ ሐፂአተኛ ነኝ ግን አንተ ደግሞ ይቅር ባይ አምላክ ነህ እባክህ አምላኬ በግፍ ለሚታረዱት ለሚገደሉት ፍረድልኝ አባቴ እባክህ እራራልን እዘንልን ፍትልሕን ካንተ ከፈጣሪ እንሻለን እባክህ ጌታ ሆይ🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤💔💔💔💔💔
2026-10-25 23:06:59
2
nigist_210
City2112 :
ለሰው መተረቻም አድርጎ የሚበቀል ስሙ እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለን!🤲
2026-10-26 06:50:32
1
kiduesn
kidusan :
የኔ አባት አንተላይ ጥይት እንደት ጨከኑ
2026-10-26 06:42:21
1
To see more videos from user @zekaryaskiros, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About