@birhane_abaw: ለኢትዮጵያ መንግሥት ያለኝ አሳብ በአርሲና በአካባቢው ክርስቲያኖች ላይ በሚደርሰው መከራ፣ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል እና እጅግ ስልታዊ ጥቃት ለእኔ ከማንም በላይ የመጀመሪያው ተጠያቂ የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥ የሚቃወሙት ሰዎች መካከል ሁለት ሦስቱ ባሉበት ድሮን በመተኮስ፣ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት በማድረስ በማንም ዘንድ የታወቀ መንግሥት ነው። ከፈለገ ሱዳን ገብቶ፣ ሲፈልግም ሶማሌ ተሻግሮ የሚዋጋ፣ ፍላጎቱን ለመፈጸም የማያመነታ መንግሥት እንደሆነ በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ከትግራይ ጋር በነበረው ጦርነት በሚዲያ በኩራት ይናገር እንደነበረው የሕወሓትን መሪዎች በተንቤን ዋሻዎች ውስጥ ከሚስቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የሚያይ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ አየዋቸሁ ብሎ የሚተኩስ መሆኑን ደጋግሞ በሚዲያ ራሱ ነግሮናል። ‘’ከጠላቶቼ ጋር ያለ ሁሉ ያለምንም መሣሪያ መረጣ ይመታል’’ ሲል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የሰማነው በራሱ በመግሥት ሚዲያ ነው። እንዲህ ያለ ‘ረቂቅ ቴክኖሎጂ የታጠቀና ብቃት ያለው መንግሥት’ በየጊዜው በበርካታ ወረዳዎች ከደርዘን በላይ እየገደሉ፣ እያፈኑና እያገቱ የሚሔዱ አርሲ ውስጥ ያሉ አጥቂዎችን ለማየት እንዴት ተሳነው? ወይስ ማየት የሚችለው ወደ ሰሜን ሲሆን ብቻ ነው እንዴ? ለእኔ ገዳዮቹን ለማጥቃት ባይፈልግ እንኳ ሟቾቹን ለማዳን የሚቸገርበት ምንም ምክንያት አይታየኝም። ምክንያት አለ ከተባለ ብቸኛው ምክንያቱ ፍላጎት ማጣቱ ብቻ ይመስለኛል። ለማዳን ፍላጎት ቢኖረው በፍጹም እንዲህ ሊሆን አይችልም። አንዴ፣ ሁለቴም፣ ሦስቴም፣ አራቴም ተዘናጋ እንበል። በየወሩ፣ በየሳምንቱ ፣ ዓመቱን ሙሉ፣ ለተከታታይ ዓመታት ይህ ሁሉ ሲፈጸም ተጎጂዎችን ካላማዳኑ በላይ በጣም የሚያበሳጨው ፣ መግለጫና ማስፈራሪያ የሚያስወጣው፣ መከራውን በሚዘግቡ አካላት ላይ መሆኑ ፍላጎቱን ያሳብቅበታል። ለእኔ የአርሲ ክርስቲያኖች ሞት የመንግሥት ፍላጎት አይደለም ለማለት የሚያስችል አንድም ምክንያት አግኝቼ አላውቅም። እንዲያውም በቂ ምክንያት ያለው በተቃራኒው ያለውን ለማመን ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መረዳቴን ደግሞ ለራሱ ለመንግሥትም ቢሰማም ባይሰማም፣ ለዓለም ማኅበረሰብም ቢያደርግም ባያደርግም መናገር ክርስቲያናዊ ግዴታየ ነው ብዬ አምናለሁ። መንግሥት ፍላጎቱ የዜጎቹ ደኅንነት መጠበቅ ከሆነ አርሲ ውስጥ ሰላም ማምጣት በጣም ቀላል እንኳ ባይሆን በፍጹም ከባድ ድርጊት እንዳልሆነ ግን አምናለሁ። ከድርጊቱ የምረዳው ግን ፍላጎቱ አይደለም። ይህን በቃል እንዲነግረኝ አልጠብቅም። ይኸው ይኸንን ሁለት ቀናት እንኳን የአርሲ ሀገረ ስብከት ያወጣቸውን የድረሱን መግለጫዎች ሰሚ አለማግኘታቸውንና የሚመለከተው አካል ደግሞ ዝምታው ከላይ ያልኩትን ከማጽናት በላይ ናቸው፡፡ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
ብርሃነ አበው
Region: ET
Monday 26 October 2026 07:14:52 GMT
Music
Download
Comments
sew mehon ... :
Ewnet new ! Memhrachen Brhanu Admas EGZEABHAR Amlak yetebkelen
2026-10-27 07:55:21
0
emahoy :
ዋናዉ ገዳይ አስገዳይ መነግስት ነዉ
2026-10-26 16:25:00
2
efi :
ገዳዮቻችን በመንግስት እውቅና ነው
2026-10-27 10:18:17
0
fitsum zewude :
እውነት ነው
2026-10-26 12:51:31
1
Alemu Yirdaw :
እኛ ጉዳዩ አደለንም
2026-10-27 02:27:38
0
jo :
በትክክል
2026-10-26 15:54:32
0
Add+KU :
በጣም ያማል!!!!
2026-10-26 14:50:48
0
Tsegish :
እውነት ነው
2026-10-26 15:15:58
0
ንጉሥ :
ለኢትዮጵያ መንግሥት ያለኝ አሳብ
በአርሲና በአካባቢው ክርስቲያኖች ላይ በሚደርሰው መከራ፣ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል እና እጅግ ስልታዊ ጥቃት ለእኔ ከማንም በላይ የመጀመሪያው ተጠያቂ የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥ የሚቃወሙት ሰዎች መካከል ሁለት ሦስቱ ባሉበት ድሮን በመተኮስ፣ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት በማድረስ በማንም ዘንድ የታወቀ መንግሥት ነው። ከፈለገ ሱዳን ገብቶ፣ ሲፈልግም ሶማሌ ተሻግሮ የሚዋጋ፣ ፍላጎቱን ለመፈጸም የማያመነታ መንግሥት እንደሆነ በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ከትግራይ ጋር በነበረው ጦርነት በሚዲያ በኩራት ይናገር እንደነበረው የሕወሓትን መሪዎች በተንቤን ዋሻዎች ውስጥ ከሚስቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የሚያይ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ አየዋቸሁ ብሎ የሚተኩስ መሆኑን ደጋግሞ በሚዲያ ራሱ ነግሮናል። ‘’ከጠላቶቼ ጋር ያለ ሁሉ ያለምንም መሣሪያ መረጣ ይመታል’’ ሲል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የሰማነው በራሱ በመግሥት ሚዲያ ነው። እንዲህ ያለ ‘ረቂቅ ቴክኖሎጂ የታጠቀና ብቃት ያለው መንግሥት’ በየጊዜው በበርካታ ወረዳዎች ከደርዘን በላይ እየገደሉ፣ እያፈኑና እያገቱ የሚሔዱ አርሲ ውስጥ ያሉ አጥቂዎችን ለማየት እንዴት ተሳነው? ወይስ ማየት የሚችለው ወደ ሰሜን ሲሆን ብቻ ነው እንዴ?
ለእኔ ገዳዮቹን ለማጥቃት ባይፈልግ እንኳ ሟቾቹን ለማዳን የሚቸገርበት ምንም ምክንያት አይታየኝም። ምክንያት አለ ከተባለ ብቸኛው ምክንያቱ ፍላጎት ማጣቱ ብቻ ይመስለኛል። ለማዳን ፍላጎት ቢኖረው በፍጹም እንዲህ ሊሆን አይችልም። አንዴ፣ ሁለቴም፣ ሦስቴም፣ አራቴም ተዘናጋ እንበል። በየወሩ፣ በየሳምንቱ ፣ ዓመቱን ሙሉ፣ ለተከታታይ ዓመታት ይህ ሁሉ ሲፈጸም ተጎጂዎችን ካላማዳኑ በላይ በጣም የሚያበሳጨው ፣ መግለጫና ማስፈራሪያ የሚያስወጣው፣ መከራውን በሚዘግቡ አካላት ላይ መሆኑ ፍላጎቱን ያሳብቅበታል። ለእኔ የአርሲ ክርስቲያኖች ሞት የመንግሥት ፍላጎት አይደለም ለማለት የሚያስችል አንድም ምክንያት አግኝቼ አላውቅም። እንዲያውም በቂ ምክንያት ያለው በተቃራኒው ያለውን ለማመን ነው፡፡
ስለዚህ ይህን መረዳቴን ደግሞ ለራሱ ለመንግሥትም ቢሰማም ባይሰማም፣ ለዓለም ማኅበረሰብም ቢያደርግም ባያደርግም መናገር ክርስቲያናዊ ግዴታየ ነው ብዬ አምናለሁ። መንግሥት ፍላጎቱ የዜጎቹ ደኅንነት መጠበቅ ከሆነ አርሲ ውስጥ ሰላም ማምጣት በጣም ቀላል እንኳ ባይሆን በፍጹም ከባድ ድርጊት እንዳልሆነ ግን አምናለሁ። ከድርጊቱ የምረዳው ግን ፍላጎቱ አይደለም። ይህን በቃል እንዲነግረኝ አልጠብቅም። ይኸው ይኸንን ሁለት ቀናት እንኳን የአርሲ ሀገረ ስብከት ያወጣቸውን የድረሱን መግለጫዎች ሰሚ አለማግኘታቸውንና የሚመለከተው አካል ደግሞ ዝምታው ከላይ ያልኩትን ከማጽናት በላይ ናቸው፡፡
ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
2026-10-26 13:52:38
2
አምላኬሆይ ያተ እጂ የሰው ጥገኛ አታድርገኝ :
😳😳😳
2026-10-26 14:10:38
1
አምላኬሆይ ያተ እጂ የሰው ጥገኛ አታድርገኝ :
😳😳😳
2026-10-26 14:08:02
0
አምላኬሆይ ያተ እጂ የሰው ጥገኛ አታድርገኝ :
😳😳😳
2026-10-26 14:08:45
0
አምላኬሆይ ያተ እጂ የሰው ጥገኛ አታድርገኝ :
🥰🥰🥰
2026-10-26 14:10:25
0
አምላኬሆይ ያተ እጂ የሰው ጥገኛ አታድርገኝ :
🥰🥰🥰
2026-10-26 14:08:02
0
ሄላ የእመአአምላክ ባሪያ :
@ሄላ የእመአአምላክ ባሪያ:ፍትህ እረኞች ለተዋቸው ለአርሲ ኦርቶዶክሳውያን አርሲ ትጣራለች
2026-10-26 07:46:11
1
To see more videos from user @birhane_abaw, please go to the Tikwm
homepage.