@yewendlij0: ይህ ሕፃን በአንገቱ ላይ ያሰረው መስቀል ምን እንደሆነ እንኳን ትርጉሙን አያውቅም ምናልባትም አፉን አልፈታም። - ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩ :- ዓመቱን ሙሉ የሚሠራ መምሪያ እንዲኖር ስለመጠየቅ ይህ ሕፃን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ምናልባትም አፉን አልፈታም። በአንገቱ ላይ ያሰረው መስቀል ምን እንደሆነ እንኳን ትርጉሙን አያውቅም። ሃይማኖቱንም ዘሩንም ፖለቲካም ኢኮኖሚም አያውቅም። የሚስበቅ የሚሮጥበትና የሚጫወበት እንጂ የሚማርበት የሚሠራበት ዕድሜ ላይ እንኳን አልደረሰም። ይህንን አይተን እንቅልፍ እንዴት በዓይናችን ይዞራል? እንዴትስ ልንረሳው እንችላለን? እኛ እንዲህ ከታመምን እዚህ ሕፃን ላይ ሰይፍ ያሳረፉ እንዴት ተኝተው ያድሩ ይሆን? የዚህ ሕፃን ኃጢአት ያልሠራች ነፍስ እግዚአብሔር ፊት ስትቆም ምን ብላ ታስፈርድ ይሆን? እሳት አይዘንብ ይሆን? ይህ ሕፃን በአርሲ ክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ምን ላይ እንደደረሰና ቢሳካላቸው ለእኛም የሚያስቡትን ጥጉን ማሳያ ነው። እንደዚህ ሕፃን ንጹሕ ብትሆኑም አይቀርላችሁም ነው። ምንም ብንል ይህን መልአክ የመሰለ ሕፃን አይቶ የማያዝን አካል ሊያዝንልን አይችልም። አምና ልክ ይህን ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃት ደረሰ። በበኩሌ በሶሻል ሚድያ በዚህ https://www.facebook.com/share/p/19mnnoAPQK/?mibextid=wwXIfr ማስፈንጠሪያ ላይ የምታነቡትን ጽሑፍ ጻፍሁ። ብዙዎችም የተሰማቸውን ኀዘንና ቁጭት በታያቸው መንገድ ገለጹ። ሆኖም ተጯጩኸን ምንም ያህል ለውጥ ሳይመጣ ተረሳ። መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመቀየር ምንም ነገር ስለማንሠራ ‘ጮኸው ፣ ጮኸው ይተዉታል’ ከመባል በስተቀር ምንም አላተረፍንም። ገዳዮቻችን ግን አላማቸውን አልረሱትም አዘናግተው ደገሙት። ድጋሚ ሲከሰት ያንኑ ዓይነት ጽሑፍ ደግሞ መጻፍ ‘ተመሳሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ’ እንደሆነ ታየኝ። እውነት ለመናገር ‘እገሌ ምነው ዝም አለ?’ ላለመባል የሚደረግ ማስመሰልም ሆኖ ታየኝ። እንደዛ ከማድረግ ደግሞ ከልብ የሆነ ጸሎትና ዝምታ ይሻላል። በስልታዊ ዕቅድ (strategy) የሚደረግን ጥቃት ምንም ስልት በሌለው (non- strategic) መንገድ ለመፍታት ስለምንሞክርም ምንም ነገር መለወጥ አልቻልንም። በዚህ ምክንያት ከሌላው ቀድሞ በመጮህ ለቤተ ክርስቲያን የበለጠ አሳቢ መስሎ መታየትና ሌሎችን የማሳጣት መብት መጎናጸፍ እንደ ስኬት እየታየ መጣ። ሞትን ከማስቆም ይልቅ ‘ማን የበለጠ አለቀሰ?’ የሚለው የራስን ጽድቅ የማስመዝገብ (virtue signaling) እሽቅድድምና ‘እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ’ ዓይነት የማርታ ክስ አየሩን ይዞት ዋናው ጉዳይ ተዘነጋ። አሁንም እንደዚህ ሕፃን ያሉ ንጹሐን ከግፍ አላመለጡም። በዚህ ዙር የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ግን በቀጥታ ሀገረ ስብከቱም ቅዱስ ሲኖዶስም ቀድመው ምላሽና መረጃ ስለሠጡ እንደዚሁም ከየአቅጣጫው ችግሩን የመተንተንና መፍትሔ የመጠቆም ዝንባሌዎች እየተበራከቱ ስለመጡ አሁን ድረስ በምልዓተ ጉባኤ ላይ ካለው ከቅዱስ ሲኖዶስ ምን ይጠበቃል? በሚለው ላይ የበኩሌን ሃሳብ ለማዋጣት ዕድል የሚሠጥ ሆኖ ታየኝ። . ስለዚህ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ግድ ሆነብኝ። የምጽፈው ‘ብለን ነበር ሰሚ አጥተን ነው እንጂ’ ብሎ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለመመጻደቅ ሳይሆን ውሳኔ ሰጪ አካላት ቢመለከቱት የሚያጤኗቸው ሃሳቦች ከተገኙ በሚል ነው። ከቅዱስ ሲኖዶስ ምን እንጠብቃለን? ቅዱስ ሲኖዶስ በተመሳሳይ ጥቃቶች ወቅት እስከ አሁን ያደረጋቸውን ምላሾች በዝርዝር እንመልከታቸው። የሰማዕትነት ክብር ስም መሥጠት (ለሊብያ ሰማዕታት) ፣ ጸሎተ ምሕላና ፍትሐት ማድረግ ፣ ጥቃቱን በሀገረ ስብከት ደረጃ ፣ አለዚያም በቅዱስ ሲኖዶስ በማውገዝ መግለጫዎችን ማውጣት ፣ የመንግሥት አካላትን በግንባር ቀርቦ ማነጋገር ፣ ተጎጂዎቹን ወደ ሥፍራው ሔዶ ማጽናናት ፣ ማኅበራትንና ምእመናንን በማስተባበር ተፈናቃዮችን መደጎም ናቸው። እነዚህ ምላሾች ቀስ በቀስ እየቀዘቀዙ የመጡ ሲሆን በተናጠል አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ለብቻቸው መግለጫ በማውጣት ፣ የተራድኦ ሥራ በመሥራት እንደ ሲኖዶስ ምላሽ ያልተሠጠበትን ሁኔታ በራሳቸው ለመወጣት የሞከሩባቸው ጊዜያትም ነበሩ። የተወሰዱት እርምጃዎች ግን ችግሩን በመፍታት ረገድ ያደረጉት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ በመሆኑና ነገሮች ተባብሰው በመቀጠላቸው የነበሩት ምላሾችም ቀስ በቀስ ቀርተዋል። በዚህ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱን ‘ለመንጋው የማይገደው’ እረኛ አድርጎ በማየት ተስፋ የቆረጠውና ከእንግዲህም ምንም የማይጠብቀው ሰው ቁጥር እንዲበዛ ምክንያት ሆኗል። ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩት በመንፈሳዊ ትምህርታቸው እና በገዳማዊ ሕይወታቸው ተመልምለው እንጂ ከጥቂቶች በስተቀር በአስተዳደር ዘርፍ በትምህርትና በሥራ ሲዘጋጁ ኖረው እንዳልሆነ ይታወቃል። በእርግጥ መንፈሳዊነት ከተኖረበት ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር በቂውና ዋነኛው መሣሪያ ነው። የቤተ ክርስቲያን ችግርም የሚፈታው በጠረጴዛ ዙሪያ ከሚደረግ ውይይት በላይ በመንበሩ ዙሪያ በሚደረገው ቅዳሴ መሆኑ የታወቀ ነው። ቤተ ክርስቲያን ክፉ ዘመናትን የተሻገረችው በብልጣብልጥ አዋቂዎች ሳይሆን በየዋሃን መናኞች መንፈሳዊ ብልሃት እንደነበረ ታሪክ ያስታውሰናል። ነገር ግን ሐዋርያው ‘ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ’ እንዳለው ሆኖም ያለንበት የቀበሮና የተኩላ ዘመን በመሆኑ በፍልጥ የመጣውን በፈሊጥ የማስተዳደር ጥበብን የሚጠይቅ ዘመን ነው። እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ እና እነ ቅዱስ ባስልዮስ ከባዱን ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ያሳለፏት የዘመኑን ጥበብ በመማራቸው እና የአስተዳደርም የንግግርም ጥበባቸው ዓለም ከነበራት የሚበልጥ እንጂ የሚያንስ ስላልነበረ ነው። ሊቃነ ጳጳሳት በሰሞነኛነት ፣ በገዳም አበምኔትነት ፣ በደብር አለቅነት ፣ በሰባኬ ወንጌልነት ፣ በወረዳ ቤተ ክህነት ኃላፊነት ፣ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የሥራ ልምድ አካብተው ፣ በሁሉም መዋቅር ውስጥ ሠርተው ተፈትነው ወደሚበልጠው ሲመት ሲደርሱ በቀላሉ ማስተዳደር የሚችሉ ይሆናሉ። በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አገላለጽ ‘ተቋማዊ እንክብካቤ ሳያገኙ’ ከባድ የኃላፊነት ሸክምን በአንድ ጊዜ የተረከቡ አባቶች ከሆኑ ግን ሸክሙ ይከብዳቸዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥቂት ዐሠርት ዓመታት በፊት ለጵጵስና ከመሾምዋ አስቀድማ ልጆችዋን ወደ ልዩ ልዩ ሀገራት ለከፍተኛ ትምህርት እየላከች ለዓመታት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ፣ የሌሎች ሀገራትን ልምድ እንዲቀስሙ ታደርግ ነበር። በዚህም ምክንያት እንደ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዓይነት ጳጳሳትና እንደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዓይነት ፓትርያርኮች ኖረዋት አስደናቂ አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መሠረት ማስጣል ችላ ነበር። ይህ ዓይነቱ ልምድ አሁን አሁን ጨርሶ እየቀረ የመጣና ምናልባት መረጃ አጥሮኝ ካልሆነ በቀር ቤተ ክርስቲያን ‘እዚህ ሔደህ ተምረህልኝ ና’ ብላ ለነገ የምታዘጋጀው ሰውም የለም። ካሉትም አባቶች በዕድሜ ገና የሆኑ ብዙ መሥራት የሚችሉ አባቶችን ምን ዓይነት ድጋፍ ቢደረግላቸው የበለጠ መሥራት እንደሚችሉ ስላልታሰበበት አቅም እየባከነ እንዳለ ይታያል። ሄኖክ ሀይሉ
hayemi
Region: SA
Monday 26 October 2026 10:06:26 GMT
Music
Download
Comments
𝐌👄𝐌𝐫𝐢𝐭𝐢👭Ⓜ︎♥️🍫🍭 :
[Crying][Crying][Crying][Crying][Crying][Crying]ኡፍፍፍ
2026-10-26 16:38:15
0
Rita :
የኔአባት[Crying][Crying][Crying]
2026-10-26 14:42:42
0
የድንግል ልጅ :
Abet chekane........fetari yiferedebachew
2026-10-26 17:30:34
1
ሁን ያለው አይቀርም :
ኡፍፍፍፍፍፍፍ አቤቱ በቃህ በለን😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 19:34:37
2
ሰላሜ ነሽ ድንግል :
ፍትህ ለአርሲ😭😭😭😭
2026-10-27 00:28:28
0
sannaayit negash :
uuuuuuuuuuuuuu😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 14:11:27
1
Adii :
fiti larsi ortodokis
2026-10-26 17:22:30
1
hawe :
2026-10-26 23:51:22
0
my😘 :
2026-10-26 20:59:36
0
my😘 :
2026-10-26 20:59:18
0
my😘 :
2026-10-26 20:59:13
0
አድራሻዬ ከመሰቀሉ ስራ ነው 💒💒✝️❣️ :
😭
2026-10-26 20:49:40
0
Adona selale💍 :
🥺🥺🥺🥺😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 22:47:59
0
my😘 :
2026-10-26 20:59:29
0
Hana 2712🦋 :
😭😭😭
2026-10-26 23:43:19
0
ዜድ የሰማእቱ ልጅ :
እረ ፍትህ አርሲ😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 20:34:35
0
ነኚ።ባለማህተቧ :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 20:24:13
0
ለኔስ እናቴ ማርያም ናት :
ሰው በሰው እዴት የጨክናል ያው በህፃን
ጌታ ሆይ እባክህን ተመልከተን
2026-10-26 20:35:03
0
ዜድ የሰማእቱ ልጅ :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 20:33:30
0
ቅዱስ ገብርኤል አተ ጠብቀኝ❤❤❤ :
😭😭😭
2026-10-26 20:24:24
0
እግዛ ብሄርይመሠገን 💯 💕 :
2026-10-26 10:50:18
0
To see more videos from user @yewendlij0, please go to the Tikwm
homepage.