@alarz.green: في أطيب من هيك كعكة !🥯💚 . . للطلب و خدمتكم بشكل أفضل وسريع يرجى التواصل على الارقام التالية📲:(03/383620)(76385620)(06385620) #حلويات_الارز_الاخضر #حلويات #حلو_عربي #حلويات_عربية #كنافة_بالفستق

حلويات الارز الاخضرalarz green
حلويات الارز الاخضرalarz green
Open In TikTok:
Region: LB
Monday 26 October 2026 11:09:07 GMT
128185
840
11
476

Music

Download

Comments

dr.ashrafbash
Dr:Ashraf bash :
دمار للصحه
2026-10-26 16:49:34
1
raven7_08
𝓡𝓐𝓥𝓔𝓝 :
Wen 3enwen mahal plz?
2026-10-26 14:18:08
0
msri368
ابو المعتصم بالله المصري :
شو سعرا اخي
2026-10-26 16:32:26
0
mona.art.2
Mona Art~More Than Art~ :
ضمار هيك شوفة بهليل
2026-10-26 16:18:49
0
abu.altyaib
أبوالطيب الدرعاوي 🇸🇾 🇸🇪 :
🥰
2026-10-26 16:42:35
0
aboomaar43
ابـو عــمــر 🍂 :
وين محلك معليم
2026-10-26 15:22:43
0
omalbaraa95
أم البراء :
شو سعرا؟
2026-10-26 14:21:07
0
user4707761731841
حياة الروح :
2026-10-26 13:34:28
0
ali84271
ali :
❤️❤️❤️
2026-10-26 16:47:42
0
To see more videos from user @alarz.green, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ደስ አለኝ 🫠 ✍️በየዘመኑ ድንቅ ብዕረኞች ይፈጠራሉ ከታላላቆች የተማሩትን ያወቁትን የጠነከረውን አይረሴ የሙዚቃ ስንዳሬዎችን ለመረከብ አልጋ ወራሽነታቸውን ያበረታሉ በፅናትም ይተጋሉ ሆኖም ግን
ደስ አለኝ 🫠 ✍️በየዘመኑ ድንቅ ብዕረኞች ይፈጠራሉ ከታላላቆች የተማሩትን ያወቁትን የጠነከረውን አይረሴ የሙዚቃ ስንዳሬዎችን ለመረከብ አልጋ ወራሽነታቸውን ያበረታሉ በፅናትም ይተጋሉ ሆኖም ግን "ብዙ ጊዜ የግጥም እና የዜማ ማህንዲሶችን [ደራሲዎች] ስማቸውን አጉልቶ ማውጣት በህግ የተከለከለ እስኪመስል ባላየ ሲታለፉ ማየት ሊጠገን የሚገባው የዘርፉ ስብራት ነው። ይሁንና አሁን አሁን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ስብራቱ እስኪጠገን ማይጠብቁ በዘመናዊው የሙዚቃ አብዮት ጉዞ ድንቅ የሙዚቃ ግጥም ደራሲዎችን ለማየት ችለናል። ታዲያ የዛሬው ባለታሪካችን ከነዚህም መካከል የፊት አውራሪነቱን ቦታ ይይዛል ለበርካታ ታዳጊ እና ታላላቅ ሙዚቀኞች የጥበብን ውሃልክ ጠብቀው የተጠመቁ የዜማ ግጥሞችን አበርክቷል። ይኼንን ዘመን በውብ የዘፈን ግጥሞቹ እያስደሰተን ያለው ታናሹ ብዕረኛ ባለተስፋው የግጥም ሀብታምና ሊቅ ወጣቱ ናትናኤል ግርማቸው ገ/ስላሴ🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ናቲ በለጋ ዕድሜው በሳል የሙዚቃ ግጥሞችን በመፃፍ እጅን በመዳፍ የሚያስጨብጡ ፍሬዎቹን በማቅረብ ለድምፃውያን ደጀንነቱን አጎልብቷል። ዘመን ጠመቅ ጭብጦችን እየመዘዘ ኪናዊ ጉልበት እና ውበት በማላበስ ብዕሩን እያተባ የጥበብ ምርታማነትን ወደ ተሻለ ከፍታ የማሻገር ቱባ ተስፋ አስጨብጧል። በወጣት የዕድሜ ክልል ታሽተው ለፍሬ ላይበቁ የሚችሉ ትልልቅ ሃሳቦችን እና ለመረዳት ተጨማሪ ዕድሜ የሚጠይቁ ረቂቅ የህይወት እሴቶችን በተባ ብዕሩ ሲራቀቅባቸው ያስቀናል።" ለውበት የሚሰጠው ትኩረት እጅግ ይደንቃል(አንዳንዶች ግነት አለበት ቢሉም) ይሄን የዛሬው የዳዊት ፅጌ ሙዚቃ ብቻ መስማት የሱን የውበት መነፅር ይገልፃል ባይ ነኝ በአጭሩ ናትናኤል ግርማቸው የዚህ (አሁን ላይ ያለው) ዘመን የግጥም መልክ ነው ማለት እንችላለን። በሀሳብ የበሰሉ ፣ በውበት የደረጁ የሙዚቃ ግጥሞችን ለበርካታ ድምጻዊያን አበርክቷልና። በተጨማሪም የግጥም ደራሲው ናትናኤል ግርማቸው መልከ ቀና እና አመለ ሸጋ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩለታል። እስኪ ለአመታት ለአድማጮች ከደረሱ የሙዚቃ ስራዎቹ ውስጥ ለምሳሌ ጥቂቱን እናንሳ: ዛሬ የጋበዝኳቹ ሙዚቃ የተካተተበት የዳዊት ፅጌ የመጀመሪያ አልበም "የኔ ዜማ ላይ የተካተቱን እትቱ ፣ ደሳለኝ ፣ ኢትዮጵያ የተሰኙ ዘፈኖችን ጨምሮ 5 ሙዚቃዎችን የማስተዋል እያዩ "እንዚራ" አልበም ላይ: መጥቼ ነበር ፣እቴ ፣ደግሰን ፣ጉብልዬ፣ ሳልጥል ዳስ ሙዚቃዎች ላይ በግጥም ተሳትፏል። የራሄል ጌቱ ፦ ኢትዮጵያዬ እና ገዳይ የግርማ ተፈራ ካሣ ፦ መርጦ_ማፍቀር_የለም ለታምር ግዛው :- ምነዋ እና ሌሎችም ሙዚቃዎች የአዲስ ለገሰ ፦ እንጃ የሄዋን ገ/ወልድ ፦ ምን_ይጠቅምሃል ፣ ምነዋ ፣ ሼሙና ለማስተዋል እያዩ ፦ ጀግና የተሰኘውን ነጠላ ዜማና አልበሙ ውስጥ ያሉትን 5 ዘፈኖች ለብስራት ሱራፌል ፦ የቤት_ስራ እና ሌሎች 7 ስራዎች ለታረቀኝ ሙሉ ፦ ስሚያቸው ለተመስገን ታፈሰ ፦ ሳብዬ ለአህመድ ተሾመ ( ዲንቢ ) ፦ አይ_መሬት_ያለ_ሰው እና ሸገር ለጂ መሳይ ከበደ ፦ አገኘኋት የመሳይ ተፈራ ካሣ: "የልቤን" አልበም ላይ በበርካታ ሙዚቃዎች ላይ ተሳትፏል። አብዱ ኪያርና አዲስ ሙላት በጋራ ያቀነቀኑትን የውብዳር የለምለም ኃይሚካኤል "ማያዬ" አልበም የቤተልሔም ሸረፈዲን ፣ የዳዊት መለሠ እና ሌሎችም አልበሞች ላይ ተሳትፏል። ሌሎችም እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ተወዳጅ ስራዎችንና ሌሎች በርካታ የዘፈን ግጥሞችን ያበረከተልን የዘመናችን ጎበዝ ገጣሚ ነው። 📌እስቲ ጥቂት ደግሞ ከናቲ ግርማቸው ድረሰቶች የተወሰኑ ስንኞች መዘን የግጥሞቹን ብስለት እንመልከት 📌(ዳዊት ጽጌ-እትቱ) "በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደጅል እኔስ ባንቺ ጉዳይ ብልጠትን አልከጅል ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ አይኔ አንቺን ካላገኘሁ መንጋቱስ ለምኔ የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደአንጀቴ ወንዙ ዳር አትጥሪኝ መልክሽ ይታየኛል አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል👌 📌 ማስተዋል እያዩ (ጀግና ) "ቀን የሰጠው ለታ ቅል ድንጋይን ሰብሮ ወትሮስ እንደ ጀግና ያውቃል ወይ ፎክሮ አገኘሽኝ እንጂ ድንገት ስዘናጋ ባልቆጨኝ ለፍቅርሽ የከፈልኩት ዋጋ ሳስበው ሳስበው ገባኝ ሳዳምጠው ውስጤን ሽንፈት አልለውም በቃ ባንቺ መበለጤን እንኳን ሰው ደካማው ቀርቶ የፈጠረው ጌታ ተስሞ ተሽጧል በወዳጁ ማታ"🤕 📌አዲስ ለገሠ (እንጃ ) "አውቃለሁ ነክቼ የእርግብ ላባ ስሱን ግን እንዳንቺ ገላ እንጃ መለስለሱን" 📌ተዓምር ግዛው (ምነዋ) አያምጣው ነው እንጂ አያድርስ የሰው ሰው ተወዶ የታል ክስ ምነው ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ በኔው በጭምቷ በረታ ባንተ ቦታ ቢያረገኝ ምነው በሆነኩኝ ግድ የለሽ ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ አይኔን ከፍቅርህ እንዳሸሽ 📌 ግርማ ተፈራ ካሳ (መርጦ ማፍቀር የለም) "ዓይኔ ድንገት ሰርቆ ዓይንሽን ያየውና ሰው ያስታውሰኛል እንደገና ልቤ ከዳፈንኩት እሳት እየጫረ ከገፅሽ ያነባት ጀማመረ እኔስ ምዬ ነበር ላላነሳት ምስሏን በአንቺ ቀርፃው እንዴት ልርሳት"👌🥰 ተቦርነህ ስለ ናቲ ሲናገር "የነ ይልምሽ ገብረዓብ የነ ፀጋዬ ደቦጭ ልጅ የነ መሰለ ጌታሁን ታናሽ ወንድም ነው" ይላል እንዲህ ለሚተጉ ሐሳብ ለሚያሻግሩ አለማመስገን እና አለማድነቅ ንፉግነት ነው ስራዎቻቸውን ጆሮ ሰጥታችሁ ብታዳምጡት አሁን አዲስ መልክ ፣ አዲስ ሐሳብ፣ አዲስ ቀለም አለ ናትናኤል ግርማቸው ዘናጭ ብዕረኝ፣ የበሰሉ ግጥሞች መገኛ፣ ከውብ ግጥሞች ጀርባ ያለ እውነተኛ የዘመኑ ብዕረኛ ክብር እውቅና ይገባዋል እያልኩ ለዛሬ አበቃሁ🙌🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #ዳዊትፅጌ #ደስአለኝ #ethiopianmusic #musictube369

About