@ashe_ye_buzye_lij: #post 1129 | ጉዳዩ፦ ዓመቱን ሙሉ የሚሠራ መምሪያ እንዲኖር ስለመጠየቅ፤ ይህ ሕፃን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ምናልባትም አፉን አልፈታም። በአንገቱ ላይ ያሰረው መስቀል ምን እንደሆነ እንኳን ትርጉሙን አያውቅም። ሃይማኖቱንም ዘሩንም ፖለቲካም ኢኮኖሚም አያውቅም። የሚስቅበት የሚሮጥበትና የሚጫወበት እንጂ የሚማርበት የሚሠራበት ዕድሜ ላይ እንኳን አልደረሰም። ይህንን አይተን እንቅልፍ እንዴት በዓይናችን ይዞራል? እኛ እንዲህ ከታመምን እዚህ ሕፃን ላይ ሰይፍ ያሳረፉ እንዴት ተኝተው ያድሩ ይሆን? የዚህ ሕፃን ኃጢአት ያልሠራች ነፍስ እግዚአብሔር ፊት ስትቆም ምን ብላ ታስፈርድ ይሆን? እሳት አይዘንብ ይሆን? አምና ልክ ይህን ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃት ደረሰ። በበኩሌ በሶሻል ሚድያ ጻፍሁ። ብዙዎችም የተሰማቸውን ኀዘንና ቁጭት ገለጹ። ሆኖም ተጯጩኸን ምንም ያህል ለውጥ ሳይመጣ ተረሳ። መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመቀየር ምንም ነገር ስለማንሠራ ‘ጮኸው ፣ ጮኸው ይተዉታል’ ከመባል በስተቀር ምንም አላተረፍንም። ገዳዮቻችን ግን አላማቸውን አልረሱትም አዘናግተው ደገሙት። ድጋሚ ሲከሰት ያንኑ ዓይነት ጽሑፍ ደግሞ መጻፍ ‘ተመሳሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ’ እንደሆነ ታየኝ። እንደዛ ከማድረግ ደግሞ ከልብ የሆነ ጸሎትና ዝምታ ይሻላል። የሚገርመው ዋናውን ችግር ትተን እርስ በእርሳችን በመናከስና አንዱ ሌላውን በማጥቃትና ማሳጣት ላይ ብዙ ጊዜ አጠፋን። በገላ. 5፡15 ሐዋርያው ‘እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ’ እንዳለው እኛኑ በሚጎዳ መሰዳደብና መፈራረጅ ኃይላችንን ጨርሰን ቁጭ ስንል እነርሱ ግን አሁንም ሌላ ዙር ቀጠሉ። ሞትን ከማስቆም ይልቅ ‘ማን የበለጠ አለቀሰ?’ የሚለው የራስን ጽድቅ የማስመዝገብ (virtue signaling) እሽቅድድምና ‘እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ’ ዓይነት የማርታ ክስ አየሩን ይዞት ዋናው ጉዳይ ተዘነጋ። አሁንም እንደዚህ ሕፃን ያሉ ንጹሐን ከግፍ አላመለጡም። በዚህ ዙር የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ግን በቀጥታ ሀገረ ስብከቱም ቅዱስ ሲኖዶስም ቀድመው ምላሽና መረጃ ስለሠጡ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምን ይጠበቃል? በሚለው ላይ የበኩሌን ሃሳብ ለማዋጣት ዕድል የሚሠጥ ሆኖ ታየኝ። የምጽፈው ‘ብለን ነበር ሰሚ አጥተን ነው እንጂ’ ብሎ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለመመጻደቅ ሳይሆን ውሳኔ ሰጪ አካላት ቢመለከቱት የሚያጤኗቸው ሃሳቦች ከተገኙ በሚል ነው። ከቅዱስ ሲኖዶስ ምን እንጠብቃለን? ቅዱስ ሲኖዶስ በተመሳሳይ ጥቃቶች ወቅት እስከ አሁን ያደረጋቸውን ምላሾች (የሰማዕትነት ክብር መስጠት፣ ጸሎተ ምሕላ ማድረግ፣ መግለጫዎችን ማውጣት፣ መንግሥትን ማነጋገር እና ተጎጂዎችን ማጽናናት) ብንመለከት፤ እነዚህ ምላሾች ቀስ በቀስ እየቀዘቀዙ መጥተዋል። ነገሮች ተባብሰው በመቀጠላቸው የነበሩት ምላሾችም በመቀነሳቸው፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ‘ለመንጋው የማይገደው’ እረኛ አድርጎ በማየት ተስፋ የቆረጠው ሰው ቁጥር እንዲበዛ ምክንያት ሆኗል። ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩት በመንፈሳዊ ትምህርታቸው እና በገዳማዊ ሕይወታቸው ተመልምለው እንጂ በአስተዳደር ዘርፍ ተዘጋጅተው እንዳልሆነ ይታወቃል። ነገር ግን ያለንበት የቀበሮና የተኩላ ዘመን በፍልጥ የመጣውን በፈሊጥ የማስተዳደር ጥበብን ይጠይቃል። ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓት የሚሰበሰበው በጥቅምትና በርክበ ካህናት ብቻ ነው። በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰበሰብ ጉባኤ በየወሩ የሚፈጸም ጥቃትንና በከፍተኛ ፍጥነት የሚደረግ ዘመቻን እንዴት ለማስቆም ይችላል? በዚያ ላይ እጅግ ብዙ የሀገረ ስብከት አጀንዳዎችንና ሀገራዊ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ውሳኔ መሥጠት በዕድሜ አረጋውያን አባቶች ላይ እጅግ አድካሚ ሒደት ነው። ይህ ሁኔታ በየሥፍራው የሚከሰቱ ጥቃቶችን ለማስቆም ቀርቶ በአግባቡ ለማዘን ራሱ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር አይደለም። ቅዱስ ሲኖዶስ ዝም ቢልም ሆነ መግለጫ ቢሰጥ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከመተቸት አያመልጥም። የዚህ ሁሉ መንሥኤ ጉዳዩ በአግባቡ የሚያዝበት አግባብ አለመፈጠሩ ነው። ፣ቤተ ክርስቲያኒቱ ዓመቱን ሙሉ የሚሠራ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ያስፈልጋታል!! ቅዱስ ሲኖዶስ ለግንቦት ቀጠሮ ይዞ አበው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሳይበተኑ በፊት ከጥቅምት እስከ ግንቦት ድረስ ለሚከሰቱ ተመሳሳይ ጥቃቶች እልባት እንዲተዉ እንመኛለን። ይህም ዓመቱን ሙሉ የሚሠራ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ነው። ይህ መምሪያ በየሥፍራው የሚከሰቱ ጥቃቶች ዙሪያ የሚሠራ የአደጋ ስጋቶችን አስቀድሞ የሚያጠናና የሚተነትን ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን ሳይጠባበቅ የቤተ ክርስቲያኒቱንና የምእመናንን ደህንነት የሚከታተል ቢሆን ነገሩ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ሆኖ ከመረሳት እንዲድን ያደርጋል። ይህንን ሥራ የሚሠራው አካል ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ፤ በውስጡ የሕግ ባለሙያዎች፣ የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኤክስፐርቶች፣ የዲፕሎማሲ እና የደህንነት ባለሙያዎች፣ የአይቲ እና የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ቢካተቱበት ቤተ ክርስቲያን ማንም እየተነሣ የፈለገውን ሲያደርግ አቅም እንደሌላት መስላ ከመታየት ትድናለች። ከዚያ ውጪ ወደድንም ጠላንም ቤተ ክርስቲያንዋ ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆንዋ በብስጭትም ቢሆን ቅዱስ ሲኖዶስን ከማጥቃት መቆጠብ የሚጠቅመው ራሳችንን ነው። የመጨረሻው ዘመን አንዱ ምልክት የሆነው የካህናት መገደል የሚጀምረው ከሰይፍ ሳይሆን ከሰብእና ገደላ (character assasination) ነው። በማኅበራዊ ሚድያ አንዱን አባት ወክለው ሌላውን እየሰደቡ በሊቃነ ጳጳሳት መካከል ጠብ የሚያጋግሉ የፌስቡክ አቡነ ቀሲሶች መፈጠራቸው ተቋማዊ ራስን ማጥፋት (institutional suicide) እየተፈጸመ እንዳለ የሚያሳይ ነው። የራሳችንን ቅዱስ ሲኖዶስ ባቃለልንና ውስጣዊ ችግሮቻችንን አደባባይ ባሠጣን ቁጥር የሲኖዶሱን የመደራደር አቅም በገዛ እጃችን እያዳከምን እንገኛለን። እንዲህ ያሉ ጥቃቶች ሲፈጸሙ መንግሥት ተጠያቂ መሆኑ የማይቀር ነው። በሥልጣን ላይ ያለን መንግሥት የሚደግፉትም የሚቃወሙትም ዜጎች እስከሆኑ ድረስ እኩል መብቴን አስከብርልኝ ብለው የመጠየቅ መብት አላቸው። ቅዱስ ሲኖዶስና ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትወክለው አካል በአግባቡ ሥራውን ከሠራ በመንግሥት ወገን ሊደረግ የሚገባው እርምጃ ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ይቻላል። በተረፈ ግን ተስፋ አትቁረጡ:: ለፈጣሪ እንዲህ በሉት:- “መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን?” — ማርቆስ 4:38 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ~~~~ጥቅምት 16 2019 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። (ኤፌ. 4:29-31) #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ #አሼ_ነኝ✌ #ቤቱን_like_share_follow_copylink_repost_ማድረጋችሁን_አትርሱ🙏
Äşĥę Mąñ✍✌
Region: ET
Monday 26 October 2026 11:49:52 GMT
Music
Download
Comments
meskerem :
እግዚአብሔር ሆይ ፍርዱን ካንተ ነው የምንጠብቀው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 16:14:34
11
Estifanos Estifanos dejene :
justice from God only
2026-10-26 15:11:35
0
@Eng.Yosef :
minaw geta gin betam zm ale🥹🥹😭?
2026-10-26 16:26:21
0
ወሰን አልባ :
የዘንድሮ ጳጳስ ሆዱ ካልጎደለ ምን አገባው ህዝቡ ቢያልቅ
2026-10-26 17:25:57
1
amie :
የኔ አጥያት ነው አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ጌታ ሆይ እባክን ማረኝ ሰትምረኝ ይቅር ሰትለኝ ይሄን ሁሉ ግፍ አላይም ነበር
2026-10-26 16:36:20
5
zemed :
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው መኖር እየወደዱ ለተፈጸመባቸው ግፍ መቼም እግዚአብሔር ዝም አይልም የጊዜ ጉዳይ ነው። የእግዚአብሔርን ክንድ ማንስ ይችለዋል የፈጸሙት እና እያዩ ማዳን እየቻሉ ዝም ላሉ አካላት እግዚአብሔር ይፈርዳል መጨረሻቸውም ከእነሱ የከፋ ያድርግላቸው።
2026-10-26 16:42:39
3
@እፎ ነሀሉ ምስለ ሰብእ ከሰዉ @🙏21#እናቴ :
በሲኖዶስ ላይ ችግር አለ
2026-10-26 16:54:19
1
Ashebir Taye :
እግዚአብሔር ይፍረድ አቤቱ ህዝብህን አድን
2026-10-26 15:58:55
5
TESHOME :
ፈጣሪ ይፍረድ
2026-10-26 16:49:36
1
mulugieta :
እይይይይይ
2026-10-26 18:04:53
0
kaleab :
የእስራኤል አምላክ ሆይ🙏🙏🙏
2026-10-26 16:37:53
1
zemarit adna moges :
ወይኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-26 18:03:28
0
zin :
ጌታ ሆይ በቃ በለን በኛ ሀጢያት እፃናቱ አይቀፀፉ
2026-10-26 16:41:12
1
user7549852024018 :
ፈጣሪ ሆይ የምህረት እጅህን ዘርጋልን !!
2026-10-26 16:44:51
1
jone Tocha :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ድነግል ማሪያም ድረሸልን
2026-10-26 16:44:21
1
user83145197794376 :
እግዚአብሔር ሆይ እረ በይቅርታህ አስበን
2026-10-26 16:40:00
1
Fast :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭አርሲ አዝነናል
2026-10-26 17:59:52
0
@M love.9 :
ፍትህለአርሲ ክርስቲያኖች
2026-10-26 13:29:46
2
user9720231712147 :
😭😭😭
2026-10-26 13:21:03
1
Beti ye 27 :
የእስራኤል ቅዱስሆይ ስለምን ዝምአልከን?😭😭😭😭
2026-10-26 17:56:09
0
Zekarias demise Demise :
እግዚአብሔር ጻዲቅ ፈራጅ ነው!!!ጽዋው ሲሞላ አቤት የሱ ፍትሕ አሰጣጥ"ማን በፊቱ መቆም"ይችላል!!
2026-10-26 18:04:21
0
afomiya :
አምላክችን ሆይ እንደ ሃጢያታችን ሳይሆን እንደቸርነትህ አስበን ህፃናቱን አስባቸው!!!!!
2026-10-26 18:05:10
0
አርሂቡ የእጅስራዎች :
እመብርሀን እመብዙሀን የጌታዬ እናት ሰማእቱን ቅዱስ ጊዪርጊስን ይዘሽ ነይልን
2026-10-26 18:06:10
0
𝐘𝐚𝐫𝐞𝐝𝐚 :
“መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን?” — ማርቆስ 4:38
2026-10-26 17:58:34
0
Engidawork :
Amemen mnorem telan tolo na abete
2026-10-26 13:43:09
0
To see more videos from user @ashe_ye_buzye_lij, please go to the Tikwm
homepage.