@ilkin7660:

fff7777
fff7777
Open In TikTok:
Region: AZ
Monday 26 October 2026 13:11:23 GMT
3621
28
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @ilkin7660, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ጠይም 😮‍💨 ✍️ በፈረንጆች 1989 ዓም አስቴር አወቀ አሜሪካ ሀገር መኖር ከጀመረች በሗላ ለአለም ያስተዋወቃት አልበም ነው ይሄ ዛሬ የጋበዝኳቹ አስቀድሞ ከሸበሌ ባንድ ከዛም በድጋሚ የተጫወተችው
ጠይም 😮‍💨 ✍️ በፈረንጆች 1989 ዓም አስቴር አወቀ አሜሪካ ሀገር መኖር ከጀመረች በሗላ ለአለም ያስተዋወቃት አልበም ነው ይሄ ዛሬ የጋበዝኳቹ አስቀድሞ ከሸበሌ ባንድ ከዛም በድጋሚ የተጫወተችው "ጠይም" የተካተተበት ድንቅ አልበም ታዲያ በርካታ ድንቅ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሲሆን የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ ኢትዮጲያውያን የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾች ተካተውበታል የአድማስ ባንዶቹ ሄኖክ ተመስገን ቤዝ ጊታር፣ አበጋዝ ሺዎታ ኪቦርድ እና ካሱ አድማሱ ክራር በወጣትነታቸው ወደ ኢትዮጲያ ከመምጣታቸው በፊት የተጫወቱበትም ነበረ ታዲያ በ triple earth በኩል ለአድማጭ የደረሰው ይህ አልበም ጥራቱ አጀብ የሚያስብል ነበር ይሄንንም ተከትሎ በበርካታ መድረኮች ላይ እንደ ሰበቡ አይነት ሙዚቃዎችን እየተጋበዘች ለማቅረብ ችላ እንደነበር ይታወሳል👌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን በግሌ እጅግ የመውደው የማከብረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስጦታ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺዎታ 🙌ከኢትዮጲያዊ አባቱ እና ከነርስነት የሞያ ባላቤት ጃፓናዊ እናቱ በነጮች አቆጣጠር ነሀሴ 28,1964 G.C በጃፓን ነበር የተወለደው ገና የ 1 አመት ልጅ እያለ ነው ወደ ኢትዮጲያ የመጣው...ያደገውም በኢትዮጵያ ነው ...ቅዱስ ዮሴፍና ሊሴ ገ/ማርያም ከተማረባቸው ትምህርት ቤቶች የሚጠቀሱት ናቸው~አበጋዝ የሚለው ስም የቅድመ አያቱ ስም ነበር....ቅድም አያቱም "አበጋዝ አባተ" ይባላል!~ታዲያ የቅድመ አያቱ ስም ለሱ መጣሪያነት ሊሆንበት የቻለበት ምክንያት አባቱና የአባቱ የአክስት ልጅ ከዝምድናው ባሻገር አያተቸውን የሚወዱ ልጆች ናቸው...."ወንድ ልጅ ከወለድን እኔ ነኝ ቀድሜ "አበጋዝ" የምለው" የሚል ፍክክርም ይገጥማሉ በወቅቱ!~ታዲያ ከብዙ ጊዜ መለያየት በኋላ እነዚህ ሁለት ሰዎች ሲገናኙ እንዳቀዱት ሁለቱም ወንድ ልጅ ወልደው ሁለቱም ስማቸውን በአያተቸው ስም አበጋዝ ብለው ነበር የሰየሙት!~ይሁን እንጂ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ነፍስ ማወቅ በጀመረበት ጊዜ በጓደኞቹ ሙድ ስለሚያዝበትና ከመልኩ ጋር ስሙ ስለማይሄድ በወቅቱ የራሱን ስም ይጠላው ነበር! ~እያደገ ሲመጣ ግን ስሙ የተለየና ብዙ ሰው ላይ የማያየው unique ስም እንደሆነ ሲገባው እጅግ ወደደው! ~አበጋዝ በልጅነቱ እንደማንኛውም ወንድ ልጅ ኳስ መጫወትን ይመርጥ ነበር ለሙዚቃ ብዙም ፍቅር አልነበረውም....ፒያኒስት የመሆን ህልሟ ያልተሳካው እናቱ ግን እግሮቹን ለኳስ ከመፈቅድ ይልቅ በእጆቹ እጣቶች ፒያኖ እንዲጫወቱ አደረገች አስገደደችው ጭምር!...በወቅቱ አበጋዝ ባይፈልግም በእናቱ ተፅዕኖ ምክንያት ሙዚቃ መሳሪያ መጫወትን ሀ አለ በልጅነቱ...ታዲያ በግዴታ በእናቱ ምክንያት የጀመረው የአበጋዝና የሙዚቃ ጋብቻ በቀላሉ የሚፈታ አልነበርም...የእድሜ ልክ እስኪመስል እስካሁንም የፀኑ ናቸው!~አበጋዝ ኤልክትሪካል ኢንጅነሪንግ ሊማር ጀምሮ ትቶት ነው ወደ ሙዚቃው አለም የገባው. ...ኋላ ላይ የ sound and Audio engineer መሆኑ ግን አልቀረም!~አበጋዝ የደረጀ መኮነን አድናቂና ነው...ወደ ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ዓለም የገባው እንደዚህ ነበር....በነጮች በ 1975/76 G.C በዳዊት ይፍሩ ተመስርቶ ዝናውን ባከባተው በዳህላክ ባንድ ከሰሩ ሰዎች ጋርና በዚህ ባንድ ውስጥ ሲሰሩ ከነበሩ ስመጥር ሙዚቀኞች ጋር አብሮ የመስራትና ልምዱን የማካበት እድል አገኝቷል አበጋዝ! ~በ 1970s G.C አቆጣጠር በሙላቱ አስታትቄ ፣ በነ ሀይሉ መርጊያ ፣ በግርማ በየነ ፣ በሞገስ ሀብቴ የተመሰረተው ዋልያስ ባንድ ሌላኛው በወቅቱ የነበረው ዝነኛው ባንድ ነበር ....ነገር ግን ይሄ ባንድ የሙዚቃ ቱር ያደርጋሉ ወደ አሜሪካ በ 1981 G.C አቆጣጠር ~ታዲያ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ካቀረቡት ሙዚቀኞች መካከል ሀይሉ መርጊያና ሞገስ ሀብቴ በወቅቱ በነበረው የደረግ አገዛዝ ስላልተመቻቸው ወደ ሀገራቸው አልተመለሱም ነበር!~ሌላዌ ባንድ ጊዜውን ጠብቆ በ 1981 G.C አቆጣጠር ከፈረሰው ከዳህላክ ባንድና ከዋቢ ሸበሌ ባንድ ሙዚቀኛች ተወጣጥተው "Ethio star " የሚባል ባንድ ይመስረታል!~በዚህ ባንድ ውስጥ ነበር የ professional ስራውን በክፍያ "1" ብሎ የጀመረው አበጋዙ ክብረወርቅ ሺኦታ!~በ 1982 በክፍያ በኢትዮ ስታር ስራ ሲሰራ አበጋዙ....በ 400 እና በ 500 ብር በወቅቱ ደህና ክፍያ እየተከፈለው በዚህ ባንድ ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያ ከመጫወት በተጨማሪ በቅንብር ተሳትፏል... አሻራውን ያሳረፈባቸው ስራዎች በአልበም ደረጃ አምስት ይጠጋሉ...የሙሉቀን መለሰን "ውሃ ወላዋይን" ጨምሮ!~በስራው በታታሪነቱና በብቃቱ የሚገረመው ሙሉቀን መለሰ በ 1984 G.C ወደ አሜሪካ ቱር ሲያደርግ ካሉት ሙዚቀኞች ውስጥ አበጋዝን መርጦ ይዞት ይሄዳል!~ወደ አሜሪካ በሄደበት ጊዜ ነበር ከሱ 4 አመት ቀድሞ አሜሪካ የገባውን ታዋቂውን የ ቤዝ ጊታሪስት ተጫዋችና የልቡን ጓደኛ "ሄኖክ ተመስገን" ያገኘው!~ታዲያ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ያላሰበው አበጋዝም በ 1984 G.C "አድማስ ባንድን" ከጓዶኛቹ ጋር መሰረት!~የዚህ የአድማስ የባንድ አባላትም1.አበጋዝ ክብረ ወርቅ ~ሲንተሳይዘር/ፐርከሽን/ድራም እና ኪቦርድ2.ሄኖክ ተመስገን ~ቤዝ ጊታሪስት3.ቴዎድርስ አክሊሉ ~ ኪቦርዲስት4.ዮሴፍ ተስፋዬ ~ድራመር~ታዲያ ከዚህ ባንድ አባላት ጋር በአንድ አፓርታማ በኒዮርክ ነበር የሚኖሩት! ~በአድማስ ባንድ በ 1984 G.C ...6 በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተሰራ፣ 1 ደግሞ ድምፅ ያለው ዘፈን (ስሞን በየነ ዘፋኙ) በአጠቃላይ 7 ዘፈኖችን የያዘ "Sons of Ethiopia " የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ለቀቁ!ዘፈኖቹም 1.አንቺ ባለ ጋሜ 2.ባህታስ ... 3.ትዝ አለኝ የጥንቱ 4.ካላጣሽው ዋጋ 5.ሳምባ ሸጊቱ 6.አስታውሳለው (ስሞን በየነ ድምፅ) 7.ወደ እናቴ~ ታዲያ በዚህ አልበም ውስጥ ethio jazz ስልቶችን ከምዕራባዊያን መዚቃ ስልቶችን (ሳምባና ሬጌ) የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃ መሳሪያዎችን በመጠቀም ነበር ለአለም ያስተዋወቁት!~ይሁን እንጂ 1986 G.C ይዞት የሄደው ሙሉቀን መለሰ ሙዚቃ አቆመ የዚህ ጊዜ ነበር...የመድረክ ፐርፎርማንሱና ቱሮች ሲቀሩ አድማስ ባንድም ሆነ አበጋዝ ትንሽ ነገሮቹ የከበዳቸው!~ከዛ ግን ሰርጎችንንና የተለያዩ ክለቦች ውስጥ መስራት ጀመሩ!~ታዲያ በዚህ ህይወታቸው እሱና ጓደኛው ሄኖክ እንደ ገጠመኝ ከሚያስታውሱት አንድ Negarit የሚባል ክለብ ላይ በሚሰሩበት ስዓት ድራመር ካልተጨመረ ብለው ከስራ መባረራቸውና በወቅቱ ገንዘብ ማጣታቸው አሜሪካ ውስጥ አንዱ ገጠመኛቸው ነበር ይሄ!~ታዲያ በ 1991G.C ነበር አበጋዝ ጓደኛውን ሄኖክን ተከትሎ ወደ ቦስተን "Berklle Collage of music" ለመማር የገባው.....በ 1995 G.C በዚህ የሙዚቃ ትምህርት ቤትም በ "Jazz Composition and performance (professional music ) " በባችለር ዲግሪ ተመረቀ!~ታዲያ ከዚህ የሙዚቃ ትምህርት በኋላ እንደ አዲስ አበጋዝ የስራ ብቃቱን ጫፍ ለአለም ማሳየት ጀመረ... ይቀጥላል... 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #አስቴርአወቀ #ጠይም #ethiopianmusic🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #musictube369

About